Телеграм

Commercial Bank of Ethiopia - Official

@combankethofficial Финансы и инвестиции
РКН: проверяем Не иноагент
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Статистика обновлена 14.11.2026 в 21:15 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики220 220
Охват поста16 155 7% от подписчиков
ERR за месяц7,34%
ERR за 24 часа5,54%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Commercial Bank of Ethiopia - Official tg220 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ፈጠራ ሲደገፍ፣ ሀገር ወደላቀ ምእራፍ!

*********
ፈጠራ ሀሳብን ወደ መፍትሔ ይቀይራል፤
መፍትሔ ወደ ንግድ ይለወጣል፤
ንግድ ደግሞ የሥራ ዕድልን ይፈጥራል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈጠራን መደገፍ የግለሰብን ሀሳብ መደገፍ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገርን የኢኮኖሚ ዕድገት መደገፍ፣ ለዜጎች የሥራ እድልን መፍጠር በአጠቃላይ የሀገራችንን እድገት ማፋጠን መሆኑን በእጅጉ ያምናል።

ለዚህም ነው ባንካችን ፈጠራን ለማበረታታት እና የሥራ ፈጣሪዎችን ለማብቃት የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኘው።

"ፈጠራን ዛሬ እንደግፍ፤ የነገን ኢትዮጵያ ዛሬ እንገንባ" በሚል ሀሳብም ባንካችን የኢቢሲ ዋና አጋር በመሆን "ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

5ኛው ዙር ውድድር ነገ ህዳር 6 ቀን 2019 ዓ.ም አሸናፊዎቹን በመለየት ፍፃሜውን ያገኛል።

የፍጻሜውን ውድድር የተመለከቱ ልዩ ዘገባዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን የምናደርሳችሁ በመሆኑ እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

“ፈጠራ ሲደገፍ፣ ሀገር ወደላቀ ምዕራፍ” የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !

#CBE #Nagadras #Entrepreneurship #Innovation #DigitalTransformation #ነጋድራስ
👁 3.6 тыс. 👏 8👍 3 💬 2 вчера в 16:01
Commercial Bank of Ethiopia - Official tg220 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ታላቅ ሀሳብ የታላቅ ሀገር መሠረት ነው!!
*********


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታሪክ በአጭሩ ሀገር ማሳደግ፣ ሀገር መገንባት፣ ለወገን መድረስ ነው።
  
ባንካችን ከ84 ዓመታት በላይ የተለያዩ የልማት ዘርፎችን የፋይናንስ ፍላጎት በማሟላት ለኢትዮጵያ እድገት የማይተካ ሚና ተጫውቷል።

ዛሬ ደግሞ የዓለም ኢኮኖሚ በፈጠራና በዲጂታል ቴክኖሎጂ በሚመራበት ዘመን፣ ባንካችን ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን በማስፋፋት፣ የደንበኞችን የባንክ ልምድ በማዘመን እና የፋይናንስ ተደራሽነትን በማሳደግ ለአዲሱ የኢኮኖሚ ምዕራፍ መሠረት እየጣለ ይገኛል።

ባንካችን ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የሚያቀርበው የ"ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር" የዚህ ተልዕኮው አንዱ መገለጫ ነው።

ባንካችን የንግድ ሥራ የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ተግባራዊ የንግድ ሥራ ለመቀየር፣ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት እና አዳዲስ የኢኮኖሚ አቅም ለማፍራት የሚያግዝ መድረክ የመፍጠርን አስፈላጊነት በመገንዘብ የነገዋን ኢትዮጵያ በዛሬው የፈጠራ ሀሳብ እየገነባ ይገኛል።

ፈጠራን ደግፈን ሀገርን እንገነባለን!

******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !

#CBE #Nagadras #Entrepreneurship #Innovation #DigitalTransformation
👁 6.2 тыс. 👍 10❤ 9 💬 3 вчера в 12:06
Commercial Bank of Ethiopia - Official tg220 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የፋይናንስ ተደራሽነትን ማሳደግ ለግብርናው እድገት!
************
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሥራ ግንኙነታቸውን ለማጠናከርና ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል።
 
ውይይቱ በተቋማቱ መካከል ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በመፍጠርና በጋራ በመሥራት የግብርና ፋይናንስን ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም አርሶ አደሮችና ሌሎች ተጠቃሚዎች የግብርና ግብዓት አቅርቦትና የተቀናጀ የሜካናይዜሽን አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት የሚያስችላቸውን አማራጮች ማስፋት ላይ ያተኮረ ነው።
 
በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለግብርናው ዘርፍ ቅድሚያ በመስጠት ፋይናንስ እያቀረበ መሆኑ ተገልጿል።
 
በተለይም ባንካችን ከስትራቴጂክ የግብርና ግብዓቶች መካከል አንዱ ለሆነው የአፈር ማዳበሪያ ግዥ የውጭ ምንዛሬ በማቅረብ ለግብርናው ዘርፍ ዕድገት ወሳኝ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተብራርቷል።
 
ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን በማጠናከርና በተቀናጀ መንገድ በመሥራት ለሀገራዊ ዕድገት የሚኖራቸውን አስተዋፅኦ ለማሳደግ ተስማምተዋል።
 
በውይይቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆል ሴል ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር እስክንድር አስፋው እና የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ እና ሌሎች የተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
👁 4.8 тыс. ❤ 13👏 3😁 1 💬 2 вчера в 10:35