Телеграм

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

@yasin_nuru Религия и эзотерика
РКН: проверяем Не иноагент
የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች

Yasin Nuru

"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7}

UNOFFICIAL

ለአስተያየት👇👇
@Hasabbbbot

ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇
@yasin_nuru_hadis

Статистика обновлена 15.11.2026 в 04:30 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики42 435
Охват поста12 481 29% от подписчиков
ERR за месяц29,41%
ERR за 24 часа12,67%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU tg42 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
20 ምርጥ መልዕክቶችን ላካፍላችሁ

1. ነገሮች ሲጠኑባችሁ ወደ ሱጁድና ዱዓእ ፍጠኑ እንጂ ብሶትና ለቅሶ አታብዙ፡፡

2. ሁሉም ነገር ይሄዳል፤ ሲሄድ ግን አይመለስም፡፡ ዱዓእ ሲቀር፡፡ ዱዓእ ተስፋን፣ በረከትን፣ ሲሳይን፣ ድልን፣ ስጦታን ይዞ ይመለሳል፡፡

3. በምድር ላይ አንድም ስኬታማ ሰው የለም፡፡ ለወላጆቹ መልካም የመዋል ታሪክ ያለው ቢሆን እንጂ፡፡

4. የሰው ልጅ ሆኖ ከሀሳብ ነፃ የሆነ የለም፡፡ ሆኖም ግን ያለበት ሀገር ዱንያ መሆኗን እያስታወሰ ፈገግ የሚል ብዙ ሰው አለ፡፡

5. ምርጦቹ ጓደኞችህ ዱንያ የሳቀችልህ ቀን አይደናገጡም፡፡ በዞረችብህ ጊዜም አይደሰቱብህም፡፡

6. ግርማ ሞገስን ከሚያጎናጽፉ ነገሮች መካከል ብዙ አለማውራት፤ የፊትን ዉበት ከሚጨምሩ ነገሮች መካከል ፈገግታን ማብዛት ይገኙበታል፡፡

7. የሰው ልጅ ባያምንበትም እንኳ የሚናገርን ሰው ሀሳብ ቢያዳምጥ የሚማረው ነገር ይኖራል፡፡

8. ልጅህን ቁርኣንን አስተምረው፤ ቁርኣን ሁሉንም ነገር ያስተምረዋል፡፡

9. ትላልቅ ሰዎችን አክብሩ፤ ዘመናቸው ባልሆነ ዘመን ውስጥ እየኖሩ ነውና፡፡

10. ሁሉንም ሰው ለማስወደድና ለማርካት አትፍጨርጨር፡፡ በዚህ ጉዳይ ነቢያትም እንኳን አልተሳካላቸውምና፡፡

11. ዉስጥህን ህመም እየተሰማህ ፈገግ የምትል ከሆነ የጥንካሬህ ማሳያ ነው፡፡

12. የሰው ልጅ የሚመዘነው ባለው ነገር ሳይሆን በሚሰጠው ነው፡፡ ፀሐይ እሳት ጭምር አላት ነገርግን ብርሃን ትሠጣለች፤ ፍጥረተ ዓለሙን በብርሃን ትሞላለች፡፡

13. በእናቱ እግር ሥር አገልጋይ ሆኖ የኖረ በሰዎች አናት ላይ ንጉስ ሆኖ ይኖራል፡፡

14. ብዙ በመናገር የማይታወቅ ሰው መናገር ሲጀምር ትኩረት ይስባል፡፡

15. ባመለጠችህ አንዲት ኮከብ አትከፋ፡፡ ሰማይ በከዋክብት የተሞላች ናት፡፡ እሷን ከረሳህ ምናልባት ጨረቃ ትወጣልህ ይሆናል ማን ያውቃል፡፡

16. ከአላህ (ሱ.ወ.) መልካም ነገር እንጂ አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ወደ ቀናው መንገድ መራን፣ ጤና ሰጠን፣ ዕድሜ ሰጠን፣ ቤተሰብ ሰጠን፣ ብዙ ብዙ ነገር ሰጠን፡፡

17. ልንረሳቸው ብንፈልግ እንኳን ዉስጣችን የማይረሳቸው ብዙ ኃጢአቶችን ይዘን እየዞርን ነው፡፡

18. የሐዘን ባቡር ፉርጎው ቢበዛም ቢረዝምም የመጨረሻ ፌርማታው ደስታ ስለመሆኑ  አንጠራጠር፡፡
ዕድል
19. ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አንዳንድ  ደግሞ ዕድሜ ነው፡፡ ዕድሜህ ሊሆን የሚችልን ዕድል በቀላሉ አታሳልፍ፡፡

20. የተጃጃለ ሰው ሁኔታው እንደ በራሪ አዕዋፍ ነው፡፡ ከፍ ባለ ቁጥር ሰውን አሳንሶ ይመለከታል፡፡

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru
👁 3.3 тыс. ❤ 76👍 10🥰 9 💬 22 ↻ 63 вчера в 08:15
ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU tg42 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
'የታክሲ የለኝም እባክህ ልጄን ይዘሃት ሂድ....😥;

«እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!»

ዛሬ ጠዋት ታክሲ ውስጥ ሙሉ ተሳፋሪውን በእንባ ያራጨ፣ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን እያደማው ያለ ልብ ሰባሪ ክስተት...

ጠዋት ወደ ስራ ለመሄድ ታክሲ ተሰልፌ ገባሁ። በመስኮት በኩል ሳስተውል አንዲት እናት በጣም ቆንጆ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ትንሽ ልጇን እጅ ይዛ ቆማለች። ታክሲው ሊሞላ ጥቂት ሰው ብቻ ነው የቀረው፤ «ይቺ እናት ለምን አትገባም? ልጇ አረፈደች እኮ...» እያልኩ በልቤ ሳስብ...

እናትየው ድንገት ወደ መጀመሪያው ወንበር ተጠግታ መስኮቱን አንኳኳች። የፊት ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰውዬ መስኮቱን ሲከፍተው በለዘበ፣ በሀፍረትና በጭንቀት በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለችው፦

«ወንድሜ... እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!»

ይሄን ስትል የታክሲው ድባብ ድንገት ፀጥ አለ፤ ልቤ ተንሰፈሰፈ! «እቀፋት ንፁህ ናት» የሚለው ቃሏ እንደ ጦር ልቤ ውስጥ ተሰካብኝ። ድህነት እንዲህ ያሳንሳል? የገዛ ልጇን ሰው እንዲሸከምላት ስትለምን እንኳ «ንፁህ ናት» ብላ ይቅርታ እንድትጠይቅ ያስገድዳል?

የፊት ወንበር የተቀመጠው ጨዋ ሰው ያለምንም ማመንታት «ኧረ በደስታ እህቴ! ምንም ችግር የለውም፤ ችግር አይንካሽ አምጪያት» ብሎ ልጅቷን በክብር ተቀብሎ አቀፋት። ረዳቱም «የትምህርት ቤቱን በር አውቀዋለሁ እዛው አወርዳታለሁ አትጨነቂ» አለ።

እናት ግን ልቧ አልቻለም... የልቧ ጭንቀት እረፍት ነሳትና ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው «እባክህ ስልክህን ጻፍልኝ?» አለችው፤ የእናት አንጀት አይደል! ስልኩን ተቀበለች።
ድህነት አይኑ ይጥፋ ወላሂ!  ይሄን ያየው ተሳፋሪ በሙሉ ልቡ ተነካ። ሁሉም ኪሱን ፈትሾ ለነገዋ፣ ለቀጣዩ ቀኗ የታክሲ የሚሆናትን ብር አዋጥቶ ሰጣት።

ታክሲው ተነስቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር... ያቺ ምስኪን እናት ታክሲው እይታዋ እስኪሰወር ድረስ እዛው ቆማ፣ በልጇ ላይ ያፈጠጠውን የፍቅርና የጭንቀት ዐይኗን ሳትነቅል እያየችን ቀረች።

እናት ማለት ይቺ ናት... ለልጇ ትምህርት ስትል ክብሯን ጥላ የምትለምን፣ ራሷ በባዶ እግሯ ቆማ ልጇን ወደ ከፍታ የምትሸኝ!
ፈጣሪ ለደጉ ተሳፋሪም፣ ለምስኪኗ እናትም ይድረስላቸው።

(መረጃው የአሃዱ ሚዲያ ነው/Afi Natilus)

@yasin_nuru @yasin_nuru
👁 5.4 тыс. 💔 188❤ 58😢 55 💬 53 ↻ 62 13 ноября
ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU tg42 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ዱዓ (የበለጠ) ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ወቅቶችና ሀኔታዎች!

1. በአዛንና ኢቃም መሀል

2.ከሁሉም ፈርድ ሰላቶች መጨረሻ ላይ

3. በሌሊት የመጨረሻ ክፍል ላይ

4. ሱጁድ ላይ

5. በሚፆምበትና እንዲሁም በሚፈጠርበት ወቅት ላይ

6. በጀሙዓ የመጨረሻ ክፍል ላይ

7. ዘምዘም ውሀን በሚጠጣበት ጊዜ

8. በዝናብ ወቅት

9. የተበዳይ ዱዓ

10. አንድ ሙስሊም ለሌላ ወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ

11. የመንገደኛ ዱዓ

12. ወላጅ ለልጁ የሚያደርገው

وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

@yasin_nuru
@yasin_nuru
👁 6.9 тыс. ❤ 139👍 38🥰 9 💬 38 ↻ 98 11 ноября