Телеграм

Amen Institute of Technology Official®

@amenelectricaltechnology Высшее образование и курсы
РКН: проверяем Не иноагент
✅We provide professional #training with Job creation supported by workshop and on-site training which is unique in its kind.
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
📱0991156969
📱0939555510

Статистика обновлена 15.11.2026 в 10:48 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики23 014
Охват поста3 055 13% от подписчиков
ERR за месяц13,27%
ERR за 24 часа4,80%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Amen Institute of Technology Official® tg23 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
✅#የቅጥር_ማስታወቂያ
===

↪️ዛሬም አንድ የቅጥር ደብዳቤ ለድርጅታችን ደርሶታል። ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ እና በዚህ ዘርፍ መስራት የምትፈልጉ ተከታዮቻችን/ሰልጣኞቻችን ማስታወቂያው ላይ የተገለጸው ቦታ በአካል በመሄድ ወይም ማስታወቂያው በተቀመጠው ቴሌግራም ወይም ኢ-ሜል ድርፍጅቱ በቀጥታ መላክ ትችላላችሁ❗️

👉ድርጅታችን ለዚህ ማስታወቂያ ምንም አይነት ክፍያ አልተቀበለም❗️አይቀበልም❗️

Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL

#አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት
👁 858 ❤ 3🔥 2 ↻ 2 вчера в 14:08
Amen Institute of Technology Official® tg23 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
✅ ነገ ቅዳሜ ህዳር 05/2019 ዓ.ም ተመዝግበው መጀመር የሚጭሏቸው 4 የተመረጡ የተግባር ስልጠናዎች፦
=======
👉አንተ ነገ ነገ እያልክ  ቀድመው የወሰኑት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሥራ እድል እየፈጠሩ ነው❗️ እነዚህ ስልጠናዎች የሚሰጡት ቅዳሜ ከ8-11 ሰዓት እና እሁድ ከ3-6 ሰዓት ነው❗️
1️⃣ አድቫንስድ የቤት ዕቃዎች ጥገና(ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ስማርት ቲቪ፣ እና የኤሌክትሪክ ምድጃ/ኦቨን ጥገና)
2️⃣ አድቫንስድ የደህንነት ሲስተም ዝርጋታ (CCTV ካሜራ፣ ፋየር አላርም፣ አክሰስ ኮንትሮል፣ የኤሌክትሪክ አጥር፣ ታይም አቴንዳንስ፣ ቪዲዮ ኢንተርኮም ወዘተ...)
3️⃣ አድቫንስድ የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች ጥገና (የጀነሬተር ጥገና፣ ሞተር ኮንትሮል ሲስተምና ኤሌክትሪካል ሞተር ሪዋይንዲንግ)
4️⃣ አድቫንስድ አውቶካድ  ኤሌክትሪካል ዲዛይን
✅ አድራሻ፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
📞 ፈጣን የመረጃና የምዝገባ ስልክ ቁጥሮች፦
👉 0991 15 69 69
👉 0939 55 55 10
🔗 ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
❌ወጣትነት በክህሎት ካልታጀበ፣ እርጅና በቁጭት ያልፋል❗️
👁 980 ❤ 8 💬 1 ↻ 3 13 ноября
Amen Institute of Technology Official® tg23 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
✅#ትራንስፎርመር_ምንድን_ነው❓
What is Transformer ❓
======
1️⃣. #መሰረታዊ_አሰራር (Working Principle)
👉ትራንስፎርመር (The Transformer)
1️⃣. #መሰረታዊ_አሰራሩ (Working Principle)
👉ትራንስፎርመር የኤሌክትሪክ ኃይልን ከአንድ ሰርክዩት ወደ ሌላኛው ያለ ምንም አካላዊ ግንኙነት (Static Device) የሚያስተላልፍ መሣሪያ ነው❗️
👉ትራንስፎርመር የሚሰራው #በፋራዴይ_የኢንዳክሽን ህግ ነው❗️
👉በመጀመሪያው ጥቅል ሽቦ (Primary Winding) ውስጥ የሚያልፈው የኤሲ (AC) ጅረት መግነጢሳዊ ፍሰት (Magnetic Flux) ይፈጥራል፤ ይህ ፍሰት ደግሞ በሁለተኛው ጥቅል ሽቦ (Secondary Winding) ላይ ቮልቴጅ ይፈጥራል❗️
👉ትራንስፎርመር የሚሰራው በ AC ብቻ ነው፤ በ DC አይሰራም❗️
2️⃣. የትራንስፎርመር አይነቶች (Types of Transformers)
እንደ ተግባራቸው በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡
🔘 Step-up Transformer: ቮልቴጁን ከፍ የሚያደርግ (ለምሳሌ ከማመንጫ ጣቢያ ወደ ማስተላለፊያ መስመር ሲላክ)።
🔘 Step-down Transformer: ቮልቴጁን የሚቀንስ (ለምሳሌ ከመንገድ ዳር ካለው መስመር ወደ 220V/380V ዝቅ አድርጎ ለቤት ሲሰጥ)።
እንደ ማቀዝቀዣ ስርአታቸው ደግሞ፦
🔘 Oil-Immersed: በዘይት የሚቀዘቅዙ (አብዛኛው የውጪ ትራንስፎርመሮች)።
🔘 Dry Type: በነፋስ የሚቀዘቅዙ (አብዛኛውን ጊዜ በህንፃዎች ውስጥ ለደህንነት ሲባል የሚገጠሙ)።
3. #ዋና_ዋና_ክፍሎች (Main Components)
#ኮር (Core):
👉መግነጢሳዊ ፍሰቱ የሚያልፍበት ከላሚኔትድ ብረት የተሰራ ክፍል።
#ዊንዲንግ (Windings):
👉ከመዳብ ወይም ከአሉሙኒየም የተሰሩ ጥቅል ሽቦዎች።
#ቡሺንግ (Bushings):
👉የከፍተኛ ቮልቴጅ ገመዶች ወደ ትራንስፎርመሩ የሚገቡበት የሴራሚክ መከላከያ።
#ታፕ_ቼንጀር (Tap Changer):
👉ቮልቴጁን (Output Voltage) በትንሹ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ የሚያገለግል መቆጣጠሪያ።
4⃣. #ጥገና_እና_ደህንነት (Maintenance and Safety)
👉አንድ ትራንስፎርመር ለ 30 እና 40 ዓመታት እንዲያገለግል እነዚህን ነገሮች ተከታተል፡
🔘#የዘይት_ደረጃ (Oil Level and Quality):
👉በትራንስፎርመር ውስጥ ያለው ዘይት ለማቀዝቀዝ እና ለኢንሱሌሽን ያገለግላል።
👉ዘይቱ ከቆሸሸ ወይም እርጥበት ከገባ ትራንስፎርመሩ ሊፈነዳ ይችላል።
🔘#የቡክሆልዝ_ሪሌይ (Buchholz Relay):
👉በትራንስፎርመሩ ውስጥ የጋዝ መፈጠር ወይም የዘይት መፍሰስ ሲኖር ወዲያውኑ መብራት የሚያጠፋ የደህንነት መሣሪያ ነው።
🔘 #የሙቀት_መጠን (Temperature)
👉ከፍተኛ ሙቀት የኢንሱሌሽን ዕድሜን ያሳጥረዋል።
5⃣. #ትራንስፎርመር_ሬቲንግ (Rating)
ትራንስፎርመር የሚለካው በ kVA (Kilo-Volt-Ampere) እንጂ በ kW አይደለም። ይህ የሆነበት ምክንያት በትራንስፎርመሩ ላይ የሚፈጠረው ሙቀት በቮልቴጅ እና በከረንት (Current) ላይ እንጂ በፓወር ፋክተር (Power Factor) ላይ ስላልተመሰረተ ነው።
👉ትራንስፎርመር ሲጮህ (Humming sound) ከሰማህ የኮር ላሚኔሽኑ መላላቱን ወይም ኦቨርሎድ መሆኑን ያሳያል።
👉ሁልጊዜ ትራንስፎርመር አካባቢ ስትቆም ጆሮህን ከሌላው ጊዜ በተለየ ተጠቀም❗️
6⃣.ትራንስፎርመር_ምርመራ( TransformerTesting)
👉በትራንስፎርመር ስራ ላይ ምርመራ (Testing) ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው።
👉ትራንስፎርመር ውድ እና ለሲስተሙ ቁልፍ መሣሪያ ስለሆነ፣ ሳይመረመር ኃይል ከተሰጠው ከፍተኛ አደጋ ሊያደርስ ይችላል።
👉በስራ ላይ የምንጠቀምባቸውን ዋና ዋና የአለካክ/የምርመራ ዘዴዎች እናያለን፦
🔷. #የኢንሱሌሽን_ምርመራ (Insulation Resistance Test - Megger)
👉ይህ ምርመራ በትራንስፎርመሩ ሽቦዎች (Windings) እና በብረት አካሉ (Body) መካከል ያለው መከላከያ ጠንካራ መሆኑን ለማረጋገጥ ይደረጋል።
👉 ለመለካት የምንጠቀምርው መሣሪያ ሜገር ነው።
👉የምንለካበት መንገድ ደግሞ በ Primary እና Body፣ በ Secondary እና Body፣ እንዲሁም በ Primary እና Secondary መካከል ያለውን የመከላከል አቅም (በ Mega-Ohms) እንለካለን።
👉ውጤቱ በጣም ዝቅተኛ ከሆነ (ለምሳሌ ከ 100MΩ በታች ከሆነ) በትራንስፎርመሩ ውስጥ #እርጥበት ወይም #ብልሽት መኖሩን ያሳያል።
🔹. #የቮልቴጅ_ሬሺዮ_ምርመራ (Voltage Ratio Test)
👉ትራንስፎርመሩ በትክክል ቮልቴጁን መቀነሱን ወይም መጨመሩን ለማረጋገጥ ይደረጋል።
👉 በ Primary በኩል የታወቀ ዝቅተኛ ቮልቴጅ (ለምሳሌ 400V) ሰጥተን በ Secondary በኩል የሚወጣውን ቮልቴጅ እንለካለን።
🔹. #የሽቦዎች_መቋቋም_ምርመራ (Winding Resistance Test)
👉ይህ ምርመራ በሽቦዎቹ መጋጠሚያዎች ላይ መላላት (Loose connection) ወይም መቆረጥ መኖሩን ለማወቅ ይረዳል።
👉በዝቅተኛ የዲሲ (DC) ከረንት በመጠቀም የእያንዳንዱን ሽቦ የመቋቋም አቅም (Resistance) በ Ohms እንለካለን።
👉ውጤቱን ከአምራቹ ዳታሺት (Nameplate) ጋር መወዳደር አለበት።
🔹. #የዘይት_ምርመራ (Transformer Oil Dielectric Test)
👉ለዘይት ትራንስፎርመሮች ብቻ የሚደረግ ሲሆን፣ ዘይቱ ኤሌክትሪክ የመከላከል አቅሙን (Dielectric strength) አለማጣቱን ለማወቅ ይደረጋል።
👉የዘይት ናሙና ወስደን በሁለት ኤሌክትሮዶች መካከል ቮልቴጅ በመጨመር ዘይቱ እስከ ስንት ኪሎ ቮልት (kV) መሸከም እንደሚችል (Breakdown Voltage - BDV) እንለካለን።
👉ጥሩ ዘይት: ቢያንስ ከ 30kV እስከ 40kV በላይ መሸከም አለበት።
🔹. #ሌሎች_ጥቃቅን_ምርመራዎች
👉 Polarity Test: የሽቦዎቹ አቅጣጫ (Phase) ትክክል መሆኑን ማረጋገጫ።
👉Continuity Test: ሽቦዎቹ ውስጥ መቆረጥ አለመኖሩን በቀላሉ በኦም ሜትር ማረጋገጥ።
#ማስጠንቀቂያ❌
👉ምንም አይነት ምርመራ ከመጀመራችሁ በፊት ትራንስፎርመሩ ከኃይል መስመር (Power Source) መላቀቁን እና የተጠራቀመ ኃይል (Static charge) ካለ 'Ground' ተደርጎ መፈሰሱን አረጋግጡ።
መልካም የሥራ ጊዜ ከተማሩበት ለሌሎች #ሼር ማድረግ እንዳይረሹ❗️

✅ የተመረጡ ስልጠናዎች በተግባር ስልጥነው አንቱ የተባሉ ባለሙያ መሆንና በቀጥታ ሥራ መጀመር ከፈለጉ ፈጥነው ይመዝገቡ❗️
👉 በአሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተግባር ስልጠና በርካቶች በተግባር ስልጠንነው በቀጥታ ወደ ሥራ ቅጥር ገብተዋል❗️በርካቶች የራሳቸውን ሥራ ጀምረው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሥራ እየፈጠሩ ነው ❗️
❗️ጊዜ ሳያባክኑ ዛሬውኑ ይቀላቀሉን❗️
✅አድራሻ፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
📞ይደውሉ❗️
👉 0991 15 69 69
👉 0939 55 55 10
🔗 ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
❌ወጣትነት በክህሎት ካልታጀበ፣ እርጅና በቁጭት ያልፋል❗️
👁 1.2 тыс. ❤ 6🔥 2👏 2 ↻ 6 13 ноября