( ርዕስ - ከየቱ ነህ አንተ? )
አንዳንድ የሰንበት ፅንስ ፥ አጓጉል ያደገ
የነገርን ዱካ ፥ ሰርክ እየፈለገ
አገር በእሳት ስትነድ ፥ ዳር ሆኖ ይሞቃል
እናት እርቃን ቆማ ፥ በሀፍረቷ ይስቃል
ኢትዮጵያን ረግሟት ፥ ጠላቷን ያደንቃል።
እስኪ ልጠይቅህ ፥ ከየቱ ነህ አንተ?
ወሬ ከሚነዳው ፥ ሽብር ከሚነዛው
ከታረዘው ደርሶ ፥ እንደ ኖህ ዘመን ሰው
በንስሓ ዕድሜ ላይ ፥ በርበሬ ነስንሶ ፤ በሀዘንተኛው ሀገር ላይሟርት ከሚዘራው
ወይስ ለጽናቷ እንደ ነህምያ ፥ ተግቶ ከሚሰራው
ከየቱ ነህ ?
ቁልቁል እያሳዩት ፥ ሙት እየቆጠረ ፥ እኝ እኝ ከሚሉቱ
በእርግማን ተጠምደው ፥ በስድብ ትጥቅ ታጥቀው ፥ ስተው ከሚያስቱ
ከመፍትሔው ይልቅ ፥ ችግር ብቻ ይዘው ከሚጨነቁቱ
ወይስ ከበረቱት ፥ ይሄ ቀን እንዲያጥር በጾም በጸሎቱ
ከየቱ ነህ አንተ ?
ሚናህስ ምንድን ነው ?ምቾት
እስኪ ኅሊናህን ፥ ለሰከንድ ጠይቀው
ከየለሁበትም ፥ ከአያገባኝሙ
“ሲያሻቹ ተጣሉ ፥ ስትሹ ተስማሙ
ተንኮል ክፋታችሁ ፥ ጎርፍ ሆኖ እስኪወስደኝ
ልብላ ልልበስ ላጊጥ ፥ ታውኝ ላይ ነኝ”
ከሚሉት ሰነፎች ነው የምትቆጠር ...?
ወይስ ስንቅ አጉራሽ ነህ ፥ የደህና ልጆ እጦት ላሰቃያት ሀገር
ክንደ ብርቱ እናትህ ፥ ቤቷ ጭር ብሎ
ዓይኗ ሰው ተርቦ ፥ መልኳ ክሰል መስሎ
በመበታተን ሟርት ፥ ጀሮዋ እየደማተለመደ
በጸሎት ካልደከምክ ፥ በጾም ካልበረታህ ፤ የክፉ ቀን ደራሽ ልጇ አይደለህማ።
የወገን ሞት ዜና ፥ ከራስ ተዋረደ
እንደ ደህና ነገር ፥ ሰበር
ላንዱ የሚያዝን ሆድ ፥ ላንዱ እየጨከነ
ከሞት ሞት በመምረጥ ፥ ልባችን ባከነ
ያች ያች የአብሮነት ሀገር ፥ አውሬነት ከፋባት
ብርሃንን እየሻተች ፥ ዳግም ጉም ጋረዳት
ታዲያ ለዚች ሀገር ፥ ከተዋሕዶ አብራክ ለተከፈለችው
በእግዚአብሔር ይመስገን ፥ አፏን ለፈታችው
ቅዱሳን ስውራን ፥ ታምር ለሰሩባት
በቃልኪዳናቸው ፥ ትውልድ ላዳኑባት
ለዚች ቅድስት ሃገር ፥ ቀኑ ሲጨላልም ፥ ዘመኑ ሲከፋ...
“የተዋሕዶ ልጅ ነኝ ፥ ለማተቤ ታማኝ
ተቀምጨ ማላይ ፥ አንድ እናት ሀገሬን ፥ መከራ ሲቀማኝ”
ብሎ የሚቆም ጀግና ፥ የክፉ ቀን ደራሽ ፥ እንዴት ጎበዝ ይጥፋ/2/
እናት ተዋሕዶ ጠላት ተነሥቶባት ፥ ቅጥሯ ሲነቀነቅ
የነገሥታቱ ክንድ አያገባኝ ገብቶ ፥ ከመቅደሷ ሲዘልቅ
ለማተባቸው ክብር ፥ ሺወች ሲንገላቱ
“የእምዬን ክፉ አልይ ፥ እኔን ያስቀድመኝ” ፤ ብለው ከሚቆሙት ቀኝ አዝማቾች አንዱ
ወይስ ጠላት ሰፈር ፥ እሳት ለመሞቅ ፥ ማልደው ከሚሄዱት
ወይስ ተስፋን ታጥቀው ፥ ተባብረው ተናበው
መላ እየመቱ ፥ ዘርን አደላድለው ፥ ነገር ለማሳመር ከሚታገሉቱ
ወይስ በእውር ድንብር “ልንጠፋ ነው በቃ” ፤ በሚል ድኩም ዜማ ሀገር ከሚያውኩቱ
ከዋናው ሞት ቀድመው ፥ በሃሳብ ከሚሞቱ ?
እንደ ሃገር ታመናል ፤ እንደ ሀገር ደክመናል ፤ እንደ ሀገር ሰክረናል
ነገር የሚያሰክን ፤ ልብን የሚመልስ ፤ መድኃኒት ያሻናል
ብለው በመጨነቅ ፥ ከተዋሕዶ ዛፍ ፥ መድኃኒት በማግኘት ከሚሽቀዳደሙ
እነሱ ተፅናንተው ፥ በመዳን ቃል ተስፋ ፥ ወገን ከሚያክሙ
ወይስ ካዳር ቁመው ፥ አገልጋዩን ነቅፈው ፥ ካህናት ከሚያሙ
እኮ ከየቱ ነህ ?
ድርሻህስ ምንድን ነው ?
እንደ ጻድቁ ኖኅ ፥ የማንቂያውን ደወል ፥ ለትውልድ አስታዋሽ
መርከብ አዘጋጅቶ ፥ ክፉ ቀን የሚያልፍ ፥ ቤተሰቡን ቀስቃሽ
ወይም እንደ ዮናስ ፥ በብርቱ ጩኸቱ ፥ ህዝቡን ከሐጢአት መላሽ
ወይስ ሰነፍ ታካች ፥ ለትውልድ የማይተርፍ ፥ ለራሱ የማይበቃ
ሀገርና እምነቱ ፥ ሰርክ እየተጠቃ
ሺ ቀስቃሽ ቀስቅሶት ፥ ሺ ጊዜ የማይነቃ
ወይስ ወይስ ወይስ ... ከየቱ ነህ ?
ምንጭ ፦ ( MK EOTC )
የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል