Телеграм

ustaz yasin nuru offcial

@ustaz_yasin_nuru_offcial Религия и эзотерика
РКН: проверяем Иноагент: проверяем
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial

Статистика обновлена 15.11.2026 в 05:02 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики6 570
Охват поста1 838 28% от подписчиков
ERR за месяц27,98%
ERR за 24 часа14,22%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
ustaz yasin nuru offcial tg6.6 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ሁለት ችላ ያልናቸው ነገሮች
==================

❶ አቡበክር ኢብኑ ዐያሽ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል፦

«ከሰዎች አንዱ አንድ ዲርሃም ቢጠፋበት፣ ቀኑን ሙሉ፦ «ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ…! ዲርሃሜ ጠፋ!» እያለ ያሳልፋል። ዲርሃሙ እንደጠፋበት ቀኑን ሙሉ ያወራል፤ ነገር ግን፦ «ቀኔ አለፈ፤ በውስጡም ምንም መልካም ሥራ ሳልሰራበት አለፈ!» በማለት አያዝንም።»

📚 ሒልየቱል አውሊያእ፥ ቅጽ 8፥ ገጽ 303

❷ ኢማሙ ሐሰን አልበስሪ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ፦

«በደጋጎቹ ዘመን አንድ ሰው እሾህ ቢወጋው እንኳን፦ «ይህ በሠራሁት ኃጢአት ምክንያት መሆኑን አውቃለሁ፤ ጌታዬም በእኔ ላይ በደል አልፈጸመም» ይል ነበር።»

💮 ሁለቱ ነገሮች
————————
— ሰው የጠፋበትን ገንዘብ እንደ ትልቅ ኪሳራ ይቆጥራል፤ ነገር ግን የሚያልፈውን ዕድሜ እና ያለ መልካም ሥራ የሚያልፉትን ቀናት አያስተውልም። ይህ ከባድ ቸልተኝነት ነው። ጸጸት በማይጠቅምበት ጊዜም ጸጸትን ያከናንባል!

— ሙእሚን በሚደርስበት መከራ ላይ ነፍሱን ይመረምራል፣ ኃጢአቱንም ይጠይቃል፤ አላህንም ከበደል ያጠራል። የሚደርስበትን ችግር በገዛ እጁ፣ በወንጀሉ መዘዝ የደረሰበት መሆኑን ያስተነትናል እንጂ አላህን አያማርርም!

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
👁 934 ❤ 15👍 10🔥 1 ↻ 7 9 ноября
ustaz yasin nuru offcial tg6.6 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
{إِنَّ الإِنسانَ لِرَبِّهِ لَكَنودٌ}


የሰው ልጅ ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው::

[العاديات - آية 6]
:
ሐሰኑል በስሪይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል፦

«[በዚህ አንቀጽ ላይ እንደተመለከተው] የሰው ልጅ ጌታውን አብዝቶ የሚያማርር ነው፤ መከራዎችን ይቆጥራል፣ ፀጋዎችን ግን ይረሳል።»

📚 ተፍሲር አል-ጠበሪ
:
ሰው የሚደርስበትን ችግር በቀላሉ ያስታውሳል፤ ነገር ግን አላህ የለገሰውን ብዙ ፀጋዎች ይዘነጋል። ስለዚህ ከሙእሚን የሚጠበቀው በመከራ ጊዜ መታገሥ፣ በፀጋ ጊዜ ማመስገንና በሁሉም ሁኔታው ውስጥ አላህን ማስታወስ ነው።
የአላህ መልክተኛ [ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም] እንዲህ ብለዋል: ‐
«የሙእሚን ነገር ይደንቃል። ሁሉም ነገሩ ለርሱ መልካም ነው። ጥሩ ነገር ካጋጠመው አላህን ያመሰግናል፤ መልካምም ይሆንለታል። ጉዳት ከገጠመውም ይታገሳል፤ መልካምም ይሆንለታል።»
የፈካ ማለዳ ይሁንልን!

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈ @ustaz_yasin_nuru_offcial
👁 1.1 тыс. ❤ 13😢 2 ↻ 2 8 ноября
ustaz yasin nuru offcial tg6.6 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ኢላሂ!
የማይወድቅ ዱዐ ስጠን።
ሁኔታችንን አስተካክል።
ልጆቻችንን አብጅልን።
ያማረ አደብ ስጠን።
በረካ ስጠን።
ቀልባችንን አርጥብልን።
ጭንቀታችንን ገላግለን።
ጉዳያችንን አግራልን።
በሽተኞችን አሽርልን።
ለሟቾቻችን እዘን።
ወንጀላችንን ማርልን።
ነውራችንን ሽፍንልን።
መከራን አቅልልልን።
ከፈተና ጠብቀን።
አሚን!              
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈
@ustaz_yasin_nuru_offcial
👁 1.7 тыс. ❤ 35 ↻ 11 4 ноября