Телеграм

Aster Abebe Official

@asterabebe Блоги и блогеры
РКН: проверяем Не иноагент

Статистика обновлена 15.11.2026 в 04:29 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики10 638
Охват поста3 996 38% от подписчиков
ERR за месяц37,56%
ERR за 24 часа29,58%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Aster Abebe Official tg10 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
🥰ከዚህች ሰአት አድነኝ ልበልን?🤔 ወይ ጉኡኡኡኡኡኡኡኡኡድ
የተላኩት ለዛ ነው። ለዚህች ሰአት ነው የመጣሁት። ተወው በቃ አይነት ነገር
መከራ ካፈለቃቸው ፀሎቶች ወደ ፍቃዱን ማወቅ ያሸጋግረን አሜን 😍
አሜን
👁 3.1 тыс. ❤ 160🔥 21🙏 19 ↻ 15 3 ноября
Aster Abebe Official tg10 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ከሁለት ሳምንት በፊት ፀጉሬን ልሰራ ከአንዲት የፀጉር ባለሞያ ጓደኛዬ ቤት ጎራ ባልኩበት ተሰርቼ እስክጨርስ በሚል እናቴ ጋር face time ተደዋወልን። እንደፀጉር መሰራት ሚያሰለቸኝ ጉዳይ የለም እስ 😞እስ 😕 እህ 🥹 እያልኩ እየተመናቀርኩ ነው ተሰርቼ ምጨርሰው። ህመሙን እንዲያስረሳኝ የቆጥ የባጡን እያወራን በመሀል ካሜራውን ወደጓደኛዬ ዞር አደረኩና አስተዋወኳቸው። ይቺናት ይኸውልሽ ፀጉሬን ምትነጨኝ አልኳት አመድ-ኣፋሽ ሳደርጋት። እንደናት ቆጣ ብላ ቀስ ብለሽ ስሪያት አለቻት። ካልሆነ ተቆረጪው እሱም ያምርብሻል ብላ አስተያየትዋን ለኔ ጣል አድርጋ ጨዋታቸውን ቀጠሉ :: የመቆረጤን ጉዳይ ጓደኛይ ባትቀበለውም ለምን ካላችሁ ናፍቆትዋን ምትወጣው አልፎ አልፎ ፀጉሬን ልሰራ ስሄድ በላሳምርሽ ሰበብ ፀጉሬን በመንጨት ነዋ 🥰
ወሬው ቀጠለ .................

እናቴ: የየት ሰፈር ልጅ ነሽ

ጓደኛዬ ፤ አዋሳ 😍 አለች ትንሽ እየታበየች 🫣የአዋሳ ልጅ በመሆኗ 😍አዋሳ አብሮ መብላቱ ፣መጠጣቱ ፣ በር እኮ አይዘጋም 😍 የራበው የጠማው ሁሉ ገብቶ እንዲበላ እያለች ምንም እንኳን አዋሳን ባላውቃትም ግን ከአመታት በፊት ገና ከሀገሬ ሳልወጣ እግር ጥሎኝ በሄድኩበት ክፍለ-ሀገራት ሁሉ ያየሁትን የደግነት ጥግ ይቺ ምላችሁ ጓደኛዬ ለአዋሳ ብቻ አድርጋው ስታወራ እናቴ ቆጣ ብላ ተይ ተይ መሬት ያዢ አለቻት።
ለነገሩ ጓደኛዬ ላይ አልፈረድኩባትም ምናልባት አዋሳን ብቻ ይሆናል ምታውቃት ብዬ 🫣

እናቴ እርምትዋን ቀጠለች። የዛሬን አያድርገውና ሰው ሳይከፋፋ እንኳን የተራበን ማብላት ፣ ማደሪያ የሌለውን በር ከፍቶ የእግዜር እንግዳ በሚል መቀበል አይደለም አንድ እናት የሰፈሩ ልጅ ሁሉ እናት ነበረች። የጡትዋ ወተት የደረቀባት አራስ እናት ካለች ከራሳችን ልጆች ነጥቀን ጡታችንን ላልወለድናቸው ልጆች እናጠባ ነበር። ዛሬ ላይ መተማመን ጠፍቶ በራችንም ተዘጋ አጥራችንንም አስረዝመን አጠርን። መልካምነት የሁሉ ኢትዮጰያዊ መለያ ነው ብላ ከተማውን ከገጠሩ ቀላቅላ አንድ አድርጋ ገላገለችን። 😍
የገረመኝ ከእናቴ ቀጥሎ ያወራው የታላቅ ወንድሜ የቢኒያም አበበ ንግግር ነው።

ቢኒያም ፤- አሁን ገባኝ 😞

እናቴ ፤- ምኑ 🤔

ቢኒያም ፤-ያለፈ ያገደመ ሁሉ ወንድም እና እህቴ የሚመስለኝ ጉዳይ 😂

እናቴ ፤- አንተ ? ምን ልትል ነው ? አጠገቧ ጋደም እንዳለ ወሬውን ቀጠለ

ቢኒያም ፤- አዋ ! መንገደኛ ሁሉ እኔ የጠጣሁትን ጡት ጠጥተው ነው ለካ ወንድሞቼ የመሰሉኝ ብሎ እርፍ 🤓
👇🏽
ለቀልድ እንደሆነ ቢገባኝም የቢኒ ንግግር ውስጤ ግን ይህን ቀጥሎ ያሰላስል ጀመረ። ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ የመረጣቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኖዋል ...,. የሚለውን ቃል 🧐

የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን አንዱን እየሱስን ብትበላ እንመስለዉ ዘንድ ከተወሰነልን መልክ እንዲህ ባልራቅን ብዬ አሰብኩ። የቁመት ፣ የትከሻ ፣ የመቅላት እና የመጥቆር ጉዳይ ሳይሆን ባህሪው በኛ ሊገለጥ ባልቸገረን ብዬ እንደ እናቶቻችን ጡት ለአካሉም አንድ ምግብ አንድ ውሀ ተመኘሁ። እሱም እየሱስ ነው።
ጨዋታቸው ልመስለዉ ከተገባኝ እና አብ ከወሰነልኝ መልክ የራቀውን የመልኬን ጉዳይ አሳብቆብኛል።
አንድ አብልቶ አንድ አጠጥቶ አንድ ያድርገን እወዳችዃለው። 😍😍
👁 4.8 тыс. ❤ 142❤‍🔥 24👍 7 ↻ 11 31 октября