ኅዳር 5 2019
በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት በተጨማሪ ለህክምና በሚወስደው ጊዜና ወጪ ብዙዎች ይፈተናሉ።
በተለይም በህክምና ተቋማት አለመስፋፋት ምክንያት ከክልሎች የሚመጡት ታካሚዎች የማረፊያ ቦታ ማግኘት እና ሌሎችም ተደራራቢ ችግሮች ይገጥሟቸዋል፡፡
ይህንን ችግር ለማቃለል አለም ፍሬ ፒንክ ሀውስ የካንሰር ፋውንዴሽን ከተለያዩ ክልሎች ለጡት እና ለማህፀን ጫፍ ካንሰር ህክምና ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሴት ታካሚዎችን እያገዝኩ ነው ብሏል፡፡
ፋውንዴሽኑ ይህንን የሚያግዝና በካንሰር ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የእግር ጉዞ ማሰናዳቱንም ሰምተናል፡፡
ነገር ግን ካለው የችግሩ ስፋት አንጻር አሁንም በርካታ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡
በጡት ካንሰር ምክንያት ያጧት እህታቸውን ለማስታወስ ፋውንዴሽኑን መመስረታቸውን የሚናገሩት የአለም ፍሬ ፒንክ ሀውስ ካንሰር ፋውዴሽን መስራችና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ፍሬይወት ደርሶ ከካንሰር ህክምና ጋር በተያያዘ በተለይ ከክልሎች የሚመጡት ታካሚዎች ብዙ ችግር ይገጥማቸዋል ብለዋል፡፡
ፋውንዴሽኑ በአዲስ አበባ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም በጎንደር በተመሳሳይ ለታካሚዎች የማረፊያ፤ የምግብና ትራንስፖርት ድጋፍ ያደርጋልም ይላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ለካንሰር ህመም የቅድመ ምርመራ ላይ በብዙ ያልተሰራበት መሆኑ ችግሩን እያባባሰው መጥቷል የሚሉት ዶክተር ፍሬህይወት አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ካንሰሩ ለህክምና አስቸጋሪ ከሆነ በኋላ ወደ ህክምና እንደሚመጡና ይህም ከፍተኛ ችግር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለካንስር ህክምና ከክልሎች የሚመጡ ሴቶችን ለማገዝ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ደግሞ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ለማበረታታት በየአመቱ ፋውንዴሽኑ የእግር ጉዞ እንደሚያዘጋጅ እና በዚህ አመትም ነገ ህዳር 6 ቀን 2019 ዓ.ም ተመሳሳይ ፕሮግራም እንደተሰናዳ ተነግሯል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች የጡት ካንሰር ቀዳሚው ሲሆን ቅድመ ምርመራ ማድረግ እንዲሁም እንደ ጨረር ህክምና ያሉ አገልግሎቶች አለመስፋፋት ደግሞ ችግሩን እያባባሰው ነው ተብሏል፡፡
አለም ፍሬ ፒንክ ሀውስ ካንሰር ፋውንዴሽን እስካሁን ከ5 ሺህ 7 መቶ በላይ ለሚሆኑ የካንሰር ታካሚዎች ከአንድ አስታማሚ ጋር የመጠለያ የምግብና ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ዘገባውን ያድምጡ....
https://short.do/R2_famምህረት ስዩም