Телеграм

መጽሐፍቶችን በpdf📚

@pdfffb Литература и писательство
РКН: проверяем Не иноагент
"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome!
በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ!
፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ!
፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።

Статистика обновлена 15.11.2026 в 13:30 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики18 552
Охват поста3 601 19% от подписчиков
ERR за месяц19,41%
ERR за 24 часа4,06%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
መጽሐፍቶችን በpdf📚 tg18 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ያመሻሽ ስንኞች


በቀዝቃዛ ጎጆ፤ በደብዛዛ ኩራዝ
እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤
ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ
ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤

“””””
እሳቴን አንድጄ
ጭራሮ ማግጄ
ሰታቴየን ጥጄ
ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ
እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤

© በእውቀቱ ስዩም

ሁሌም ማንበብ📖✨
👁 883 👌 13👏 4❤ 2 ↻ 4 вчера в 10:00
መጽሐፍቶችን በpdf📚 tg18 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ውድ አንባብያን!

ደስ ያሰኘንን ዜና ልናበስራችሁ ነው።  እንደምታውቁት በሕይወት ካጣናቸው እምር ደራስያን መሐል አንዱ አቤ ጉበኛ ነው። አቤ ይበልጥ በ"አልወለድም"፣ በ"አንድ ለእናቱ" ልቦለድ ሥራዎቹ፣  በ"እሬትና ማር" እና "መስኮት" የግጥም ስብስቦቹ፣ በ"ፖለቲካና ፖለቲከኞቹ" እና "የሮም አወዳደቅ" ተውኔቶቹ እና በሌሎችም ድርሰቶቹ የምናውቀው ደራሲ ነው።

ይሄ የታወቀ ነው። የማይታወቀው በቅርቡ ከማሻ አስተዳደር ጋር በመተባበር በዚህች ከተማ በአቤ ጉበኛ "አልወለድም" ስም ቤተመጻሕፍት ልንከፍት መሆኑን ነው። ይህንን ቦታ የመረጥነው አቤ ጉበኛ ለግዞት ከርሞበት ስለነበረ  መታሰቢያ ይሆነው ዘንድ ነው። አቤ በ"አልወለድም"ና በሌሎች መጽሐፎቹ የዘውዱን ስርአት ክፉኛ ይተች ስለነበረ ወደ ኢሉባቡር ሞቻ አውራጃ ለሁለት አመታት በግዞት  ተልኮ ነበረ። ቦታው ለስርአቱ ፈታኝ የነበሩ እምቢ ባዮች መቅጫና መቀጣጫ እንዲሆናቸው የሚላኩበት ስፍራ ነበር።

አቤ የተወለደው ምእራብ ጎጃም፣ አቸፈር ወረዳ ነው። ያረፈውም የካቲት 1ቀን 1972 ዓ.ም ነው። (አወዛጋቢ ስለነበረው ሕይወቱና አሟሟቱ ሌላ ቀን እናወጋለን)

ይህንን ዜና እና እነዚህን መረጃዎች ለምንድነው የምንነግራችሁ?

አንድም ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ከወርሃ የካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ንባብና አንባቢን ለማወዳጀት የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነውና፣ በመጻሕፍት ባንኩ አማካይነት ከሃምሳ ሺህ(50,000) በላይ የሆኑ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መጻሕፍት ያለአንዳች ክፍያ የማዳረስ ጥረቱን እየቀጠለ መሆኑን አሁንም ለማስገንዘብ፣

አንድም ይህንን እያደረግን ያለነው ደጋግ አፍቃሬ መጻሕፍት ግለሰቦች በዙርያችን አሉና እነሱ በነፃ በልግስና  ባይሰጡን ኖሮ፣ ለዚህ ለተቀደሰ እቅድ አንበቃ እንደነበረ ለማስመዝገብ፣

አንድም በአቤ ጉበኛ "አልወለድም" ስም በማሻ አስተዳደር ቤተ ንባብ ስንከፍት፣ አንዳንድ ሰዎች "---ቀደም ብዬ ባውቅ ኖሮ እኔ ለአካባቢው ያለኝን ክብር፣ ወይም ለደራሲውና ለጉዳዩ ያለኝን ፍቅር ለመግለፅ ያነበብኳቸውን መጻሕፍት ወይም ለቤተ ንባቡ የሚጠቅሙ ቁሳቁሶች መለገስ የምችለውን?---" የሚል ቁጭትና ቅሬታ እንዳይሰማቸው ከወዲሁ ለማነሳሳት ነው።

የማሻ ከተማ አስተዳደር ለቤተ ንባብ ምቹ የሆነ ቦታ ባያዘጋጅልን ኖሮ፣ የአካባቢው ተወላጅ የሆነው በጎ አድራጊው ወጣቱ ሳሙኤል መኳንንት ባያግዘን ኖሮ ይህንን ሁሉ ባላቀድን! እናም አመስግኑልን!

ለበለጠ መረጃ:- 0900651010 (ኮከብ ጌታቸው)
0910009757. (ሳሙኤል መኳንንት). ብላችሁ ደውሉ።

© ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ

ሁሌም ማንበብ✨📖
👁 1.8 тыс. 👍 4❤ 2 ↻ 1 12 ноября