ተስፋ በኢየሱስ
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ 👉 @Tes_b37
Статистика обновлена 15.11.2026 в 11:37 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?
Динамика за 30 дней
Истории пока нет. График появится после следующих обновлений статистики.
Рекламные публикации
Последние публикации
Все посты канала →በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና አምድ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ፡፡
📖ዘፀአት 13÷21📖
መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የእግዚአብሔር እሳት እንዴት በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮቻችን እንደሚሠራ በተለያዩ የመጽሐፍ ክፍሎች ይዘረዝራል፡፡ የተሻለውን የእግዚአብሔርን ነገር ብንፈልግ የእግዚአብሔርን በእሳት የማጥራት ሕይወት ለመኖር ፈቃደኛ መሆን አለብን፡፡ በውስጣችን ወርቅ (ጥሩ የሆነ ነገር) በውስጥ ሕይወታችን አለን፡፡ ነገር ግን ያልተጣሩና ሊወገዱ የሚገቡ ነገሮችም አብሮ አሉን፡፡
እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር መልካምነት መደሰት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ በእሳቱ በተከታታይ ለመሠራት ጉጉት አለው፡፡ የእግዚአብሔር እሳት በሕይወትህ ሲመጣ ለውጥን የሚያመጣ ነበልባል እንደሆነ ሁልጊዜ አስታውስ እሳቱ ከሕይወታችን ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ አያደርግም፡፡
እንዲሁም ደግሞ እሳቱ እንዲያጠፋንም አያደርግም እርሱ ከምንችለው በላይ እሳቱ እንዲያይልብንም አያደርግም፡፡
በሕይወታችን ሁሌ አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ የሚመስሉና ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀላል የሚመስሉ ገጠመኞች ይፈራረቁብናል፡፡ ጳውሎስ ይህንን ጊዜያት ሲገልጽ በሁሉም እራሱን ለማስለመድና ከሁለቱ በአንዱ ለመደሰት የምችልበት እንደተማረ ይናገራል፡፡
የእግዚአብሔር ጥበብ ፍጹም እንደሆነና ሁሉን ነገር ለመልካም እንደሚሆን ተምሮአል፡፡
እኛም ልክ እንደ እርሱ ምርጫችንን ማድረግ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔርን እሳት መቋቋማችን በእኛ ሕይወት እንዳይነድ ከማድረግ መከልከል አንችልም፡፡ እሳቱ እንዲጠፋ ከመቃወም ይልቅ እሳቱ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ከተረዳን በሕይወታችን አይሎ ስራውን ሰርቶ እንዲያልፍ ወይም ያንን ጊዜ መቋቋም እንድትችሉ እግዚአብሔር ፀጋ እንዲሰጣችሁ መፀለይ ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሔር እሳት የሚመጣው ጥቅም የሌለውን ነገር ከሕይወታችን ለማቃጠልና ለእኛ መልካም መስሎ የታየን ነገር ግን እግዚአብሔር ያልወደደብንን ነገር ከእኛ ለማስወገድ ነው እንዲሁም እርሱን አልታዘዝ ስንለው ከፈጠረን አላማ ውጪ ለመኖር ስንሞክር እኛን በዚያ መንገድ ወደ ፈጠረን አላማ ለመምራት ይጠቀምበታል።
በዚያ ጊዜ ቃሉ ላይ ቆዩ መልስ አገኛለሁ ብላችሁ ሌሎች አማራጮች ፍለጋ አትዙሩ እሳቱ ከእግዚአብሔር ስለሆነ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ሚፈውሳችሁና መልስ የሚሰጣችሁ የለም።
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በምታልፍባቸው ነገሮች ውስጥ ከነገሮቹ መሸሽ የለብህም ልትፈራቸውም አይገባህም፡፡
ተስፋበኢየሱስ Channel
🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆
ጠብቅሀለሁ ጌታ ባስቀመጥከኝ ቦታ
በመጠበቂያዬ ላይ ዳግም እስክትመጣ🙌
ድምፅህን አሰማኝ ልቤ እንዲፀናና
ግን አንተ ዝም ካልከኝ እፈራለሁና...🥺🧎♂
ተስፋበኢየሱስ Channel
🔆 @HopeOfJesusChannel 🔆