Телеграм

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

@Tsion_liboled Литература и писательство
РКН: проверяем Не иноагент
የጥበብ አፍቃሪ ኖት እንግዲያውስ ትክክለኛውን ቻናል አግኝተዋል። በቻናላችን 👉 በኔና በሌሎች የተፃፉ
👉ግጥሞች🌸
🌹ወጎች 🌸
🌹ልቦለዶች 🌸
አዝናኝ አስተማሪ ታሪኮችና ሌሎች ፅሁፎችን ያገኛሉ...

━━━━━━━━ ✦
ለማንኛውም አስተያየት
@itsmetsita
Paid Promotion
@Tsiyon_awit
ይጠቀሙ።

Join us
@Tsion_liboled

Статистика обновлена 15.11.2026 в 03:29 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики7 731
Охват поста1 912 25% от подписчиков
ERR за месяц24,73%
ERR за 24 часа10,99%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘 tg7.7 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ህይወት ግን ከወሲብ ትበልጣለች? ሲኦልና ገነት  በወንድና በሴት መሀል ያሉ ይመስለኛል! ማናቸው በማን ጎን እንዳሉ አላውቅም እንጂ...

መኩሪያዬ መሰላል ነው.. አለ አይደል ከመሬት እስከ ሠማይ የሚደርሰው የያዕቆብ መሰላል ያለ?

እነሆ አለምኩ... መኩሪያዬ መሰላል ሁኖ ከማህፀኗ ሲላተም ከነፍሴ የሚመነጩ ስሜቶቼ ወደማህፀኗ ይወጡና ይወርዱ ነበር...

ወዳጄ ምን ነበር ሲኦል? ምንድነው ገነት? የሚያስብል መናጠብ ካጥንትህ ሲፈልቅ ይሰማሀል...

ሜሮን ምሽት ቤት በምዘፍንበት ቀን ሁሉ አያታለሁ... ልክ እንደሆቴሉ ሰራተኛ ሁሉ ሰላምታ መለዋወጥ ጀምረናል...

ድምፅህ ያምራል መቶም ሁለት መቶም ቲፕ.. የዘፈን ምርጫዎችህን ወድጃቸዋለሁ አምስትም አስርም (ሺህ ነው ደግሞ እሺ ዜሮዎች አሉት)  ቲፕ... ሜሪ ግን ወድጄሀለሁ ውበቷን ቲፕ.. ፈገግታዋን ቲፕ... 

ጓደኞች የሏትም.. ብቸኛ ነች... ማንም ሰው በአደባባይ እንድትኮራና እንድትደሰት አድርጓት አያውቅም... ታዲያ እኔ ቲፔን ማግኘት የለብኝም ትላላችሁ?

"ሜሪዬ.. የሕይወቴ ነፍስ.. መፅሐፉ ሰውን በአምሳሉ ፈጠረ ይል አይደል እንዴ? አንቺን የፈጠረች.. አምሳሏ የሆንሽላት ውብ እግዜርማ አለች!" የምትል ከጥቅስ የበዛች ከአንቀፅ ያነሰች.. ጋሽ ስብሀት ሜም የሆነች ደብዳቤ ፅፌ ማስቲካ በሚሸጠው ትግሬ ፈልፈላ ላኩላት...

በቀጣዬ ቀን ትናት ደብዳቤ የተሰጣት ቦታ በዛው ስአት መጣች መነፅር አድርጋለች.. ይገባኛል ከመነፅሩ ጀርባ ዓይኖቿ የደብዳቤውን ባለቤት ፍለጋ እንደሚንከራተቱ... እኔ ግን ውበቷ እንዳፈዘዘኝ ነበር " መነፅሩ ደግሞ የበለጠ አሳምሯታል" አለ ልቤ

"ዝበል ባክህ ዋቲያም ከአልጋህ እስክትወጣማ አይደለም መነፅር ዘንዶ ብታይባት ቆንጅታለች ከማለት አትመለስም!" ይላል አእምሮዬ... ከዛ እሰይ ተባብለው ይሁን ወይም በዛች ውብ ሴት ተገዳድለው እንዴት ወሬያቸው እንደሚያልቅ አላውቅም...

ብዙ አጫጭር ደብዳቤዎችን ላኩላት... ቢጨንቃት ለልጁ እሷም ደብዳቤ ሰጠችው

"ለእሷ እንዳለችህ መጀመሪያ ይሄንን አንብብ.." ብሉ ደብዳቤዎችን አሸከመኝ...

"እነዚህ ሁሉ ለፃፍክልኝ ደብዳቤዎች ምላሽ የሰጠሁት ናቸው... አንተ ግን ክፉ ነህ.. አባባን ይንሳኝ ክፉ.. ሳላውቅህ.. ሳልወድህ ትናፍቀኛለህ... ፍቅርህ ሳይሆን ናፍቆትህ ሊገድለኝ ነው.. ደግሞ አፈቀረችኝ ብለህ አንዳታስብ መናፈቅ ብቻ ነው..." የሚል አለበት።

ታዲያ ከሌሎቹ ምን አለኝ? ሰብስቤ የቆሻሻ ባስኬት ውስጥ ከተትኳቸውና ሶፋዬ ላይ ጋደም አልኩ... እንቅልፍ እስኪወስደኝ ድረስ በሀሳብ ተናጥኩ...

ምን ይሆን እነዛ ደብዳቤዎች ውስጥ የፃፈችው? ላንብባቸው እንዴ?

ኧረ ወደዛ ተወው.. በቃ መስማት የምትፈልገውን በመጀመሪያ ደብዳቤ አነበብ አይደል እንዴ? እንዲሁ የግራና የቀኝ አእምሮዎቼ ሲፋጠጡ ተመስጬ እንቅልፍ ይወስደኛል....

"ዓይንሽ ስር እኮ ነኝ! አንቺ ግን አታይኝም... ከእይታሽ ለመግባት ዛሬ ማታ ለየት ያለ ነገር አደርጋለሁ..." የምትል ደብዳቤ በፈልፈላው ላኩላት...

አትገርምም ቁልጭ ያለ የእራት ልብስ የምታምር ቀይ ቦርሳ ጣል አድርጋባት መጣች... የእራት ቀጠሮ ያለባት እንጂ እኔን ለማየት እንደዛ የተሽቀረቀረች አልመሰልህ አለኝ።

እንዲሁ እንደተማረኩ መድረኩ ላይ ወጣሁ...

እየዘፈንኩ በመሀል ከመድረኩ ወረድኩ ወደእሷ እየተራመድኩ መዝፈኔን ቀጠልኩ....

"የከፋው ይመስል ሆዴ...
ይባባል አይችል በዘዴ!

call all አሁን ደውል..
ሹክ ሹክ የመውደድ አመል! (ስልኬን አውጥቼ መነካካት ጀመርኩ... ሰዎቹ በድርጊቴ ተገርመው እያዩኝ ነው)

እናውጋ ልደውልና..
ቀልቤ ልቤ ካንቺው ነውና... (ስልኬን ሰጠኋት... እሷም 09 ተብሎ የተጀመረውን ስታይ በጣም በፍጥነት ስልክ ቁጥሯን ፅፋ ስልኬን መለሰችልኝ... ሰው ሁሉ በጭብጨባና በፊጨት አደመቀልኝ)

ቤቢ ቤቢ...." እየዘፈንኩ የማስበው ፊቷ ላይ ስላየሁት ስሜት ነው...

ከደስታዋ አብዛኛው ኪሎ የረገፈባት መሠለኝ... ዘፍኜ ስጨርስ ፈለኳት ዓይኖቼ እሩጠው እሩጠው ቢያጧት ተጣድፌ ከሆቴሉ ወጣሁ...

ቀን ቀን በረንዳው ላይ ቡና የምታፈላዋ ሴትዮ ረከቦቷን የምቻስቀምጥበት ጣውላ ላይ ቁጭ ብላ እያለቀሰች ነበር...

"ሜሪዬ ተራ የጭፈራ ቤት ዘፋኝ ሁኜ ሳለሁ አጉል ተዳፈርኩሻ ይቅርታ ስትስቂልኝኮ ልቤ ተሸነፈብኝ ምን ላርግ ፍቅርሽ ማንነቴን አስጠፋኝኮ ለዛ ነው መዳፈሬ ይቅርታ" አልኳት

"አይደለም አሴ.. አይደለም! ማንም ሰው እንዲህ ባደባባይ...."

"ይገባኛል ሜሪዬ...." ተቃቀፍን ተሳሳምን ተሳሳምን እነሆ የወሲብ ቀን ዛሬ ናት ስአቲቱም አሁን ናት የተባለ ይመስል እጄን ያዛ ልቧን ይዤ ከፊቴ እየሮጠች እየተጎተትኩ ሄጄ አልጋ ላይ ተሳፈርን...

አልነው አልነው አልነው... እኔና እሷ ብቻ ሳንሆን አልጋው.. አንሶላ.. ትራሱ.. ሳይቀሩ ነው የረኩት... አንሶላ ጓዳ ትራሱ ምናምን ጨለማው ቤት አምጣልኝ አለኝ አንቺን ምናምን ብለው ሲዘፍኑለት አይገባኝም ነበር ለካ የለመዱትን ለምደው ነው...

ወንድ ልጅ አንዴ ነው የሚያፈቅረው..እኔ ደግሞ አንዴ ወሲብን አፍቅሬያለሁ እንጂ እቺማ የልጆቼ እናት ነበር መሆን ያለባት...

እንግዲህ ምን ላድርግ ስልኳን በተቀበልኳት ቀን በአንድ ብርጭቆ ወይን አልጋዬ ላይ ያውም ወደገዛ ቤቴ አሯሩጣ ወስዳኝ ከተጋደመችልኝ ምን ቀረኝ? ልብሴን ለብሼ መውጣት ብቻ ቸው...
✍ሌዊ

@lewi_derest
👁 3 сегодня в 00:17
✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘 tg7.7 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
በረከት... ሰዎችን ሳያስቡት መርዳትና ፊታቸው ላይ ፈገግታ ማየት የሚያዝናናው ሰው ነው...

በብሩ ዘነጠበት.. ጨፈረበት... ወደቀ ተነሳ.. ብላ.. ብላ.. ብላ.. አሁን ደግሞ ሰዎችን መርዳት ያስደስተው ጀምሯል...

ግርማ የተባለ አጫራሹን ጠርቶ... "በል እስኪ ቆንጆ ትራክተር ፈልገህ ግዛና በስተ እገሌ ወዳለው ገጠራማ ስፍራ እንዲላክ አድርግ በእዛ እኛም እንሆናለንና ተዘጋጅ" አለው

ግርማ በዚህ ነገሩ ደስተኛ አይደለም ያቺ የለመዳት የዳሌ ፌሽታ ቀርታበት ለቦጩን እንደጣለ... "እሺ አሳውቅሀለሁ..." አለው

"ምን ትለጠጣለህ.. ያንተው ናቸው የት ይሄዱብሀል... እስኪ አንድ እንኳን ቁም ነገር ስራ... በል ውጣ አሁን" ብሎ ተቆጣው...

በረከት ሽማግሌው በሬዎቹን ሲፈልግ አርዶ ሲፈልግ ሽቶ መሬቱን በትራክተር ሆይ እያለ ሲያርስ በምናቡ አይቶ ፈገግ አለና ወደአልጋው ሄዶ... በጀርባው ተጋደመ... እግሮቹን ቀጥ አድርጎ እጆቹን አንዳመጣለት ለቋቸው እረፍትም ሰላምም ያለበት የመንፈላሰሰ ሰመመን ውስጥ ገባ...

"ተነስ ደርሰናል!" ሲለው ግርማ ደንገጥ ብሎ "ደረስን እንዴ" አለ ዓይኑን እያሻሸ... ማምሻቸውን አልጋ ይዘው ማምሻቸውን እራት በልተው... ከከተማዋ ወጣ ብለው ወደገጠራማው መንደር ስለሚጓዙ... ሁሉም ወደየክፍላቸው በጊዜ ዘመቱ...

የመንገዱ ከፍታና ዝቅታ በኮረብታ የተከበቡ መንገዶሉ ፒስታው የመኪናዋን ጎማዎች እንደኳስ ሲያንጠባጥባቸው እራት የበሉት ከቁርሱ ጋር... ሽንታቸው ከአራቸው ጋር እንደተንቦጫረቀ ከ1 ስአት ጉዞ ብኋላ ደረሱ...

በረከት በእርሻዎች መሀል ድንበር ሁኖ ጉብ ባለው እርከን ዱላቸውን በትከሻቸው አሳልፈው ጉንጫቸውን በትሩን በጨበቱ እጆቻቸው ላይ አስደግፈው እየተከዙ ቢያይ...

"ግርማ ግርማቸው ለቦጭህ እድል ቀንቶታል በጊዜ ሊሰበሰብ ነው በቶሎ ሰው አገኘን!" አለውና ትከሻውን መታ መታ አድርጎ ፈገግ አለ...

ብኋላ ላይ ለሽማግሌው ስለትራክተሩ እንዲያስተምራቸው ብለው ይዘውት ከመጡት ሰው እጅ የትራክተሩን ቁልፍ ተቀብሎ ትራክተሩን በቀስታ ወደ ሰፊው ማሳ ይሾፍረው ገባ... እሳቸው ጋር ደርሶ እጁን ለሰላምታ ካነሳላቸው ብኋላ እየሳቀ መሬቱን ለማረስ ይዘጋጅ ጀመር...

ሽማግሌው መሬቱ በትራክተር ሲታረስለት አይቶ ሲንደረደር ወደ ጎጆው ሰርጎ በአልጋው እራስ ጌ የሻጠውን ጠብ መንጃ አንስቶ...

  "በሚስትና በርስት የመጣ...
እግር እግሩን ብለህ አርገው ቆማጣ!"
እያሉ እየዛቱ... እሩጫም እርምጫም ያልሆነ... መድረስም ማርፈድም ያልመሠለ... ጀግንነትም.. ማወቅም.. ማሸነፍም መሸነፍም ያልሆነ አካሄድ እግራቸው ሲራመድ

ሚስታቸው ከኋላ በባዶ እግሯ ሱክ ሱክ እያለች "የዘር ማንዘርዎን ውርስ ነድሎ ፎቅ ሊገነባ ነው ነውያሉኝ? የማነው እንኳን አይባልም.. ደህና አድርገው ያቅምሱትማ! ወላዲቷን! ሲያንሰው ነው እንጂ.. ይህ መዥገራም!" ትላለች...

የትራክተሩ አሰልጣኝ ልሽና ብሎ ወደዛፎቹ ምሀል ከመግባቱ

ሽማግሌው አንድ ሁለቴ ቢያንዶቀዱቁት... በረከት እሳቸውን ለማስደሰት እራሱ እያረሰ ሊያሳያቸው ትራክተሩን ለማሽከርከር የሰለጠናቸውን አምስት ቀናት እረስቶ ለአመታት ያሽከረከራት አውቶ ሞቢል መኪናውን በሰውነቱ አስታውሶ... በደመነፍስ ማርሽና ነዳጁን ቢለው ቢለው ኤሊ እየጋለበ ያለ መሠለው... ዘሎ ወረደ አጯጯኹ ከትራክተር ሳይሆን ከአስራ ዘጠነኛ ፎቅ የዘለለ ነበር የሚመስለው...

ግርማ የመጡበት መኪናው ውስጥ ቦርጩን ገልብጥ የሴት ፎቶ እያመላለሰ በስልኩ እያየ ስለነበር የጠብ መንጃው ድምፅ እጆቹን አናውጧቸው ስልኩን ወዴት እንደወረወረው ሳያውቅ.. እጆቹማ የእራሳቸው የልብ ምት ሳይኖራቸው አይቀርም ከእሱ በላይ ደንግጠው እንዴት ከመኪናው የኋላ ወንበር ተነስቶ ጋቤና ደርሶ የመኪናውን ቁልፍ አጨባበጣቸው ሌላ ነው...

ግርማ በቃ ተበታትኗል አፉም ለብቻው ደንግጦ "ና.. ነፍጠን... በረከት ፍጠን እንሂድ... ኧረ እኔ ልነዳው ነው.. አፈጥንም..." ይቀባጥራሉ...

በረከት እንደምን ተንደፋድፎ አዲስ አበባ ድረስ በእግሩ የተጓዘ ያህል እርቆት መኪናው ጋር ደርሶ መኪናዋን ግርማ አስፈተለካት...

"ያውሎት አንዱ ወጠጤ.. ይበሉት! ያቅምሱት ይሄን ቀማኛ..." እያለች ሚስታቸው ወደዛፎቹ ተወራጨች...

"ቆይ ዝበይ..." እያሏት.. ጠብ መንጃቸውን ወደፊት ገትረው ወደሰውዬው ቀረቡና...

"ያመጣችሁትን ዶዘር ካመጣችሁበት የሚመልስ የለምጂ እግርህን ጎምጄ የጅብ እራት ባደረግሁህ ነበር... እያሉ... ትራክተሩን ይዞ እንዲጠፋ አስፈራርተው አባረሩት...

የመንደሩ ሰው ልክ እንደአባቶቻቸው ፋሽሽትን እንዳባረሩላቸው መስሎ ታያቸው...

"አይ እንዴት እንዴት አሽመድምደው እንዳበነኗቸው ባያችሁ..." እየተባባሉ እንደጀግና ሁሉ አከበሯቸው... ከእድሜያቸው በላይ ይሄ ተግባራቸው አንቱታነትን አበዛላቸው...

ከእንግዲህ ልክነትና ስህተት መመዘኛው ምንድን ነው? አለማወቅ ድንቁርና አይደለም! አቃለሁ ባይነት ሲገባበት ግን በትክክልም ድንቁርና ይሆናል...

ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ!
✍ሌዊ


@lewi_derest
👁 1.3 тыс. ❤ 13👍 1 ↻ 1 7 ноября