Tofik Bahiru
Статистика обновлена 15.11.2026 в 03:29 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?
Динамика за 30 дней
Истории пока нет. График появится после следующих обновлений статистики.
Рекламные публикации
Последние публикации
Все посты канала →ዛሬ አባቴ ይቀመጡበት የነበረውን ወንበር አየሁት። ወንበሩ ባዶ ነበር!
ለረጅም ጊዜ ከፊቱ ቆምኩኝ። በዚያ ባዶ ወንበር ውስጥ ዳግመኛ የማይመለሱ ቀናትን፣ ተናፋቂ ድምፅና በየዕለቱ እናየው የነበረውን፣ የመኖሩን ታላቅ ፀጋ ግን በሚገባ ያልተገነዘብነውን ውብ ፊታቸውን አስታውሼ የቁጭት ስሜት ተሰማኝ። የተሰማኝ ስሜት ያለፉት ዘመናት ሁሉ በዚያ ባዶ ወንበር ውስጥ የተሰበሰቡ ያህል ነበር።
የሙሐመድ ﷺ ኡማ ሆይ!
ወላጆቻችሁ ከጎናችሁ ባሉበት ጊዜ የመኖራቸውን ፀጋ በሚገባ እወቁ። በአላህ ይሁንባችሁ! አንድ ቀን ድምፃቸውን ለመስማት ብትናፍቁም የማትሰሙበት፣ ከእነርሱ ጋር ተጨማሪ አንድ ሰዓት ብትቀመጡ፣ እጃቸውን ለተጨማሪ አንድ ጊዜ ብትስሙ፣ ወይም ከእነርሱ ጋር የበለጠ ጊዜ ልታሳልፉ የምትመኙበት ቀን ይመጣል። ዛሬ ግን ከእነርሱ ጋር የምታሳልፉት ረዥም ዘመን እንዳላችሁ ታስቡ ነበር!
የዱንያ ግርግርና የሥራ ብዛት የወላጆቻችሁን ዕድሜ ከእናንተ ላይ እንዳይቀሟችሁ ተጠንቀቁ!
ኻድሟቸው። ሳትሰለቹ አገልግሏቸው። በሚጠበቅባችሁ ልክ ባለማገልገላችሁ ተፀፅታችሁ፣ ነገርግን እነርሱን ማግኘት ሳትችሉ በመቅረታችሁ ከመቆጨታችሁ በፊት ዛሬ የምትችሉትን አድርጉ!
አብራችኋቸው ተቀመጡ፤ ጊዜያችሁንም ስጧቸው። ወላጆች የሚፈልጉት ገንዘብና ስጦታ አይደለም፤ አንዳንዴ ከጎናቸው መገኘታችሁ ብቻ ይበቃቸዋል።
ልባቸውን ደስ አሰኙ፤ ተደጋጋሚ ንግግራቸውን፣ ቁጣቸውን፣ የማይመቿችሁን ቃላቶቻቸውን በትዕግሥት አዳምጡ፤ ትእዛዞቻቸውን አትሰልቹ።
እጃቸውንና ግንባራቸውን ሳሙ፤ ፍላጎታቸውን ጠይቋቸው። እርዳታ እስኪጠይቋችሁ ድረስ አትጠብቁ፤ ፍላጎታቸውን አስቀድማችሁ ለማወቅ ጣሩ።
ዱዓ እንዲያደርጉላችሁ ለምኗቸው። ከአባትና ከእናት ቀልብ የሚወጣ ዱዓ ምን ያህል የመልካም በሮችን እንደሚከፍት ማን ያውቃል!
አስታውሱ! አንድ ቀን ስልካችሁ በእነርሱ ጥሪ እንዲጮህ፣ ድምፃቸውን እንድትሰሙ፣ ስማችሁን ሲጠሩ እንድትሰሙና ከእነርሱ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች እንኳን እንድትቀመጡ የምትመኙበት ቀን ይመጣል። በዚያ ቀን ግን ይህ ሁሉ ምኞት ብቻ ሆኖ ይቀራል!
ለእነርሱ በጎ መዋላችሁን ለነገ አታስተላልፉ፤ ዚያራችሁን አታዘግዩ፤ ጊዜያችሁንና ፍቅራችሁንም አትንፈጓቸው።
አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُل رَّبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا﴾ [الإسراء: ٢٣-٢٤]
«ጌታህም እርሱን ብቻ እንድትገዙ አዘዘ፤ ለወላጆችም መልካም እንድታደርጉ አዘዘ። ከእነርሱ አንዱ ወይም ሁለቱም ከአንተ ዘንድ እርጅና ላይ ቢደርሱ፣ 'ኡፍ' እንኳን አትበላቸው፤ አትገስጻቸውም፤ ለእነርሱም የተከበረ ንግግር ተናገርላቸው። ከርኅራኄም የተነሳ የትሕትናን ክንፍ ለእነርሱ ዘርጋ፤ 'ጌታዬ ሆይ! በልጅነቴ እንዳሳደጉኝ አንተም እዘንላቸው' በል።»
[ሱረቱል ኢስራእ፡ 23-24]
ይህ ብቻ አይደለም፤ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለእናትና ለአባት በጎ መዋልን ከታላላቅ የአላህ ውዴታ ማግኛ ተግባራት መካከል አስቀምጠውታል።
አንድ ሰው ነቢዩን ﷺ፦ «ከሰዎች ሁሉ በጎ ጓደኝነቴ የሚገባው ማን ነው?» ብሎ ጠየቃቸው። «እናትህ» አሉት። «ከዚያስ?» አላቸው። «እናትህ» አሉት። «ከዚያስ?» አላቸው። «እናትህ» አሉት። «ከዚያስ?» አላቸው። «ከዚያ አባትህ» አሉት።
[ሶሒሑል ቡኻሪና ሶሒሑ ሙስሊም]
ወላጆቻችሁ በሕይወት እያሉ ይህንን እድል ተጠቀሙበት። የጀነት ታላቅ በር በፊታችሁ ተከፍቶላችኋል። እነርሱ በሕይወት እያሉ ይህንን እድል አታባክኑ፤ ነገ ከእነርሱ ጋር ያሳለፋችሁት ጊዜ ወደ ትዝታና ወደ ናፍቆት ሊቀየር ይችላልና።
የወላጆች ፀጋ ከጎናችን እስካሉ ድረስ እንዲሁ በቃላት የሚታወቅ ብቻ ሳይሆን፣ በተግባር ልንጠብቀው የሚገባ አደራ ነው።
አላህ ሆይ! ከወላጆቻችን መካከል ወደ አንተ የሄዱትን ማርልን፤ በሕይወት ያሉትንም በታዛዥነትህ ላይ ዕድሜያቸውን አርዝምልን። ለእነርሱ በጎ እንድንውል፣ እንድናገለግልና እንድናስደስታቸው እርዳን። የወላጆቻችንን ዋጋ ካመለጡን በኋላ ከሚያውቁት አታድርገን።
:
አባቴ ሆይ! አላህ ይዘንልዎ። ወንበርዎ አሁንም ባዶ ነው፤ በልቤ ያሎትን ቦታ ግን ማንም ሊሞላው አይችልም።
:
✍ በቅርቡ አባታቸውን የሸኙት ሸይኽ ዐዲል አሕመድ ሸሪፍ በግል ያጋሩኝን ኻጢራ አፍኜ ከማስቀረው ለሁላችንም ትምህርት እንዲሆን ተርጉሜ ያቀረብኩላችሁ ነው። አላህ ያስረዳን!
ከኛ በፈለግኸው ነገር ላይ አንተው አግዘን።
ውጭና ውስጣችንን አሳምርልን።
ከወደድካቸው ባሮችህ ጋር ቋጥረን።
ከችሮታና ከእድያህ ጨምረን።
ልመናችንን ተቀበለን።