Телеграм

Ethio Fm 107.8

@ethiofm107dot8 Общие новости и СМИ
РКН: проверяем Иноагент: проверяем
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Статистика обновлена 15.11.2026 в 05:29 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики18 432
Охват поста1 614 9% от подписчиков
ERR за месяц8,76%
ERR за 24 часа5,95%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Ethio Fm 107.8 tg18 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዳኞች በአፍጋኒስታን ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ላይ ቀደም ሲል ተከፍቶ የነበረውን የመጀመሪያውን የምርመራ መዝገብ በይፋ እንዲዘጋ ወሰኑ

የአናዶሉ የዜና ወኪል የፍርድ ቤቱን ሰነድ ጠቅሶ እንደዘገበው፥እንዲዘጋ የታዘዘው ይህ መዝገብ የአሜሪካ ወታደሮች ፈጽመዋቸዋል የተባሉ ወንጀሎችን ጨምሮ፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2016 ወዲህ በእስላማዊ መንግሥት የኾራሳን ክንፍ ወይም በአይ.ኤስ.አይ.ኤስ-ኬ ላይ ተከፍቶ የነበረውን ምርመራም የሚያካትት ነበር።

የፍርድ ቤቱ ዳኞች ለውሳኔያቸው በምክንያትነት ያቀረቡትየዓቃቤ ሕግ ቢሮ በዚህ የመጀመሪያ መዝገብ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ወይም የክስ ሂደቶችን በውጤታማነት ማከናወን እንደሚችል ማሳየት አለመቻሉን ነው።

በመሆኑም የሕግ ግልጽነትን እና የተገቢውን የዳኝነት ሥርዓት አስተዳደር ለማስጠበቅ ሲባል የፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት የመጀመሪያውን መዝገብ እንዲዘጋ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል የውጭ ኃይሎች ከአፍጋኒስታን መውጣታቸውን ተከትሎ ታሊባን ወደ ሥልጣን ከተመለሰበት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከኦገስት 2021 ወዲህ ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ላይ የተከፈተው የተናጠል ምርመራ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ይህ የቀጠለው ምርመራ በዋናነት ታሊባን በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ፈጽሟቸዋል በተባሉ ወንጀሎች፣ እንዲሁም በፖለቲካዊ፣ በብሔርና በሃይማኖታዊ ምክንያቶች በሚፈጸሙ ስደቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን፥በአራት የታሊባን አመራሮች ላይ የወጡት የእስር ማዘዣዎችም እንደጸኑ ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤የፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ ዳኞቹ የመጀመሪያውን ምርመራ ለመዝጋት በሰጡት ውሳኔ ላይ ይግባኝ ማለቱን ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ልዑል ወልዴ

ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም
👁 982 ↻ 2 вчера в 08:32
Ethio Fm 107.8 tg18 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን የአፍሪካ ንግድ ውህደት ጉባኤን  ለማስተናገድ የትብብር ስምምነት ተፈራረመች

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በመስከረም 2027 የሚካሄደውን አህጉራዊ የአፍሪካ ንግድ ውህደት ጉባኤ (Africa Commerce Convergence Summit - ACCS) በአዲስ አበባ ለማስተናገድ የሚያስችላትን የትብብር ስምምነት ተፈራርማለች።

የኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ባለሙያዎች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ አይሲቲ ማኅበር እና የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስና አቅርቦት ሰንሰለት ባለሙያዎች ማኅበር ከአፍሪካውያን አቻ ኮንፌዴሬሽኖች ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መድረክ ለጉባኤው ስኬታማነት የሚደረገው ዝግጅት በይፋ ተበስሯል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የጉባኤው መሥራች ናይጀል ታተርሶል፣ የኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ፋና አባይ እና የኢትዮጵያ አይሲቲ ማኅበር ፕሬዚዳንት ይልቃል አባተ የትብብር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ ወቅት የተገኙት የአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር ማቶንጎ ማታምዋንዲ፣ የታይኮን አፍሪካ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ጎው እና የአፍሪካ አቅርቦት ሰንሰለት ኮንፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ጆን ካራኒ ባደረጉት ንግግር፥አፍሪካ ከውጭ ሀገራት ጥገኝነት ተላቃ የራሷን ብራንዶች፣ የሙያ ማረጋገጫዎች እና ድንበር ተሻጋሪ የንግድና የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን መገንባት እንዳለባት አሳስበዋል።

የጉባኤው ጠንሳሽ ናይጀል ታተርሶል እና የታይኮን አፍሪካ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ጎው ባለፉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ፥የከተማዋን ፈጣን ልማት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የአፍሪካ ኅብረትን እንዲሁም የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እና የኢትስዊች የክፍያ ሥርዓቶችን መመልከታቸውን ገልጸው፥ኢትዮጵያ እስካሁን ከተካሄዱት ሁሉ የተሻለውን ጉባኤ እንደምታስተናግድ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

ይህ ጉባኤ የማርኬቲንግ፣ የአይሲቲ እና የአቅርቦት ሰንሰለት ዘርፎችን ከማገናኘት ባለፈ፤ በአዲስ አበባ በሚካሄደው መድረክ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አራተኛውን የአፍሪካ የፈጠራ ኢኮኖሚ (Creative Economy) ዘርፍን በይፋ እንደሚያስጀምር ተገልጿል።

ከ33 እስከ 40 ከሚደርሱ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከአንድ ሺህ በላይ ባለሙያዎች፣ የንግድ መሪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ጉባኤ፥ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስሩን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸው፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዝግጅቱ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ልዑል ወልዴ

ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም
👁 913 ↻ 3 вчера в 08:26
Ethio Fm 107.8 tg18 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
21ኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ከ50 በላይ ፊልሞችን በማሳየት ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ከአዲስ አበባ ቴአትርና ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው 21ኛው የፊልም ፌስቲቫል ከኅዳር 6 እስከ ኅዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ  የፌቲቫሉ መስራችና  አዘጋጅ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ  ተናግረዋል።

ፌስቲቫሉ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት  በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ እዚህ የደረሰ ሲሆን፥በዘንድሮው መርሃ ግብርም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ፊልሞች ለእይታ የሚበቁበት፣ የልምድ ልውውጦች የሚካሄዱበትና ምርጥ የፊልም ባለሙያዎች የሚሸለሙበት መድረክ እንደሚሆን ተገልጿል።

በፌስቲቫሉ የሳምንት ቆይታ ከ50 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ፊልሞች በተመረጡ ዘመናዊ የሲኒማ አዳራሾች ለእይታ ይቀርባሉ ተብሏል።

የፊልም አፍቃሪው ህብረተሰብ ያለ አንዳች የዋጋ ጫና ፊልሞችን እንዲመለከት ታስቦም «በ50 ብር 50 ፊልሞች» በሚል መሪ ቃል በቴሌብር በኩል ትኬት በመቁረጥ ሳምንቱን ሙሉ ፊልሞችን መታደም የሚያስችል ልዩ ዕድል መመቻቸቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም በዘመኑ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆኑ የቲክቶክና የዩቲዩብ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት በሞባይል ስልክ ብቻ የተቀረጹ አጫጭር ፊልሞች የሚወዳደሩበት አዲስ ዘርፍ መካተቱ ይፋ ተደርጓል።

የዘንድሮው ፌስቲቫል ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለውን ትስስር ያጠናከረ ሲሆን፥በተለይም «የራሺያ ቀናት» በሚል የራሺያ ፊልሞች የሚታዩበትና ከሀገሪቱ የመጡ ባለሙያዎች በፓናል ውይይት የሚሳተፉበት መድረክ ተዘጋጅቷል።

ከዚህም ባሻገር ከሻንጋይ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫልና ከካናዳ የፊልም ተቋማት ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት፥በፌስቲቫሉ ተወዳድረው አሸናፊ የሆኑ የኢትዮጵያ ፊልሞች ወደ ቻይና፣ ራሺያና ካናዳ በመጓዝ ለእይታና ለውድድር የሚቀርቡበት ዕድል መፈጠሩ ተመላክቷል።

በሳምንቱ የቆይታ ጊዜ ከፊልም ማሳየት በተጨማሪ ሙያዊ አቅምን የሚገነቡ ወርክሾፖች እና የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።

በፌስቲቫሉ የማጠቃለያ ቀን በ12 የተለያዩ የዘርፍ መስፈርቶች አሸናፊ ለሆኑ የኢትዮጵያ ፊልም ባለሙያዎች የዕውቅናና የዋንጫ ሽልማት እንደሚያበረክት ተጠቁሟል።

አቶ ይርጋሸዋ  አክለውም ፌስቲቫሉ ያለፉትን 21 ዓመታት በግል ጥረትና በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ አልፎ እዚህ መድረሱን አስታውሰው፣ አሁን ላይ የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር የፈጠረላቸው አጋርነት ትልቅ እፎይታ እንደሰጣቸው ገልጸዋል።

በመክፈቻውና በመዝጊያው ዕለት የሚካሄደው ሥነ-ሥርዓት መግቢያው ነፃ መሆኑን በመግለጽ፣ የጥበብ ቤተሰቦችና የሚዲያ አካላት በጋራ በመገኘት ለኢንዱስትሪው ዕድገት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም
👁 1.2 тыс. ↻ 8 13 ноября