የመውጫ ፈተና የአጋማሽ ዓመት #በድጋሜ_ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 11-17/2019 ዓ.ም ይከናወናል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ እና የመግቢያ ፈተናዎች የሚሰጡባቸውን ጊዜያት አረጋግጧል።
በዚህም፣ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 04-10/2019 ዓ.ም መሆኑ ታውቋል።
የግል ተቋማት እና በድጋሚ ተፈታኞች የመውጫ ፈተና የአጋማሽ ዓመት የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 11-17/2019 ዓ.ም ይከናወናል።
የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 10-30/2019 ዓ.ም ይከናወናል።
የአጋማሽ ዓመቱ የመውጫ እና የመግቢያ ፈተናዎች ተፈታኞች ምዝገባ በራስ-አገዝ የምዝገባ ሥርዓት (Self-Registration System) የሚከናወን መሆኑን አገልገሎቱ አሳውቋል።
ሁሉም ተቋማት ተፈታኞቻቸውን በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማስመዝገብ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻቸውን እንዲያጠናቅቁ፥ ፈተናዎቹን ለሚያስፈትኑ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዛሬው ዕለት በጻፈው ሰርኩላር አሳስቧል።
ለምዝገባ የሚከፈለው ክፍያም በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተሻሽሎ በፀደቀው የክፍያ ተመን መሠረት እንደሆነ ተገልጿል።
ትምህርታዊ መረጃ™ ✅
✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers