Телеграм

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

@ethioroads Строительство
РКН: проверяем Не иноагент
Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Статистика обновлена 15.11.2026 в 01:11 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики14 076
Охват поста4 752 34% от подписчиков
ERR за месяц33,76%
ERR за 24 часа22,04%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር tg14 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የሶዶ - አረካ መገንጠያ እና የሶዶ ከተማ - ዎሊ መንገድ ግንባታ 78.02 በመቶ ደረሰ
 
አዲስ አበባ፣ ህዳር 1
/2019 ዓ.ም (ኢመአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የሶዶ - ታርጫ መንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሶዶ - አረካ መገንጠያ እና የሶዶ ከተማ - ዎሊ ምዕራፍ-3 መንገድ ግንባታ 78.02 በመቶ ደረሰ።

የከተማ መንገዱ 12 ነጥብ 39 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በሁለት ሎት ተከፍሎ እየተሰራ ሲሆን  ሎት 1 ከሌዊ እስከ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ(7.14) ኪሎ ሜትር ፣ ሎት 2 ከጦና አደባባይ እስከ አረካመውጫ መገንጠያ ድረስ (5.25) ኪ.ሜትር  የሚዘልቅ ነው።
 
በእስካሁኑ  የስራ ሂደት 12.39 ኪ.ሜ የመንገድ ጠረጋ ፣ የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ የ1.2 ኪ.ሜ የካፕንግ፣ የ7.15 ኪ.ሜ የሰብ ቤዝ፣ የ4.3. ኪ.ሜ የቤዝ ኮርስ እንዲሁም የ3.15 ኪ.ሜ አስፋልት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ 2 ቦክስ ካልቨርቶች፣ 5 ስላብ ካልቨርት እና 7.15 ኪ.ሜ  የውሃ ማፋሰሻ ቱቦዎች ግንባታ እና በ4.84ኪ.ሜ የዉሃ ማፍሰሻ ዲች እንዲሁም በርካታ የስትራክቸር ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚሆን ሁለት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሃያ ሚሊዮን አስር ሺህ ሰባት መቶ ስምንት ብር ከአርባ ስድስት ሳንቲም (2,620,010,708.46)በሆነ  ወጪ በፌደራል መንግስት ሙሉ በሙሉ ተሸፍኗል።  
 
ግንባታውን የሚያከናውነው ዓለም-አቀፉ ቻይና ፈርስት ሀይዌይ እንጂነሪንግ ኮ. ሊሚትድ ሲሆን የጥራት እና ቁጥጥር ሥራውን ደግሞ  በሀገር-በቀሎቹ ጂ እና ዋይ ኢንጅነሪንግ ከደውል ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ጋር በጋራ እያከናወኑት ይገኛል።
 
ይህ የመንገድ ፕሮጅክት ግንባታ ከሚሰጠው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንጻር በአስፋልት ኮንክሪት እየተገባ ይገኛል።
 
የመንገድ ፕሮጀክቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ የነበረውን የሶዶ ከተማ ትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ በመቅረፍ የከተማ ዉስጥ ለዉስጥ እንቅስቃሴ እና ከከተማ ለመዉጣትም ሆነ ወደ ከተማ ለመግባት ያለውን የጉዞ ጊዜ የሚያሳጥር ይሆናል።

በወላይታ ዞን እና አጎራባች ዞኖች በስፋት የሚመረቱትን እንደ ቡና፣ ለውዝ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍ እና ቅቤ ያሉ የግብርና ምርቶችን በቀላሉ ወደ መሃል ገበያ ለማቅረብ የጎላ ሚና ይጫወታል።

ከዚህም በተጨማሪ መንገዱ አጎራባች ላይ ላሉ የአርባምንጭ፤ ደቡብ ኦሞ እንዲሁም ለአጆራ ፏፏቴ የቱሪዝም መዳረሻ በመሆን ለሀገር ውስጥ ገቢ ትልቅ አቅምን  ይፈጥራል።

የፕሮጀክቱ የጎን ስፋት በከተማ 34.0 ሜትር ሲሆን  በቀበሌ 13.80 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል ።


በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👁 3.1 тыс. ❤ 6 ↻ 4 10 ноября