ግዕዝ ቋንቋ ለያሬዳውያን
https://t.me/lola766vipbot?start=_tgr_H-sVrps0N2E0
Статистика обновлена 15.11.2026 в 04:27 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?
Динамика за 30 дней
Истории пока нет. График появится после следующих обновлений статистики.
Рекламные публикации
Последние публикации
Все посты канала →በዕለቱም ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት 120 ኩንታል ጤፍ እና 300 ባለ 5 ሊትር ዘይት ድጋፍ ተደርጓል።
ድጋፉን ይዘው በቦታው የተገኙት፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ዲ/ን ንጉሤ ባለውጊዜ በበኩላቸው ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በሠው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ማኅበራዊ ቀውሶች ተጎድተው በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች ከፍተኛ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ አስታውሰው፣ በቀጣይም መሰል ጥቃቶች በደረሱባቸው የአርሲ ወረዳዎች ለሚገኙ ወገኖች እንዲሁም በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፎችን ማድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በመጨረሻም ወገኖቻችን ለመርዳት ማኅበሩ የሚያደርገውን ጥሪ በመቀበል በመላው ዓለም የሚገኙ አጋርና ባለድርሻ አካላት የተለመደ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
✝️ድጋፍ ለማድረግ፡-✝️
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
በአሐዱ ባንክ 0025393810901
በአቢሲንያ ባንክ 37235458
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000309803648
በወጋገን ባንክ 0837331610101
በአዋሽ ባንክ -01329817420400 እንዲሁም
በወገን ፈንድ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
✝️አለሁ_እኔ_ለአርሲው_ወገኔ! ✝️
🔷ድጋፍ ያደረጋችሁ ወገኖች የድጋፋችሁን መረጃ ለማሳወቅና በጋራ ለመንቀሳቀስ ወደ ቴሌግራም ግሩፓችን ይቀላቀሉ።
👇👇👇
🔗 የቴሌግራም ግሩፕ፦
https://t.me/MkArsiSupport
ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም
ብፁዕነታቸው ይህን የተናገሩት ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ ሽርካ ወረዳ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ተፈናቅለው በጎቤሳ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች አስቸኳይ የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ቤተሰቦቻቸውን ላጡ፣ ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሁም በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት “አለሁ እኔ ለወገኔ” በሚል ድጋፍ ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዚሁ መሠረት በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በጮሌ ቢርቦ ቀበሌ የተጎዱትን ጨምሮ ከወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች በደረሰው ጥቃት ለተፈናቀሉ ወገኖች በጎቤሳ ደብረ ሰላም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በመገኘት የመጀመሪያውን ዙር ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፉ ወቅት የተገኙት የአርሲና ሶማሌ ጅጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ “ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ እየተፈጸመ ያለውን ሃይማኖት ተኮር ጥቃት በሚዲያ ቀዳሚ ድምጽ በመሆኑ እንዲሁም ከዚህ በፊትም በአሰኮ እና በተለያዩ ቦታዎች ለተፈናቀሉት ድጋፍ በማድረግ ዛሬም አብረው በቦታው ድረስ በመገኘት በሚሊዮን ገንዘብ በማውጣት ለተጎጂዎች ድጋፍ ስለሰጡና ወደፊትም ለሚያደርጉት ምስጋና ይገባቸዋል” ብለዋል።