አንዳንዴ ቆም ብዬ ሳስበው እዜር ሰውን ከአፈር ለማበጃጀት ስንት ግዜ ወራት ዘመን ፈጀበት እላለው... በዚ መሀል ታክሲው መጣ😁 ይሄ ሁሉ ትርኪ ሚርኪ ሀሳብ ማስበው ጥዋት taxi ስጠብቅ ነው ረዳቱ ከታክሲው እንደ ጂምናስቲክ ስፖርተኛ ተስፈንጥሮ ካበቃ በዋላ... 😁እንደ ጀማሪ police ዙሪያ ገባውን ቃኘና በእጁ ጠቆመና እንደ ትያትር ተመልካች ፈጠጠ ሁሉም ገነት ይገቡ ይመስል ለመሞት አንድ ሀሙስ የቀራት ሸበቶ ታክሲ ላይ ይከመሩ ጀመር እኔ መስኮት ስር መቀመጥ ስለምወድ የሞት ሞቴን ተጋፍቼ ተቀመጥኩና ጉዞ ተጀመረ...
አስቤው ይሁን በደመነሴ ላርገው ባላቅም እራሴን እያነበብኩ አገኘዋለሁ...ምን አልባት ማስታወስ የማልፈልጋቸውን ትዝታዎቼን ስለሚያስረሳኝ ይሆን.. ሌላ አለም ውስጥ ስለሚዘፍቀኝ ይሁን እንጃ... ሰው እንዴት ከትናቱ ሚያስታርቀው አንድ ክስተት እንኳ ያጣል ብዬ ጠይቅ እና ምላሽ ሳጣ ዝም እላለሁ.. ድንገት ከጎኔ "አባት አባት " የሚል ድምፅ ከምተሀተኛ እጅ ጋር ተባብረው ከሀሳቤ አነቁኝ ዞርኩ... ለምን ያህል ግዜ እንደሆነ ባላቅም እንደ ደመኛ ፊት ለፊት ተፋጠጥን... ደገመችልኝ "ሂሳብ እያለህ ነው ወንድም"... ተደናበርኩ እንዲ ስሆን እራሴን አግኝቼው አላቅም አንዲትም ቃል ሳላወጣ 6ቱንም ኪሴን በረበርኳቸው ስባሪ ሳንቲም አጣው 😁ይባስ ብሎ ስልኬም የለም...
ላቤ ካናቴ እንደ ረጋ ቅቤ እየወረደ ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ ማለት ጀመረ... "ወንድም ችግር አለ አይኖችህኮ ቀሉ አለቺኝ" ...ሊወርዱ ሲታገሉ የነበሩትን የእንባ ዘለላዋቼን ጠርጌ... በደከመ ድምፅ "ዋሌቴን ሰረቁኝ አልኳት"...
😁ይቀጥላል final ነገ
🖌121