Телеграм

ትምህርት መረጃ( academic info)

@academic_info Высшее образование и курсы
РКН: проверяем Не иноагент
@ትምህርት መረጃ( academic info)
Telegram: https://t.me/academic_info
Facebook: https://www.facebook.com/share/1EqNsbE4CN/
email: accadamicinfo@gmail.com
Instagram:https://www.instagram.com/academicinfor?igsh=ZW8xc2J0MXdxdDVj
Mobile 09725443......

Статистика обновлена 15.11.2026 в 11:38 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики11 522
Охват поста5 580 48% от подписчиков
ERR за месяц48,43%
ERR за 24 часа19,04%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
ትምህርት መረጃ( academic info) tg11 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራር ቦታዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች እንዲሸፈኑ ተደነገገ።

• የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች የአገልግሎት ዘመን በአምስት ዓመት እንዲገደብ የተወሰነሲሆን ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ በውድድር ያላለፉ አመራሮች የመምህርነት ደረጃ ዕድገትና ጥቅማጥቅማቸው ተጠብቆ ወደ ማስተማር ይመለሳሉ።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

የትምህርት ሚኒስቴር አዲሱን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተከትሎ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች የሚመረጡበትንና የሚመደቡበትን አዲስ አገር አቀፍ መመሪያ አውጥቷል።

መመሪያው የሥራ ተነሳሽነት፣ ብቃትና ልምድ ያላቸው አመራሮች ትምህርት ቤቶችን እንዲመሩ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ዓላማ ያደረገ ሲሆን፣ የምልመላ ሂደቱ በልዩ ወረዳ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ፣ በዞን ወይም በክልልና ከተማ አስተዳደር የትምህርት መዋቅሮች እንደሚከናወን ደንግጓል።

በተጨማሪም በትምህርት ቤት አመራርነት ተመልምሎ የተመደበ ማንኛውም አመራር የአገልግሎት ዘመኑ 5 ዓመት እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ከ5 ዓመት ቆይታ በኋላ ለተመሳሳይ መደብ በድጋሚ ተወዳድሮ ማለፍ ካልቻለ ወደ መምህርነት ተመድቦ አቻዎቹ የደረሱበት የደረጃ ዕድገትና ጥቅማጥቅም እንደሚጠበቅለት ተመላክቷል።

እንደ አዲሱ መመሪያ ድንጋጌ ለርዕሰ መምህርነት ለመወዳደር በቅድመ አንደኛ ደረጃ ቢያንስ ዲፕሎማ፣ ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) በትምህርት አመራር ወይም በመምህርነት የትምህርት መስክ ማግኘት ግዴታ ተደርጓል።

በደረጃ ዕድገት በኩልም አመልካቾች በመምህራን የደረጃ መሰላል መሠረት "ከፍተኛ መሪ መምህር" ደረጃ የደረሱ መሆን የሚጠበቅባቸው ሲሆን ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች፣ በልማት ወደኋላ በቀሩ ወይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች ግን ዝቅተኛው መስፈርት "ተባባሪ መሪ መምህር" እንዲሆን ተወስኗል።

በምክትል ርዕሰ መምህርነት ለመወዳደር በዲሲፕሊን ያልተቀጣ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ እና በትምህርት ክፍል ኃላፊነት፣ በፈረቃ፣ በሥርዓተ ትምህርት ወይም በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) አስተባባሪነት ቢያንስ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ማሟላት ይጠበቃል።

የደረጃ ዕድገትን በተመለከተም መደበኛ ተወዳዳሪዎች "መሪ መምህር" በአስቸጋሪና አርብቶ አደር አካባቢዎች ደግሞ ቢያንስ "ከፍተኛ መምህር" ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለባቸው በመመሪያው ተደንግጓል።

በሱፐርቫይዘርነት እና በከፍተኛ ሱፐርቫይዘርነት የሥራ መደቦች ላይ ለመመደብ በርዕሰ መምህርነት ወይም በምክትል ርዕሰ መምህርነት ያገለገሉ ባለሙያዎች የሚወዳደሩ ሲሆን፤ ለከፍተኛ ሱፐርቫይዘርነት በሱፐርቫይዘርነት ቢያንስ የሁለት ዓመት ወይም በርዕሰ መምህርነት የአራት ዓመት አገልግሎት ማሳየት የግድ ይላል።

የዕጩ አመራሮች የውድድር ሂደት የመጨረሻዎቹ ሁለት ተከታታይ ዓመታት (የአራት ሴሚስተር) አማካይ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ቢያንስ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል።

የውድድር ነጥብ አያያዙም የቴክኒክና የባሕርይ ብቃት ምዘና 60 በመቶ (በቅድሚያ ከፈተናው 80% እና ከዚያ በላይ ያመጡ ብቻ የሚያልፉበት)፣ የትምህርት ቤት መሻሻል ዕቅድ ዝግጅት 20 በመቶ እንዲሁም የዕቅድ ገለጻና ቃለ-መጠይቅ 20 በመቶ ሆኖ በአጠቃላይ ከ100 በመቶ እንደሚሰላ ተደንግጓል።

ከነዚህ ሂደቶች በኋላ ከአጠቃላይ ውጤት 70 በመቶ እና ከዚያ በላይ ካስመዘገቡት መካከል አብላጫ ነጥብ ያመጣው ተመድቦ ወደ ሥራ ይሰማራል።

መመሪያው የሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማበረታታት ልዩ ድጋፍ ያካተተ ሲሆን፤ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአመራር ቦታዎች (ርዕሰ መምህርና ምክትል ርዕሰ መምህር) ሙሉ በሙሉ በሴቶች እንዲሸፈኑ ወስኗል፤ ሴቶች በማይገኙበት ሁኔታ ብቻ ወንዶች እንዲሳተፉ ይደረጋል።

በተጨማሪም ወንድና ሴት ተወዳዳሪዎች በእኩል ውጤት ካጠናቀቁ ቅድሚያው ለሴት ተወዳዳሪ እንደሚሰጥ በግልጽ ሰፍሯል።

የአመራር ምልመላና ምደባውን በበላይነት የሚመራና ሰባት አባላት ያሉት "የምልመላና ምደባ ኮሚቴ" በየደረጃው እንዲቋቋም የተወሰነ ሲሆን፣ የመምህራን ማኅበር ሁለት ተወካዮች (አንዷ ሴት የሆነች) በኮሚቴው ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል።

በውድድሩ ቅሬታ ያለው ማንኛውም አመልካች ውሳኔውን ባወቀ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለሲቪል ሰርቪስ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን በጽሑፍ የማቅረብ መብት የተሰጠው ሲሆን የተሰጠውን አስተዳደራዊ ውሳኔ ያልተቀበለ አካል ጉዳዩን ለሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት በይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል ተመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ህዳር 2 ቀን 2019 ዓ/ም
👁 2.2 тыс. 👍 6👎 5 💬 6 ↻ 39 11 ноября
ትምህርት መረጃ( academic info) tg11 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ሠራተኞች በስራ ላይ ለመቆየት ተመዝነው ቢያንስ 70% ማምጣት አለባቸው ተባለ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞችን በባህሪ፣ በክህሎት እና በተግባር ለመመዘን የሚያስችሉ 18 መመሪያዎችን ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

በአዲሱ አሰራር መሰረት፦

📌 በሶስቱም መመዘኛዎች ከ90% በላይ ላመጣ ሰራተኛ የሁለት እርከን፣ ከ75%–90% ላመጣ ደግሞ የአንድ እርከን ጭማሪ ይደረጋል።

📌ማንኛውም ሰራተኛ በያዘው መደብ ላይ ለመቆየትም ሆነ ለማደግ በመመዘኛዎቹ ቢያንስ 70% ማምጣት አለበት።

📌 ምዘናውን ለሚያልፍ ሰራተኛ የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ለ5 ዓመታት ያገለግላል። ፈተናውን ያላለፈ ሰራተኛ ተቋሙ በ6 ወር ውስጥ አዘጋጅቶ ድጋሚ የማፈተን ግዴታ አለበት።

ኮሚሽኑ ምዘናው ሰራተኛን ለማባረር ሳይሆን የሰራተኞችን ብቃት ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጻል።
መረጃው የሸገር ኤፍ ነው
👁 3.8 тыс. 👍 6 💬 4 ↻ 21 8 ноября
ትምህርት መረጃ( academic info) tg11 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ማንኛውም ተቋም የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት የቀጣይ ዓመት የአዲስም ሆነ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድን የሚከለክል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለአስተያየት ክፍት ተደርጓል።

• በመመሪያው መሰረት ከበጋው ትምህርት ውጪ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሰበብ መደበኛውን ስርዓተ ትምህርት ማስተማር የተከለከለ ሲሆን ፤ ማጠናከሪያ ወይም የክረምት ትምህርትን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማራቅ፣ ለፈተና እንዳይቀመጡ ማድረግ ወይም ምዝገባ መከልከልም አይቻልም።

አአ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን፣ ፍትሃዊነትንና ተገቢነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ወጥ የሆነ አሰራርና ተጠያቂነትን ለመዘርጋት ያስችላል ያለውን "የአጠቃላይ ትምህርት የእውቅና ፍቃድና እድሳት አሰጣጥ መመሪያ (ረቂቅ)" አዘጋጅቶ በትምህርት ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጥባቸው ክፍት አድርጓል።

ረቂቅ መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በሚገኙ የመንግሥት፣ የግል እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ብቻ ሳይወሰን በርቀት ትምህርት፣ በማጠናከሪያ ትምህርት (ቲቶሪያል)፣ በመሰረታዊ ቋንቋ ማሰልጠኛዎች እና በማማከር አገልግሎት ላይም የሚተገበር ነው።

እንደ ረቂቅ መመሪያው ድንጋጌ፣ የትምህርት ተቋማት እውቅና ፈቃድ ለ2 ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን እድሳቱም በየሁለት ዓመቱ የሚከናወን ይሆናል።

አዲስ ለሚቋቋሙ ተቋማት የሚሰጠው የቅድመ እውቅና ፈቃድ ደግሞ የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ይኖረዋል።

የቅድመ አንደኛ፣ የአንደኛ ደረጃ (1ኛ-6ኛ ክፍል)፣ የመካከለኛ ደረጃ (7ኛ-8ኛ ክፍል) እና የማጠናከሪያ ትምህርት ፈቃድና እድሳት በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች በኩል ይሰጣል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (9ኛ-12ኛ ክፍል)፣ የቋንቋ ማሰልጠኛዎች፣ የርቀት ትምህርት እና የማማከር አገልግሎቶች እውቅና ፈቃድና እድሳት ደግሞ በማዕከል በትምህርት ቢሮው ደረጃ ይሰጣል።

የትምህርት ተቋማት እንደ አገልግሎት ዘርፋቸው በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ብቻ ማመልከት እንዳለባቸው ረቂቁ ደንግጓል።

በዚህም መሠረት ለአዲስ አጠቃላይ ትምህርት ተቋም የቅድመ እውቅና ማመልከቻ ከመጋቢት 1 እስከ ሚያዝያ 30፣ ለእውቅና እድሳትና እርከን ማሳደግ ከየካቲት 1 እስከ መጋቢት 30 ድረስ ብቻ በአካል ወይም በበይነ-መረብ ማመልከት ይቻላል።

የርቀት ትምህርት ለአንደኛ ወሰነ ትምህርት ከግንቦት 1 እስከ ሰኔ 30፣ እንዲሁም ለሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ከኅዳር 1 እስከ ታኅሣሥ 30 ድረስ ማመልከቻዎችን ይቀበላል።

የቋንቋ እና የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ደግሞ አገልግሎቱን ከመጀመራቸው 1 ወር አስቀድመው ማመልከት አለባቸው።

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያላመለከተ ተቋም አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችል ተመላክቷል።

አዲስ የሚቋቋሙ ተቋማት የቅድመ እውቅና ፈቃድ ለማግኘት ከተቀመጠው ስታንዳርድ ቢያንስ 85 በመቶ ማሟላት አለባቸው፤ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ቀሪውን 15 በመቶ አሟልተው 100 በመቶ ሲደርሱ ሙሉ እውቅና ያገኛሉ።

በመጀመሪያው ዙር ምዘና 100 በመቶ ያሟላ ተቋም ግን በቀጥታ ሙሉ እውቅና ይሰጠዋል።

በረቂቁ ድንጋጌ መሰረት የተሟላ እውቅና ፈቃድ እና እድሳት የሚሰጠው መመዘኛዎቹን 100 በመቶ ለሚያሟሉ ተቋማት ብቻ ነው።

ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ብቻ የተቋቋሙ ማዕከላት ግን የእውቅና እና የእድሳት ፈቃድ ለማግኘት ከተቀመጠው ስታንዳርድ ቢያንስ 65 በመቶ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው በረቂቁ ተመላክቷል።

ምዘና ተካሂዶ ውጤቱ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚገለጽ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር ያላሟሉ ተቋማት በ30 ቀናት ውስጥ ክፍተታቸውን አርመው ለአንድ ጊዜ ብቻ ዳግም እንዲመዘኑ ይደረጋል።

እንዲሁም ተቋማት ባስመዘገቡት ግብዓት መሠረት እየሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከኅዳር 1 ጀምሮ ድህረ-እውቅና ምዘና ይካሄዳል።

የትምህርት ተቋማት ስለሚሰሩበት ግቢ እና ሰነዶች በተመለከተም ተቋማቱ በራሳቸው ግቢ የሚሰሩ ከሆነ የተረጋገጠ የይዞታ ካርታ ማቅረብ አለባቸው።

የራሳቸው ሕንፃ የሌላቸው ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ለሁለት ዓመት የትምህርት ዘመን የሚቆይ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የኪራይ ውል እና የይዞታ ካርታ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ይዞታቸው ካርታ የሌለው ከሆነ ለአንድ ጊዜ እድሳት ብቻ የሚያገለግል የባለቤትነት የመሬት ይዞታ ደብተር ወይም ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

በተጨማሪም የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ባለሙያዎች በመምህርነት ሙያ ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እና ቢያንስ የአምስት ዓመት የማስተማር ልምድ ሊኖራቸው ይገባል።

የርቀት ትምህርት ተቋማትም የተማሪዎች የፊት ለፊት ገለጻና የቤተ-ሙከራ አገልግሎት የሚሰጡበትን ቦታ ከትምህርት ቤቶች ጋር ውል ገብተው ማቅረብ እንዳለባቸው ተደንግጓል።

ተቋማት ተማሪዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የመቀበል ግዴታ ያለባቸው ሲሆን አማካይ ውጤትን፣ የባህሪ ሪፖርትን፣ ደረጃን ወይም የቅድመ ቅበላ ፈተናን መሠረት በማድረግ በተማሪዎች ላይ ቅድመ ሁኔታ መጣል አይቻልም።

ፆታን፣ ሃይማኖትን፣ ብሔርን፣ ማህበራዊ መሠረትን፣ ፖለቲካዊ አመለካከትን ወይም የልዩ ፍላጎት ሁኔታዎችን (አካላዊ፣ አእምሯዊና ስነ-ልቦናዊ) መነሻ በማድረግ መከልከልም ሆነ አድሎ መፈጸም በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ማንኛውም ተቋም የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት የቀጣይ ዓመት የአዲስም ሆነ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድ አይችልም ይህን ጥሶ የተገኘ ተቋም ምክርና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ካላስተካከለ ለ1 ዓመት እውቅና ፈቃዱ ይታገዳል።

ማጠናከሪያ ትምህርት በወላጆችና ተማሪዎች ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆን አለበት ተብሏል።

ከበጋው ትምህርት ውጪ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሰበብ መደበኛውን ስርዓተ ትምህርት ማስተማር የተከለከለ ሲሆን፤ ማጠናከሪያ ወይም የክረምት ትምህርትን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማራቅ፣ ለፈተና እንዳይቀመጡ ማድረግ ወይም ምዝገባ መከልከል እንደማይቻል መመሪያው አስቀምጧል።

ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ/ም
👁 4 тыс. 👍 2 💬 1 ↻ 6 6 ноября