Телеграм

አርምሞ🧘🏽‍♂

@Armemo_offical История и философия
РКН: проверяем Иноагент: проверяем
ጥ ቂ ት ም ና ኔ. .🧘🏽‍♂️

Статистика обновлена 15.11.2026 в 01:26 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики12 186
Охват поста2 374 19% от подписчиков
ERR за месяц19,48%
ERR за 24 часа10,12%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
አርምሞ🧘🏽‍♂ tg12 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
🗣

ለሚኖር መሰንበት አጥሮ ፥ ሰባና ሰማንያ 'ራቀው
በለሱን አንቆሮ ተፍቶ ፥ በዋጠ ማግስት አነቀው፤
ሙታንም ለራስ አንብቶ ፥ በቁሙ ህይወት ተራበ
ሰማየ ሰማያት ሲመኝ ፥ ከጽድቁ ውድቁ ቀረበ፤

              ያ ምስኪን ድሃ ገበሬ
              ቢጸልይ ለመኖር ዛሬ
              ምሽቱን ሽፍታ ላከበት
              ተኝቶ በደረቅ ቁርበት
            ቀረለት ዛሬን መሰንበት
        ማጣት ላይ ሞት አክሎበት።

እናማ እንዲህ ቢገጥመው ፥ አምላኩን ቆሞ ከሰሰው
አምላክም የዋዛ አይደለም ፥ ድጋሚ በመኖር ካሰው፤
መታተር የማይሰለቸው ፥ ይህ ምስኪን ድሃ ገበሬ
ሰማይን ዝናብ ሲለምን ፥ ማዕልቱን አጥምዶ በሬ
ምሽቱን ገዳይ ላከበት ፥ ከስቃይ ሊገላግለው
አምርሮ አምላኩን ሲከስ ፥ ዘላለም ህይወት አደለው።

ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ አምርሮ ቃሉን ደገመ
     በስጋው ስቃይ የበላ ፥ ከነፍሱ ያላገገመ
ድጋሚ መኖር መቀጣት ፥ መሰንበት የተረገመ..

  ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ ይልቅ ይህን አነሳ
     በደሌን ይቅር ብትለኝ ያንተንም እንደምረሳ
    አባት ሆይ ፈተና በቅቶ ፥ ከክፉ የምታድነን
ሞት የለሽ ሞት እየሰጠ ፥ መከራን 'ምትገላግለን
ዘላለም ህይወት ሰርዘ ፥ ከመኖር ቀድመ ስትገድለን!


            @Imagination_officially
👁 1.4 тыс. 👏 13❤ 11😁 1 💬 4 ↻ 15 12 ноября
አርምሞ🧘🏽‍♂ tg12 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ስለዚህም ነው ይህን የምላችሁ፤ የምታነሱት ሃሳብ ከአንድ መፅሃፍ ጥቅስ በዘለለ የተሻለ የአዕምሮ ፈተና አይጠይቅም!። ስለፈጣሪያችሁ መኖር ከዚህ ቅዱስ መፅሃፍት በተሻለ ተፈጥሮ ትመሰክራለች። ልክ እንደ ሱፊው ታሪክ ነው። ይህን ታሪክ ያገኘውት ኃይለጊዮርጊስ ማሞ ከተረጎመው ጥበብ ከጲላጦስ መፅሐፍ ላይ ነው።

ሰውዬው የሱፊውን መምህር እየዘለፈ ነው፦«በአይናችሁ አይታችሁ በእጃችሁ ዳሳችሁ የማታውቁትን አምላክ አለ ብላችሁ ታመልኩታላችሁ!። እሰቲ ምን ማረጋገጫ ኖሯችሁ ነው የምታመልኩት?»

መምህሩ ጥያቄውን በጥያቄ መለሱ፦«በበረዓ መንገድ ላይ በትልቁ የግመል ዱካ ተዘርግቶ ብታይ በዛ ቦታ ግመል ማለፉን ትጠራጠራለህ?»

ሰውዬው፦«በርግጥ ዱካውን ካየው ስለምን እጠራጠራለሁ። አዎ አምናለሁ ማስረጃው በዛው አለ»

መምህሩ፦«እኛም ፈጣሪ ስለመኖሩ ለማመን የግድ እሱን ማየትና መዳሰስ አይጠበቅብንም።
ዛፉ፣ ባህሩ፣ ሰዎችና ተፈጥሮ በጠቅላላ ፈጣሪ ስለመኖሩ የማስረጃ ዱካ ናቸው።»

መጨረሻም ላይ የዚህ ታሪክ መዝግያ ያደረግኩበት ምክንያት «Natural Theology» ማለትም የተፈጥሮ ሥነ መለኮት ፍጥረታት የፈጣሪ መኖር ለማረጋገጥ የሚቀርቡ በቂ ማስረጃ መሆናቸውን ለመናገር ነው። እቺ ታሪክ ብቻ ሦስት የፍልስፍና ክርክሮችን ታስነሳለች። አንደኛው «Argument from design» የዲዛይን ንድፈ-ሃሳብ ክርክር፤ ሁለተኛው «Cosmological argument» ቅድመ መነሻዊ የህልውና ክርክር፤ እና ሦስተኛው «Inference to the best explanation» ካገኘናቸው ማስረጃዎች በመነሳት ጠለቅ ያለ ማብራርያ መስጠት።

ለምሳሌ ግመሉን ባናየውም ዱካውን ብናየው ከዛ በመነሳት ግመሉ በበረዓ ማለፉን እንደአንድ ማስረጃ መያዝ ሲሆን፤ የፈጣሪ መኖር ማረጋገጫ የፍጥረቶች መኖር ማስረጃ ይሆኑናል። ፍጡር ወይም ፍጥረታት በአንድ አካልና በአንድ ፈጣሪ ካልተፈጠሩ ካለመኖር ወደመኖር ሊመጡ አይቻለውም። ያለግመል የግመል ዱካ በምድር አይኖርም እንደማለት ያለ ነው። ያን በማመን የግመሉን ድካ ተከትለን አርባም ሠላሳም እርምጃ ብንራመድ ግመሉ ጋር መድረሳችን አይቀሬ ነው። ነገር ግን እስከዛሬ ድረስ ወደግመሉ እንዳንደርስ ያደረገን የግመሉ አለመኖር ሳይሆን ብዙ የግመል ዱካ በሰሜን፣  በደቡብ፣ በምዕራብ እና በምስራቅ በአራቱም አቅጣጫ በበረዓ ላይ አርፎ ግራ ስላጋባን ነው። በተሳሳቱ የግመል ዱካዎች ተመርቶ የሄደ ሰው ደግሞ መጨረሻው ላይ የሚጠብቀው ሌላ አውሬ ነው!።



@Armemo_offical
👁 1.3 тыс. 👏 16❤ 4👍 2 💬 2 ↻ 8 12 ноября