(በሙጃሒድ ካሊድ)
[ ከስልሳ አመት በፊት , በ1959 ዓ.ል የአፄ ሀይለ ስላሴ የህዝብ እንደራሴ ፓርላማ ውስጥ 35 ሙስሊም ተወካዮች ነበሩ :: የደሴ ከተማ እንደራሴው ታዋቂው ፊት አውራሪ አመዴ ለማ አንዱ ናቸው ::
በአፄ ኃ/ ስላሴ የስልጣን ዘመን ዘጠኝ መስጅድ ተሰርቷል ፤ አንድም መስጅድ ፈርሶ አያውቅም :: ለመጀመርያ ግዜ በአይሮፕላን ሀጅ ጉዞ የተጀመረው በእሳቸው ዘመን 1940 ነው , ይህም አድካሚ የሆነውን የእግር ጉዞ ከሶስት ወር ወደ ሶስት ሰአት ቀንሶታል ::
ለመጀመርያ ግዜ ቁርአን ከአረብኛ ወደ አማርኛ ተተርጉም እንዲታተም ትዕዛዝ ሰተዋል :: በ1960 ለሸይኽ ሲራጅ ሙሀመድ እና አምስት ተማሪዎቻቸው ሙሉ ወጪ ሸፍነው ሀጅ ልከዋቸውል ... :: ]