ኢትዮጵያ ውስጥ በኢስላም ስም የተተደራጄ ወይንም እነርሱ በሚሉት በወሀብያ ስም የተደራጄ አንድ ታጣቂ አንድ የፖለቲካ አደረጃጄት የለም!
በኢስላም ስም የማታገል የሚገድል የሚያሳድድ የሚያወድም አንድ ሀይል የለም አንድ እንኳ!!!
በኢስላም ስም እጅ የቆረጠ የለም!
በኢስላም ስም አንበርክኮ የረሸነ የለም!
በኢስላም ስም " በስመአብ ብለህ እረ¶¶¶ደው " እንዳሉት ያደረገ የለም!
በኢስላም ስም ከመስጅድ ሆኖ የጦርነት አዋጅ ያወጄ የለም!
ተገድለሀል መስጅድህ ፈርሷልና ሌላው ሀይማኖት ተነስ ብሎ ያለ ሀይል የለንም!
ኢትዮጵያ በሙስሊም ትመራ ብሎ የታገለ አንድ ሀይል የለም!
ግና በተቃራኒው ከወለጋ እስከ አክሱም ፤ ከወሎ እሰከ ጎጃም ፤ ከጎንደር እስከ መተከል በኦርቶዶክስ ፣ በፕሮቴስታንት እና በዋቄፈና ፅንፈኞች የሚገደለው የሚጨፈጨፈው የሚሳደደው ሙስሊሙ ነው።
መስጅዱ እንደ ሻማ የሚነድበት ፤ እየታገተ ከፍሎም የሚገደልበት ሙስሊሙ ነው!
ንብረቱን ጥሎ የሚሰደደው ፤ ሀገር አልባ የተደረገው ሙስሊሙ ነው!
በየስደተኛ ጣቢያ ታጉሮ "ራሳችንን አንገድል አላህ ይቆጣብናል" እያለ የሚያለቅሰው ሙስሊሙ ነው!
አፈጠርክ ሰገድክ መቃብር ቀበርክ ተብሎ የሚረሸነው
ሙስሊሙ ነው!
ግና መታኝና አለቀሰ ቀደመኝና ከሰሰ እንዲሉ ራሳቸው ገድለው አሳደው አፈናቅለው መልሰው " ወሀብያ አራ¶¶ጅ¶ጅ" ነው ይሉናል። አያፍሩም። መሳጅዶቻችንን አውደመው ራሳችሁ አወደማችሁት ይሉናል።
ቁርአናችንን ቀዳደው ራሳችሁ ቀዳዳችሁት ይሉናል!
እስኪ የትኛው በማን የሚመራው የወሀብያ ድርጅት አጠቃችሁ ብላችሁ ጠይቋቸው ! አይመልሱላችሁም መልስ የላቸውምና!
እኛን በሀይማኖታችን ያጠቁናል።
ከዚያ እነርሱ በብሔር ግጭት ሲጠቁ ወሀብያ ብለው ይሰይሙና በጋራ ዘመቻ ይከፍታሉ!
ለነርሰሱ መከላከያው ወሀብያ ነው ፣ ፖሊሱ ወሀብያ ነው ! መንግስቱ ወሀብያ ነው!
አርሲ ላይ እስኪ አንድ ሙስሊም የትጥቅ ድርጅት ያሳዩንና እንፈር!!
ኧረ እንቅፋት ራሱ ቢመታቸው ወሀብያ ነው!
በተረት ተወልደው በተረት አድገው በተረት በሚገድሉ አካላት ጋር እንዲንኖር ፈረደብን። ተናግሮ ሊግባቧቸው የማይችሉ የ 15ኛው ክፍለ ዘመን ነዋሪያን እንኳ ለመሆን የማይመጥኑ አካላት ጋር መቁሰል እጣፈንታችን ሆነ!
ሙስሊሙ ድምፁን አጥፍቶ ከመስራት ከመነገድ ውጭ እዚህች ሀገር ላይ በሚደረገው የቆሸሸ መገዳደል ውስጥ እንደ ሀይማኖት እጁን አላስገባም።
የትኛውም የኢስላም ሀይማኖት መሪ ተገዳደሉ ብሎ አልባረከም!
አላደረገም ! ይህንን ያውቁታል።
ማን በየእምነት ተቋማቱ ጅምላ መሳሪያ አሽጎ እያሰለጠነ ለሽብር እንደሚያውል ያውቁታል!
ሁሉም ያውቀዋል!
እሺ ከነዚህ ጋር እስከመቼ ስንቆስል እንኑር!
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial