የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሀጽዮን ከCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን “የአፍሪካን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ማፋጠን እና ለተለያዩ አደጋዎች የመቋቋም አቅሟን ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።
ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአደጋ ትንበያዎችን ወደ ተግባራዊ የቅድመ መከላከል እርምጃ መቀየር ያለውን ወሳኝነት አጉልተው አስረድተዋል።
በተጨማሪም ለአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ ማኅበረሰቦችን ለመጠበቅ፦
· የዝግጁነት አቅምን ማሳደግ
· የአየር ንብረት መረጃ ተደራሽነትን ማሻሻል እና
· ዘላቂ የፋይናንስ ምንጮችን ማሰባሰብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።