Телеграм

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

@housinginaddisababa Политика и экономика
РКН: проверяем Не иноагент
The interest of this Channel is giving continuous information about

Housing Projects | Real Estate | Property | Construction | Home Services.

**This page is not a gov't page.**

Статистика обновлена 15.11.2026 в 01:13 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики67 556
Охват поста18 897 28% от подписчиков
ERR за месяц27,97%
ERR за 24 часа15,85%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች tg67 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
#AddisAbaba

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስለ መኖሪያ ቤቶች ምን አሉ ?

" ቆጥበው የሚጠባበቁ ነዋሪዎቻችን አሉ። ... 14 ዓመት፣ 12 ዓመት፣ 20 ዓመት ድረስ የቆጠቡ ቆጣቢዎች እንዳሉ እናስተውላለን " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለረጅም አመታት ቆጥበው ቤት ያላገኙ ዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹ ኤኤምኤን ዘግቧል።

ከንቲባ አዳነች በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ቤቶች ለልማት ተነሺዎች እና ለቆጣቢዎች በዕጣ እንደሚተላለፉ ገልጸዋል።

ዛሬ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በመሆን በቅጠል ተራ የተሰሩ መኖሪያ ቤቶችን በጎበኙበት ወቅት በሰጡት ማብራሪያ ፤ " በጣም ለመኖር አስቸጋሪ የሆኑትን አንስተን ወደዚህ ደረጃ ቀይረን እነሱን መልሰን የምናስገባበት ነው፤ እያስገባንም ነው " ብለዋል።

" ሌላው ለቆጣቢዎች ዕጣ የሚወጣበት ቤት ነው። በተመሳሳይ እዛም እዚህም በከተማዋ በከፍተኛ የልማት ሂደት ውስጥ ስላለች የልማት ተነሺዎችም የሚገቡበት ይሆናል " ብለዋል።

ከተማ አስተዳደራቸው በማህበር የሚገነቡትንም እያገዘ እንዲጨርሱ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።

በአዲስ አበባ ያለውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረትና የዋጋ መጨመር ከግምት ውስጥ በማስገባት ከተማ አስተዳደሩ ያሉትን ችግሮች ታሳቢ ያደረገ የመፍትሄ እርምጃ እየወሰደ እንደሚቀጥል ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።

" እውነት ነው ከተማችን ላይ ከየትኛውም አካባቢ በላይ ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት አለ " ያሉት ከንቲባ አዳነች " ቆጥበውም የሚጠባበቁ ነዋሪዎቻችን አሉ። በሚሊዮኖች ሰው እንዲመዘገብና እንዲቆጥብ ሲደረግ በሚሊዮኖች ቤት አልታቀደም ነበር " ሲሉ አመልክተዋል።

" 14 ዓመት ፣ 12 ዓመት ፣ 20 ዓመት ድረስ የቆጠቡ ቆጣቢዎች እንዳሉ እናስተውላለን ፤ ይሄን ያክል በሰፊው እሱ ይቅር የዚህ ግማሽና ሩብ እየተሰራ ቢመጣ ኖሮ ሰው ይሄን ሁሉ ዘመን እየቆጠበ ቤት መጠባበቅ አይጠበቅበትም ነበር ፤ ሁለተኛ የቤትም ዋጋ በጣም ተቀይሯል ዛሬ ለዚህም አይዳረግም ነበር " ብለዋል።

" የተናግርነውን ፣ የጀመርነውን በፍጥነት የመጨረስ ትልቁ መመሪያችን ነው። ሁሉንም ቆጣቢ በፍጥነት በአንድ ጊዜ መመለስ ባንችልም እንኳን ከስር ከስር ምላሽ እየሰጠን ሌሎች ደግሞ አማራጮችን በማህበር ሆነው እንዲገነቡ እድል እየሰጠን የከተማችንን ነዋሪዎች ጥያቄ እየመለስን እንሄዳለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የቤት ግንባታዎች ተጠናክረው ስለሚቀጥሉ በ20/80 እና በ40/60 የቤት መርሃ ግብር እየቆጠቡ የሚገኙ ነዋሪዎች ቁጠባቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" ቁልፍ ስራችን የሚሆነው የቤት ግንባታ ስለሆነ አሁንም በቅርብ የምናስጀምራቸው አዳዲስ ቤቶች አሉ እንበርታ፣ በጋራ እንስራ ቁጠባችሁንም ጨምሩ በዚህ ዘመን ባለው የቤት ዋጋ ስለሆነ የሚተላለፈው ብዙውን መንግሥት ይደጉማል የተወሰነውን ያክል ባለቤቱ እራሱ መቻል ስላለበት እጅ ለእጅ ተያይዘን እናሳካዋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
👁 8.5 тыс. ❤ 37👍 12👎 8 💬 9 ↻ 20 вчера в 04:42
Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች tg67 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
Ethiopia is pushing ahead with an ambitious plan to build 1.5 million homes within five years, with Addis Ababa alone targeting 100,000 housing units across 21 construction sites.

The city’s Mayor, Adanech Abiebie, made the announcement following an inspection visit with Prime Minister Abiy Ahmed on Friday. Of the 100,000 units, 50,000 are being financed by the city administration, while the other 50,000 are being developed through public-private partnerships and housing cooperatives.

The leaders inspected 33 housing blocks in Tulu Dimtu and nine in Qetel Tera, Addis Ketema, where construction is progressing. The national housing commitment was announced by Abiy Ahmed at the Guba gathering in 2025.

#AfricaGlobalNews #Ethiopia #AbiyAhmed #HousingDevelopment #AddisAbaba
👁 7.1 тыс. ❤ 6👎 4🥰 1 ↻ 4 вчера в 04:39