በትግራይ ክልል ሸራሮ፣ ዓዲ ሃገራይ እና ቢያራ በተባሉት አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ማክሰኞ እና ረቡዕ ኅዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም. የተካሄደው ውጊያ፣ የገጠር አካባቢዎችን ያዳረሰ ነበር።
ባለፉት ቀናት በነበሩት ውጊያዎች፣ እንደ መድፍ ያሉ ከባድ መሣሪያ እና ድሮን ጥቅም ላይ መዋላቸውን ሁለት ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አንድ ነዋሪ፣ "ማክሰኞ እና ረቡዕ ዕለት በዓዲ ክልተ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ያለምንም እረፍት ውጊያ ሲካሄድ ነበር። ስንት ነፍሰ ጡሮች እና ሕፃናት ባሉበት፣ በድንገት የከባድ መሣሪያ እና የድሮን ድብደባ ሲከፈት ሕዝቡ በፍርሃት ተደናግጦ ቆመ" ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ 👉🏾👉🏾 https://bbc.in/4ezHsD1