Телеграм

"ኡማ ቲቪ " Tv

@EthioomahTvchannle Религия и эзотерика
РКН: проверяем Иноагент: проверяем
ለበለጠ ወቅታዊ መረጃወችን ለማገኘት
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

Статистика обновлена 15.11.2026 в 05:02 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики44 488
Охват поста5 271 12% от подписчиков
ERR за месяц11,85%
ERR за 24 часа10,13%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
"ኡማ ቲቪ " Tv tg44 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ወንድማችንን ሙራድ ታደሰን ደሴታውያን የሚጠሉት እውነቱን ሳይደብቅ፣ እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ስለሚናገር ነው። እውነትን ለመናገር ድፍረት፣ ለመቆም ጀግንነት ይጠይቃል። ሁሉም ሰው የሚያስደስተውን ሲናገር እርሱ ግን ያመነበትን በድፍረት የሚናገር ወንድማችን ነው።
እርሱ አንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን፣ ግዙፍ ተቋም ነው!
ጀግንነት በጩኸት ሳይሆን በአቋም ነው። በጫና ጊዜ አለመንበርከክ፣ በተቃውሞ መካከልም ድምፅን አለማጥፋት ነው። ሙራድ ያንን ድፍረት ያሳየናል።
አላህ እርሱንና ቤተሰቡን ይጠብቅልን።

ወንድም ሙራድ ታደሰ በርታ አላህ ይገዝህ ወንድማችን ይዞት የተነሳው አጀንዳ እውነትን ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ መረጃ ነውና ሁላችንም ከሱ ጎን መቆም አለብን ።
👁 1.9 тыс. 👍 109💯 42❤ 10 💬 17 ↻ 4 вчера в 18:48
"ኡማ ቲቪ " Tv tg44 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የሳውዲ አቪዬሽን ለሐጅ እና ኡምራ ተጓዦች አገልግሎት መሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

​የሳውዲ አረቢያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን (GACA) ፕሬዝዳንት አብዱል አዚዝ አል-ዱአይሌጅ እንዳስታወቁት፤ በፕሪንስ መሀመድ ቢን አብዱልአዚዝ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (መዲና) እየተከናወነ ያለው መጠነ ሰፊ የማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ የአየር ማረፊያውን ዓመታዊ የተጓዦች አቅም ከነበረበት 8 ሚሊዮን ወደ 18 ሚሊዮን ከፍ እንደሚያደርገውና በጥር 2027 ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል። ይህ ፕሮጀክት የሐጅ እና የኡምራ እንግዶች የሚደርስባቸውን የትራንስፖርትና የአገልግሎት ጫና በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፣ የሐጅ አገልግሎት ፕሮግራም ግቦችን እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።

​በተጨማሪም ባለፈው ዓመት 52 ሚሊዮን ተጓዦችን በመቀበል አዲስ ክብረ ወሰን ያስመዘገበው የጂዳው ንጉሥ አብዱልአዚዝ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሐጅ ተርሚናሎችን አቅም ወደ 16 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ ሰፊ የልማት ሥራዎች እያከናወነ ይገኛል። የሐጅ እና የኡምራ ተጓዦች አየር ማረፊያ ውስጥ ረጅም ሰዓት እንዳይጠብቁ ለማስቻል "ከቦርሳ ነፃ የሆነ ተጓዥ" መርሃ ግብር ከአራት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ እንግዶች አገልግሎት የሰጠ እንደሚገኝ የጋካ ባልስልጣናት አስታውቀዋል። ይህም ዘመናዊ ኤሌክትሮኒክ በሮች እና ስማርት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የፓስፖርት ቁጥጥር ሂደቱን ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ የሚያስችል ፈጣን አሰራር መዘርጋቱን ባለስልጣናቱ አክለዋል።
👁 2.5 тыс. ❤ 7 ↻ 1 вчера в 17:35
"ኡማ ቲቪ " Tv tg44 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ በግቢው ውስጥ በሙስሊሞች ላይ አድሎአዊ አሰራር መኖሩን አረጋገጠ

​የካናዳ ታዋቂው የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ በካምፓሶቹ ውስጥ በሙስሊሞች፣ በአረቦች እና በፍልስጤማውያን ላይ ያነጣጠረ አድልዎ መኖሩን በይፋ አረጋግጦ ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታትም ቁርጠኝነቱን ገልጿል። ይህ እውቅና የተሰጠው ከዩኒቨርሲቲው የሙስሊም፣ አረብ እና ፍልስጤማውያን አድልዎ መርማሪ ቡድን የቀረበውን ሰፊ የ300 ገጽ ሪፖርት መነሻ በማድረግ ሲሆን፤ ሪፖርቱ በግቢው ውስጥ ሙስሊሞች ከመጠን በላይ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ፣ በቂ ጥበቃ እንደማይደረግላቸው እና በምርምርና አክቲቪዝም ስራዎቻቸው ሳቢያ የንቀት ቃላት፣ የቫንዳሊዝም ድርጊቶች እና የመስመር ላይ እንግልት እንደሚደርስባቸው አጋልጧል።

​ዩኒቨርሲቲው የቀረቡትን "አንዳንድ ምክረ-ሀሳቦች ከአካዳሚክ ነፃነት ጥበቃ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው ሙሉ በሙሉ አልቀበልም " ቢልም፣ የተነሱትን ስጋቶች ለመቅረፍ ወዲያውኑ ሊወሰዱ የሚችሉ በርካታ እርምጃዎችን ይፋ አድርጓል። ከእነዚህም መካከል በአለም አቀፍ ግጭቶች የተጎዱ ተማሪዎችን በገንዘብ ለመደገፍ ጥረት ማድረግ፣ ከእነዚህ ማህበረሰቦች ጋር የተያያዙ አካዳሚክ ምርምሮችን ማጠናከር እና የካምፓሱን ሰላምና እኩልነት ጉዳዮች ለመከታተል የሙስሊም ማህበረሰብ አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋም የሚሉ ስራዎች እንደሚገኙበት ተመላክቷል።
👁 2.5 тыс. ❤ 9👍 3 вчера в 17:34