የሕዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥና የባለ አደራ አስተዳደሩ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የጀነራል ገብረእግዚአብሔር በየነ በቅፅል ስማቸው ወዲ አንጥሩ ልጅ በታጣቂዎች ተገደለ። የቀብር ሥነስርአቱም መቐለ ዓዲ ሹምዱሑን በሚገኘው የማሪያም ቤተክርስትያን መፈጸሙ ታውቋል።
በናይጄሪያ የተደራጁ ወንጀለኞች ከአንዲት ገጠር ነዋሪዎች ጋር በፈጠሩት ግጭት ከ 50 በላይ ሰዎች መገደላችው ተሰማ።
በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ሲጓዙ የነበሩ 3 የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በፈንጂ መንጎዳቸውን የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ አስታወቀ። አብዮታዊ ዘቡ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ እነዚህ ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የቀዘፋ ራዳራቸውን አጥፍተው በደቡባዊ የሰርጡ ክፍል በድብቅ ለማለፍ ሲሞክሩ በባሕር ውስጥ በተጠመደ ፈንጂ መጋየታቸውን አስታውቋል።
ሩስያና ዩክሬይን በሚቀጥሉት ሳምንታት የሰላም ድርድር ያደርጋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት አንዱ በሌላኛው ላይ የሚፈፅሙት ጥቃት እንደቀጠለ ነው። ሩስያ በዩክሬይን ድሮኖች በደረሱ ጥቃቶች 3 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉብኝ ስትል የዩክሬይን መንደር መቆጣጠሯንም አስታውቃለች።
በተለያዩ የአሜሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች በተፈጠረ የግንኙነት ችግር ከ10,000 በላይ በረራዎች መሰረዛቸውን የሐገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ገለፁ። የብልሽቱ ምክንያት የሳይበር ጥቃት ለመሆኑ እስከአሁን ማስረጃ አልተገኘም ነው የተባለው።
https://pepurl.com/p/5PSS0?at_medium=Messenger&at_campaign=Telegram&at_channel=DW_Amharic&at_dw_language=am