በ2019 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 21 እና 22/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ
● የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ
● የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ
ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● መጠኑ 3×4 የሆነ አራት ፎቶግራፎች፣
● ዲጂታል መታወቂያ፣
● ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ።
@tikvahuniversity