እንግሊዝ በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ የሚንቀሳቀሱ ሰርጓጅ መርከቦችን ለመከታተልና የባሕር ውስጥ ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ 90 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ አዲስ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ይፋ አድርጋለች።
“Atlantic Net” ተብሎ የተሰየመው ፕሮጀክት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን፣ የውሃ ውስጥ ዳሳሾችንና ራስ-ገዝ ድሮኖችን በአንድ የክትትል ሥርዓት ያቀናጃል።
ቴክኖሎጂው የሰርጓጅ መርከቦችን እንቅስቃሴ ቀድሞ ለማወቅ፣ የመገናኛ ገመዶችንና የኃይል መስመሮችንም ከጥቃት ለመጠበቅ ይረዳል።
ፕሮጀክቱ ከ Ocean Infinity Solutions ጋር በመተባበር የሚከናወን ነው፡፡ የሰው ኃይል የሚጠይቁ ባህላዊ የባሕር ኃይል ሥርዓቶችን በሮቦቲክስና በራስ-ገዝ ቴክኖሎጂዎች ለማጠናከር ያስችላል።
ፕሮጀክቱ ወደ 200 የሚጠጉ አዳዲስ የሙያ ዕድሎችንም እንደሚፈጥር ተገልጿል። ይህ እርምጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የባሕር ደኅንነትን የማረጋገጥ አዲስ ጉዞ ማሳያ ነው፡፡
ድረ ገጽ | | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን |