Телеграм

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

@AAEQOCAA Общие новости и СМИ
РКН: проверяем Иноагент: проверяем
https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F

Статистика обновлена 15.11.2026 в 05:45 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики5 860
Охват поста720 12% от подписчиков
ERR за месяц12,29%
ERR за 24 часа7,88%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Открыть пост ↗
አካል ጉዳተኛ መምህራን በሙያ ብቃት ምዘና በተገቢው እንዲመዘኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ ተገለጸ
ልዩ የምዘና ስርዓቶች አካል ጉዳተኛ መምህራን በሙያቸው እኩል ተወዳዳሪና የሙያ እድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ ተጠቆመ።
(ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን  በመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክዋኔ የማህደር ምዘና ሂደት ውስጥ አካታችነትን ለማረጋገጥ አካል ጉዳተኞች የልዩ ፍላጎት መምህራን ልዩ ምዘና አካሄደ።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያከናውናቸውን የምዘና ተግባራት ለሁሉም አካላት ፍትሃዊና ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል በዚህም መሰረት መስማት የተሳናቸው መምህራን ያላቸውን የማስተማር ብቃትና የስራ አፈጻጸም ያለምንም እንቅፋት ማሳየት እንዲችሉ ተገቢው የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎችና ምቹ የምዘና ሁኔታዎች ተመቻችቶላቸው ምዘናውን እንዲወስዱ ተደርጓል።
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የቦሌ ቅ/ጽ /ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ግዛው ምዘናውን አስመልክቶ እደገለጹት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትምህርት ጥራትን ሲያረጋግጥ የአካል ጉዳተኛ መምህራንን ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በማስቀደም ነው በዚህም መሰረት አካል ጉዳተኛ መምህራን ባሉበት ቦታ ወደ ፎቅ ሳይወጡ መዛኞን በማምጣት እንዲመዘኑ ለአይነስውራን እና መስማት ለተሳናቸው ተመዛኞችም የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ በማምጣት እንዲሁም ልዩ ድጋፍ በማድረግ ምዘና ው እየተካሄደ እንዳለ ገልጸዋል ይህ ልዩ ምዘና መምህራኑ ያለምንም የመግባባት ችግር ብቃታቸውን እንዲያሳዩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
እንዲሁም አራስ እናቶች ህፃናት ልጆቻቸውን በመያዝ ወደ ምዘናው የመጡበት አግባብ ቢኖርም በምዘና አስተባባሪዎች አማካይነት  ቅድሚያ እንዲመዘኑ  በማድረግ  በተገቢው ሁኔታ  እንዲመዘኑ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል፡፡
ምዘናውን ከወሰዱ መምህራን በበኩላቸው በምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች ታግዘን ምዘናውን መውሰዳችን ሀሳባችንንና የስራ ልምዳችንን በነጻነት እንድንገልጽ ረድቶናል እንዲሁም የተደረገልን ትኩረትም የሚያስመሰግን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ይህ ልዩ ምዘና አካል ጉዳተኛ መምህራን በሙያቸው እኩል ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሙያ እድገት ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ተገልጿል።
👁 433 ↻ 1 вчера в 11:09
Открыть пост ↗
የሙያ ብቃታቸውን በምዘና ለማረጋገጥ ወደ ምዘና ስርዓቱ የሚቀላቀሉ መምህራን እና  የት/ቤት አመራሮች ቁጥራቸው በየግዜው እያደገ መሄዱ ተገለጸ
(ህዳር 5 ቀን2019ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት የመምህራን እና የት/ቤት አመራሮች ብቃት በምዘና ለማረጋገጥ የማህደር ተግባር ምዘና በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የምዘና ሂደቱን በመቃኘት እና ተመዛኞችን ለማበረታታት በምዘና ጣቢያ ላይ የተገኙት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የምዘና ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለልኝ ወንዴ ባስተላለፍት መልዕክት
የሙያ ብቃት ምዘናውን ለመመዘን እና ብቃታቸው ለማረጋገጥ የሚመጡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በየአመቱ ቁጥራቸው እየጨመረ እና ለምዘናው የሚሰጡት ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ከዚህ ባሻገር ምዘናውን የማለፍ ምጣኔ ያደገበት ሁኔታ መኖሩን ገልጽዋል፡፡
አብዛኛው መምህራን ብቃታቸውን ለማረጋገጥ የፁሑፍ ምዘና ወስደው ለማህደር ተግባር ምዘና መድረሳቸው ደስተኞች መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ ብቃታቸውን በማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣትዝግጁ መሆናቸውን ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ምዘናው የከተማው አብይ ኮሚቴ የተሳተፋበት እና ተመዛኞች ምዘናውን በተገቢው ሁኔታ እንዲመዘኑ መዛኞች እና አስተባባሪዎችም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ  እንዲወጡ ለማስቻል እና የማበረታታት ስራ የተከናወነበት ሁኔታ መኖሩን ጠቅሰው በዚህም ምዘናው ውጤታማ እንዲሆን ከትምህርት ቢሮ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰራበት አግባብ በመኖሩ ጠቅሰው ምዘናው በአግባቡ እየተካሄደ መሆኑን  አሳውቀዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአራዳና ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እጅጋየሁ አድማሱ   በበኩላቸው እንደገለጹት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ምዘናው በአግባቡ እና በተገቢው ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው  በተለይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መንፈስ የተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ምዘናው በ3ት የምዘና ጣቢያዎችን እንዲመዘኑ የተደረገበት አግባብ ሲኖር በተለያየ ምክንያት ምዘናውን ያልወሰዱ መምህራን የት/ቤት አመራሮች በቀጣይ በሚዘጋጀው መርሐግብር ላይ ተገኝተው እንደሚመዘኑ ተናግረዋል፡፡
የመምህራን ሙያን በምዘና ማረጋገጥ ብቁ ተወዳዳሪ ዜጋን ለመፍጠር ወሳኝነት ስላለው በምዘናው ላይ ያልተሳተፍ መምህራን በተያዘው በጀት አመት በሚደረገው ምዘና ላይ  የሙያ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ለዝህም ከወዲሁ የተለያዩ የግንዛቤ መስጠት ስራን በመስራት መምህራንን የመመዝገብ እና የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጽዋል ፡፡
የኢትዩጰያ እና የአዲስ አበባ የወላጆች ማህበር ሊቀመንበር አቶ ሀሰን ሺፋ ምዘናውን አስመልክቶ እንደገለጹት የመምህራን የሙያ ብቃት ምዘና  የትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተዕፅኖ ያለው በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ መሄድ አለበት ብለዋል፡፡
ለተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እና የመማር ማስተማር ሂደቱ  በተገቢው የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ለማስኬድ በየግዜው የሚካሄዱ ምዘናዎች ጠቃሚ መሆናቸው ገልጽው  መምህራን በዚህ ሂደት ላይ ተሳትፎአቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በምዘና ጣቢያ ላይ ምዘናውን ሲከታተሉ ያገኘናቸው የዘርፍ ባለድርሻ አካላት እንደገለጹት በየትምህርት ቤቱ ብቃት ያለው መምህር እንዲኖር እና ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ዋንኛው የሙያ ብቃት መረጋገጥ መሆኑን ጠቁመው የማስተማር ስነ ዘዴን ከእውቀት ጋር አቀናጅቶ ለማስተማር እና ተማሪዎች ተገቢውን እውቀት እንዲያገኙ ለማስቻል ብቃታቸው በምዘና የተረጋገጠ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ማፍራት የሚያስፈልግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የሙያ ብቃት ምዘና መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች  ያሉበትን የእውቀት ደረጃ በማወቅ እና በራሳቸው እንዲተማመኑ የሚያስችል  በመሆኑ ሁሉም በምዘናው ሂደት ላይ እንዲያልፍ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
👁 356 вчера в 10:50
Открыть пост ↗
የዜና ቻናል የሆነው (CMN) በአዲስ አበባ የቤት ችግርን ለመፍታት በተያዘው ዕቅድ 100 ሺ ቤቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን በሰበር ዜና ዘግቧል፡፡

የዜና ቻናል የሆነው (CMN) በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ በአምስት ዓመታት ውስጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት በተያዘው ሀገራዊ ዕቅድ መሠረት በ21 ሳይቶች የ100,000 ቤቶች ግንባታ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ በሰበር ዜና ዘገባው ለአለም አስነብቧል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ በመገንባት ላይ ከሚገኙ ቤቶች መካከል ግማሽ ያህሉ በከተማ አስተዳደሩ በጀት የሚሸፈን ሲሆን፣ ቀሪው ደግሞ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት እንዲሁም በቤት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት እየተገነባ እንደሚገኝ በዘገባው ገልፃል፡፡

በተለይም ቱሉ ዲምቱ እና ቅጠል ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢዎች የሚካሄዱት እነዚህ ፕሮጀክቶች በመዲናዋ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ዘግቧል።
👁 323 вчера в 10:26