Телеграм

📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔

@amharicspritualbooks Религия и эзотерика
РКН: проверяем Не иноагент
Buy ads: https://telega.io/c/amharicspritualbooks

ይህ ቻናል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ፣ መጽሔቶችን ፣ ክርስቲያናዊ የድረ-ገጽ ጽሁፎችን በሰፊው ለአንባቢያን ለማድረስ ይጥራል። የመጽሐፍ ምረቃ ማስታወቂያ ፣ ሀሳብ እና አስተያየት ካሎት በ Direct message በኩል ያድርሱን።

Статистика обновлена 15.11.2026 в 03:06 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики29 971
Охват поста8 139 27% от подписчиков
ERR за месяц27,16%
ERR за 24 часа6,77%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔 tg29 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ከሶስት ቀናት በፊት ከቀድሞው የትምህርት ቤት ጓደኛዬ የተላከልኝ የSMS መልእክት👇

"ሰላም Zed እንዴት ነህ! ይኸውልህ! ትላንትና ምን ተከሰተ መሰለህ ድንገት የስልኬ ስክሪን በራ። የገባውን የጽሑፍ መልዕክት ስመለከት፣ የቀድሞ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ነበረች

በትምህርት ቤት ዘመናችን የነበረን ቅርበት የጠበቀ ነበር፤ ከተለያየን በኋላም ቢሆን እንኳ በመካከላችን ያለው ቅርርብ የጠበቀ ነበር። ሆኖም ግን፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በግንኙነታችን ላይ አንድ ያልተጻፈ ሕግ እየተተገበረ መሆኑን በዝምታ አስተውያለሁ።

እርሷ ወደ እኔ ብቅ የምትለው ሁልጊዜ በሕይወቷ ውስጥ አንድ ዓይነት ማዕበል ሲነሳ ብቻ ነው። ልቧ ሲሰበር፣ ቤተሰቦቿ ሲያስከፏት፣ ወይም በሥራ ቦታዋ ተስፋ ስትቆርጥ... የስሜት ሸክሟን የምታራግፍበት "የነፍስ ማረፊያ ጣቢያ" አድርጋ እየተጠቀመችብኝ ነው። ሰዓታትን የሚፈጁ ምክሮቼንና ማጽናኛዎቼን ትቀበላለች። ልክ ነፋሱ ጸጥ ሲልና ፊቷ ሲፈካ ግን፣ እንደ ጠዋት ጤዛ ትተናለች። ስለ እኔ ሕይወት፣ ስለ ድካሜ ወይም ስለ ደስታዬ ጠይቃኝ እንኳ አታውቅም።

የትናንቱ መልዕክቷም ከቀደሙት የተለየ አልነበረም፦ "ዛሬ በጣም ከፍቶኛል፣ ትንሽ እናውራ?" የሚል ነበር።

መልዕክቱን እያነበብኩ ለጥቂት ደቂቃዎች በሃሳብ ተዋጥኩ። መልስ ብሰጣት፣ ዛሬም የእርሷን የስሜት ቁስል ለመጠገን ስል የራሴን ውስጣዊ ሰላም አሳልፌ እንደምሰጥ አውቃለሁ። ዝም ብላት ደግሞ፣ በውስጤ ያለው መንፈሳዊ ሰው "እንዴት የተቸገረችን እህት ችላ ትላለህ? የክርስቶስ ፍቅር የት አለ?" እያለ ይሞግተኛል(በዛላይ ለእርሷ የፍቅር ስሜት አለኝ)

በመጨረሻም አን ውሳኔ ወሰንኩ። ይኸውም! መልዕክቱን አንብቤ በዝምታ አለፍኩት።

በልቤ ውስጥ ምንም ዓይነት ጥላቻ፣ ቅሬታ ወይም የበቀል ስሜት የለም። እንደውም በጸሎቴ አሰብኳት። ነገር ግን፣ የእርሷን ሕይወት ለማቅናት ስል የራሴን መንፈሳዊና አእምሮአዊ ጤንነት መስዋዕት ማድረግ እንደሌለብኝ አመንኩ። የራሴን ሰላም ለመጠበቅ ስል፣ ለጊዜው እርሷንና ችግሮቿን "ቸል ብዬ ማለፍን" መረጥኩ።

አሁን ግን አንድ ጥያቄ በውስጤ እየተመላለሰ ዕረፍት እየነሳኝ ነው

ይህ ውሳኔዬ መጽሐፍ ቅዱስ የሚደግፈው "ጤናማ ቸልተኝነት" (ራስን ከአድካሚ ግንኙነት የመጠበቅ ጥበብ) ሊባል የሚችል ነው? ወይስ በመንፈሳዊነት ሽፋን የተሸፈነ ግድየለሽነትና ፍቅር ማጣት ነው?
ሌሎችን ለመርዳት ስንል የራሳችንን ውስጣዊ ሰላም እስከ ምን ድረስ ነው መስዋዕት ማድረግ ያለብን? መንፈሳዊ ድንበር የቱ ጋር ነው የሚሰመረው? እባክህ እስቲ የሆነ ነገር በልኝ Zed!🙏



Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library
👁 2 тыс. ❤ 28😁 2 💬 3 ↻ 12 13 ноября
📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔 tg29 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ኢየሱስ አምላክ ከሆነ፣ አምላክ እንዴት ሊሞት ይችላል? ለሚለው ጥያቄ እኛ ክርስቲያኖች ለሙስሊም ወገኖቻችን እንዴት ብንመልስላቸው ጥሩ ይመስላችኋል?

በመጀመሪያ ክርስቲያኖች ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፣ ከእስልምናው የዓለም አተያይ በመነሳት እንዲወያዩ አበረታታለሁ። መጀመሪያ ላይ ይህ ጥያቄ ብዙ ክርስቲያኖችን ግራ ሊያጋባ የሚችል ይመስላል፤ ነገር ግን የጥያቄው መነሻ መሠረት ስህተት ያለበትና አቋም የታጣበት ነው። ምክንያቱም ሙስሊሞች ለኢየሱስ ብቻ ሲሉ የ"ሞት"ን ትርጓሜ ወደ "መኖር ማክተም" እየቀየሩት ስለሆነ ነው። ጥያቄያቸውም "አምላክ እንዴት መኖር ያቆማል" የሚል ይመስላል። ችግሩ ግን፣ ለክርስቲያኖችም ሆነ ለሙስሊሞች የ"ሞት" ትርጓሜ "መኖር ማቆም" ማለት አይደለም።

የሚገርመው፣ ቁርአን ራሱ ይህንን ሐሳብ የሚደግፉ ምሳሌዎችን ይሰጣል፦

"በአላህ መንገድ የሚገደሉትንም 'ሙታን' አትበሏቸው፤ እነርሱ በሕይወት ናቸው፤ ነገር ግን እናንተ አታውቁም (አትገነዘቡም)።" (ሱራ 2፡154)

ተመሳሳይ ሐሳብ በሱራ 3፡169 ላይም እናገኛለን፦

"በአላህ መንገድ የተገደሉትን እንደ ሙታን አትቁጠሯቸው፤ እነርሱ በጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ሲሳይ ይለገሱላቸማል።"

እነዚህ ጥቅሶች አንድ ሙስሊም ከራሱ የእምነት ማዕቀፍ ውስጥ ሳይወጣ እንኳ፣ ሞት ማለት "መኖር ማቆም" እንዳልሆነ እንዲረዳ ያደርጉታል። በክርስቲያናዊ ትምህርት ግን የኢየሱስ ሞት ከዚህ በላይ ትልቅና ጥልቅ ትርጉም አለው። ኢየሱስ የሰው ልጅን ባሕርይ የተዋሐደው ለተወሰኑ ዓላማዎች ነበር፦

"ልጆቹ ሥጋንና ደምን ስለ ተካፈሉ፣ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፣ ይህም ዲያብሎስ ነው፣ በሞትም ፍርሃት ዕድሜ ልካቸው በባርነት ታስረው የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፣ እርሱ ደግሞ እንዲሁ በሥጋና በደም ተካፈለ።" (ዕብራውያን 2፡14–15)

"የሰው ልጅ እንኳ ሊያገለግለው ሳይሆን ሊያገለግል፣ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጥቷልና።" (ማርቆስ 10፡45)

"ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ፤ ከአብ እንደ ተገኘ የአንድያ ልጅ ክብር የሆነውን ክብሩን አየን። ... ማንም እግዚአብሔርን ከቶ አላየውም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድያ ልጅ እርሱ ተረከው። (ዮሐንስ 1፡14–18)

በነገራችን ላይ እኮ የኢየሱስ መለኮታዊ ማንነቱ ሞቷል አላልንም አይደል እንዴ! ይልቁንም ገንዘቡ አድርጎ የወሰደው ስጋው እንጂ።

Telegram| Facebook | Instagram  | Twitter(X) |Christian e Library
👁 3.5 тыс. ❤ 40👍 6👏 2 ↻ 34 11 ноября
📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔 tg29 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
መጣ መጣ የሳምንቱ ማለቂያ(Weekend) በዚሁለት ቀናት የተበላሸም ሆነ አዲስ የሚገጠሙ የልብስ መኪናዎችን እያስተካከልንና እየገጠምን እንገኛለን! ከታች ባሉ አድራሻዎች ቀድመው ቀጠሮ ያሲዙ ባሉበት መፍትሄ እንሰጣለን!

የአዳዲስ ማሽን ገጠማና የተበላሹ ማሽኖችን የመጠገን ስራ እንሰራለን +251925447525 ወይም @amanu97 ላይ ያናግሩን፥ ያሉበት መጥተን መፍትሄ እንሰጣልን።
📍አድራሻ፦ አዲስ አበባ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.me/machine_maintenance
👁 5.7 тыс. ❤ 7👍 7👏 1 💬 2 ↻ 1 6 ноября