Телеграм

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

@eotcgssu21 Религия и эзотерика
РКН: проверяем Не иноагент

Статистика обновлена 15.11.2026 в 04:27 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики16 987
Охват поста6 122 36% от подписчиков
ERR за месяц36,04%
ERR за 24 часа36,04%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU tg16 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የአርሲ ሰማእታት እና የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን አስመልክቶ ወቅታዊ መልእክት።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፤በአርሲ በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ሊገታ ያልቻለ እና ከልካይ የሌለው ተከታታይ ግድያ ምክንያት እጅግ አዝነናል ። በዚህም ለኦርቶዶክሳውያን ይልቁንም ለሰማእታት ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን።

የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ሞት ፣ መፈናቀልና ስደት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍቶ ይገኛል።
በቀቢፀ ተስፋ ውስጥ የወደቁትን፤ የሚታደጋቸው ሸተው በጭንቀት ያሉትን ቤት ይቁጠራቸው። ሃይማኖታቸው ምክንያት ሆኖ ግድያ ፣ ጥቃት ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ የሚደርሰባቸው ወገኖቻችን ጩኸት ተበራክቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋግሞ እየተፈጸመ ያለውን የኦርቶዶክሳዊያን ሞት ፣ ስደት እና የአቢያተ ክርስቲያናት ቃጠሎን አስመልክቶ የወግዘትና የሐዘን መግለጫ ቢያወጣም መከራውን አልቆመውም ። ተጨባጭ መፍትሔ ማምጣትም አልተቻለም።

በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ
ይኸን ተከታታይ ማቆሚያ የሌለው ዕልቂት አስመልክቶ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሊቃውንት ፣ ምዕመናን እና ወጣቶች ያሳተፈ የምክክር ጉባኤ በመሰየም በአርሲና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸሙትን ኢሰብዓዊና ሰይጣናዊ ድርጊቶችን በጥናት በመለየት ፤ ምክንያታቸውን በመተንተን የአደጋ መከላከልና የተጎዱትን የማበርታት ሥራ እንዲሁም የአንድን ዜጋ በነጻነት የመኖር እና የማምለክ ህገ መንግሥታዊ መብቱን ባላስጠበቁ የመንግስት አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ መንግስትን በመጠየቅ እና ኃላፊነትን ባለመወጣት ተጠያቂነት እንዲሰፍን በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ በትህትና በልጅነት መንፈስ እናሳስባለን ።

ከዚህም በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ ሩፉኤልን የሚመሩት ኢህጉረ ስብከት አስመልከቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ
ጥቅምት 16 እና 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሰፊው መወያየቱንና በርካታ ማስራጃዎችን ጉባኤው ማዳመጡን ተረድተናል። በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተፈጸሙ የተባሉ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰቶች ለመስማት የሚዘገንኑ እንኳን አማንያኑን ኢአማንያንን የሚያስደነግጡ ፤ አንገትን የሚያሰደፉ እኩይ ተግባራት መሆናቸውን በሚገባ ተገንዝበናል ።


የተፈጸመውን አስተዳደራዊ እና ቀኖናዊ ጉዳዮች ጥሰት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ ያለ ልዩነት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የማስጠበቅ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል። ጥቂት የሀሳብ ልዩነቶች መፈጠራቸውን ታዝበናል። ይኸ የሀሳብ ልዩነት ቀኖና እና ህገ ቤተክርስትያንን ከመጠበቅ አንጻር የቀረበ እንዳይደለ ተረድተናል ። በተፈጸሙ አሳፉሪ ድርጊት አንገታችንን የደፋነው ሳያንሰን የአደባባይ ምስጢር በሆነው ጉዳይ ላይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ያለ ልዩነት አልመወሰን ራሱን የቻለ የቀኖና ጥሰት ነው ። ይህን ጉዳይ በሕገ ቤተክርስትያን መሠረት አድርጎ አለመወሰን ለነገም የሲኖዶስን ልዕልና ያሳጣል ሥርዓት አልበኝነትን ያነግሳል ። ስለሆነም ምልዐተ ጉባዔው ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የማስጠበቅ ፍጹም የማይሽራረፍ መንፈሳዊ ግዴታውን በምልዐት እንዲውጣ በትህትና እናሳስባለን ።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
👁 6.1 тыс. ❤ 64👍 30👏 10 ↻ 24 28 октября