Телеграм

ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች

@ney_ney_emye_maryam Религия и эзотерика
РКН: проверяем Не иноагент
Buy ads : here
https://telega.io/c/ney_ney_emye_maryam

♦️⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
🎻 የበገና መዝሙራት  
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @kingo08bot ላይ

Статистика обновлена 16.11.2026 в 18:36 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики46 973 +24 за 1 день
Охват поста3 142 7% от подписчиков
ERR за месяц6,69%
ERR за 24 часа3,79%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች tg46 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
#ድንግል_ማርያም_በቤተመቅደስ

ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ አሰምታ ትናገር ነበር
ሰላም ላንቺ ይሄን አለኝ ቅዱስ ገብርኤል
ሌላ ምንም አላውቅ ያውቃል እግዚአብሔር /2/


ከመቅደስ ቁጭ ብዬ ትንቢት እየሰማሁ
ሀሩን አስማምቼ ጥበብን እየፈተልኩ
ሳለሁ በመገረም ያንን ቃል አስቤ
አምላክ ሰው ሆነብኝ ተመሰጠ ልቤ
ማናት ብዬ ሳስብ ያቺ ብላቴና
ገብርኤል ደረሰ ብስራቱን ያዘና
ዙፋኑ አደረገኝ የባሪያቱን ውርደት ተመልክቷልና

አዝ ..
እንዴት ያንን ማህፀን ሰማይን ይሆናል
የልዑሉ ዙፋን ወዴት ይተከላል
እያልኩኝ ስጠይቅ በልቤ ለራሴ
የመንፈስ ቅዱስ ሃይል አደረ በራሴ
ማናት ብዬ ሳስብ ያቺ ብላቴና
ገብርኤል ደረሰ ብስራቱን ያዘና
ዙፋኑ አደረገኝ የባሪያቱን ውርደት ተመልክቷልና

አዝ ..
እንዴት ከድሃ ቤት ይሄ ንጉስ ያድራል
ለርሱ የተገባ ሰው ወዴት ይገኛል
ገሊላን አሰብኳት ዞሬ በህሊና
ለካስ ተሸንፏል በባሪያው ትትና
ማናት ብዬ ሳስብ ያቺ ብላቴና
ገብርኤል ደረሰ ብስራቱን ያዘና
ዙፋኑ አደረገኝ የባሪያቱን ውርደት ተመልክቷልና

አዝ ..
እሳት የማይበላው ሀመልማል አይኖርም
እንዲህ ያለ ቅጠል ናዝሬት አይገኝም
ህሊናዬ መጥቆ ሲበር ወደ ሲና
አንቺኮነሽ አለኝ ገብርኤል መጣና
ማናት ብዬ ሳስብ ያቺ ብላቴና
ገብርኤል ደረሰ ብስራቱን ያዘና
ዙፋኑ አደረገኝ የባሪያቱን ውርደት ተመልክቷልና
ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ አሰምታ ትናገር ነበር
ሰላም ላንቺ ይሄን አለኝ ቅዱስ ገብርኤል
ሌላ ምንም አላውቅ ያውቃል እግዚአብሔር


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
     #ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏

    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

   ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot
👁 1.8 тыс. 😘 12❤ 9🥰 6 ↻ 40 8 ноября
ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች tg46 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
#አክሊለ_ፅጌ

አክሊለ ፅጌ ማርያም አክሊለ ፅጌ/2/

ስሟ ማርያም ነው    አክሊለ ፅጌ
የጌታ እናት             "
እናት አባቷ             "
ያወጡላት              "
ከምድር ማር          "
ከሰማይ ያም          "
ብለው ሰየሟት         "
ድንግል ማርያምን         "

አዝ

የስሟ ጣህም          አክሊለ ፅጌ
ከማር ይበልጣል         "
እንደሷ ያለ               "
ከየት ይገኛል           "
የፍቅር መዝገብ        "
ነቅህ የሌለባት              "
ለክብሯ ወደር           "
ማን አግኝቶላት               "
            አዝ......
የከበረ ዘውድ          አክሊለ ፅጌ
የወርቅ ሙዳይ
የሽቱ ብልቃጥ    
የነፍሴ ሲሳይ           "
ከጥፋት ውሀ    "
ኖህ የዳነብሽ             "
የሰላም መርከብ       "
ቤቱ አንቺ ነሽ                      "
             አዝ......
በቤተ መቅደስ            አክሊለ ፅጌ
ስትኖር ተመርጣ                   "
ምግቧን ይዞላት                    "
ፋኑኤል መጣ                        "
አስራ አምስት ዓመት               "
ሲሆናት ድንግል                     "
በገብርኤል ብስራት                "
ተፀነሰ ቃል                            "


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
     #ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏

    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

   ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot
👁 2.4 тыс. 🥰 14❤ 11😘 4 ↻ 24 7 ноября
ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች tg46 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
#በልሳነ_ሱራፊ

በልሳነ ሱራፊ ቅዱስ
የኪሩብ ዙፋን ንጉሥ
ሥላሴ መመኪያችን
አንተ ነህ አምላካችን

በስብሐት ተከብበህ ሳለህ በቅድምና
ከሰማይ ወረደ የምስጋናህ መና
የኋላውን ኑሮ በምድር እንዲቀምሰው
የአባትነት ፍቅርህ ፈቀደለት ለሰው

የሰውን ድካሙን አንተው ታውቀዋለህ
ከእንቅልፉ እስኪነቃ ትታገሠዋለህ
ፍቅርህን ተረድቶ ማረኝ ያለ ለታ
በመላእክት ሀገር ይኾናል ደስታ

ለፍርድ አትቸኩልም ፈጥነህ ልታጠፋ
የተናቅን ስንኾን አትቆርጥብን ተስፋ
አቤት ያንተ ሥራ አቤት ያንተ ነገር
ስጦታህ አያልቅም ቢወራ ቢነገር

ደስታም ቢኾን ሐዘን ሁሉ ኀላፊ ነው
የነፍሳችን ናፍቆት አንተ ጋር መድረስ ነው
መቆጠር ከሕዝብህ መግባት ከኪዳኑ
በመንግሥትህ መኖር እያመሰገኑ

ግጥም፦ ገጣሚት ሐዊ ባልቻ
ዜማ፦ ዲ.ን ይሁንሰላም አስራት

.እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
     #ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏

    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

   ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot
👁 5.2 тыс. ❤ 25👍 8🥰 8 ↻ 63 19 октября