Телеграм

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

@FDRE_MoLSofficial Карьера и вакансии
РКН: проверяем Не иноагент
FDRE, Ministry of Labor and Skills

Статистика обновлена 15.11.2026 в 01:41 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики70 461
Охват поста18 436 26% от подписчиков
ERR за месяц26,16%
ERR за 24 часа17,94%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia tg70 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
"የሥራ ማዕከላት ግንባታ በጥራትና በፍጥነት ተገንብተው ለታለመላቸው ዓላማ መዋል ይገባቸዋል።" ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ


የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን ዘመናዊ የሥራ ማዕከላት የግንባታ ሂደትና ያሉበትን የአፈጻጸም ደረጃ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።

በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተገለጸው፤ የተጀመሩት የሥራ ማዕከላት ግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለታለመላቸው የልማትና የወጣቶች አገልግሎት ዓላማ መዋል እንደሚገባቸዉ ተመላክቷል።

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ እንደገለጹት እየተገነቡ ያሉ የሥራ ማዕከላት ለወጣቶችና ለሥራ ፈላጊዎች በአንድ ማዕከል (One-Stop Service) ፈጣንና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የግንባታው ጥራትና ደረጃ ሳይጓደል በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ መዋል ይገባቸዋል።

ግንባታውን እያከናወኑ የሚገኙ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸዉ የግንባታውን ሥራ ጥራትና ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ሙሉ አቅማችዉን አቀናጅተዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

የሥራ ማዕከላት የአገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ ፣ የሥራ ፈላጊዎችና ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጓቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ያስችላል ሲል የዘገበው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው።
👁 12 тыс. ❤ 104🙏 6👌 5 ↻ 8 6 ноября
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia tg70 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ሥልጠናን ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁና ምርታማ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሰራ ነው፡፡

ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓቱን ከሥራ ገበያውና ከኢንዱስትሪው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁ፣ ምርታማና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትር ዴኤታው ይህን የገለጹት የSTEP IV – Horti-Skills የሆርቲካልቸር ክህሎት ልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያና የትግበራ ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ላይ ነው።

የክህሎት ልማት ስኬት የሚለካው በሚሰለጥኑ ዜጎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን፣ ሠልጣኞች በሥራ ገበያው በሚኖራቸው ተሳትፎ፣ በሚያገኙት የሥራ ዕድል፣ በሚፈጥሩት የራስ ሥራና ለኢኮኖሚው በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ በሥልጠና ተቋማትና በሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ የክህሎት ክፍተቶችን በመሙላትና የአሰልጣኞችን ብቃት በማሳደግ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በማጠናከር ላይ ያተኩራል።

ሆርቲካልቸር የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ የሀገርን ተወዳዳሪነት ለማጠናከርና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አቅም ያለው ዘርፍ ነው።

ይህንን አቅም ለመጠቀም ዘመናዊ ቴክኒካዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ዲጂታልና የሥራ ፈጠራ ክህሎቶች የተላበሰ የሰው ኃይል ማፍራት ወሳኝ ነው።

ፕሮጀክቱ የግሉን ዘርፍ በክህሎት ፍላጎት መለየትና በሙያ ደረጃዎች ዝግጅት ላይ በማሳተፍ፣ ተግባራዊ ሥልጠናንና የሥልጠና ጥራትን በማሻሻል፣ የተቋማትን ባለቤትነትና የውጤቶችን ዘላቂነት በማጠናከር ላይ ያተኩራል። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በዘርፉ የሥራ ቅጥርና የሥራ ፈጠራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል።

ፕሮጀክቱ በጀርመንና በኔዘርላንድስ መንግሥታት የገንዘብ ድጋፍ፣ በGIZ ትግበራና ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የሚከናወን ነው፡፡

ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
👁 12 тыс. ❤ 28👏 5🤩 4 ↻ 3 6 ноября
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia tg70 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
በ22 ቀናት ንቅናቄ ከ25 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎች ተፈጠሩ

የአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የሁለተኛው ዙር የ22 ቀናት የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ ዕቅድ አፈጻጸምን ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ጋር ገምግሟል።

በግምገማው በንቅናቄው ወቅት 25,944 የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸው፣ ከ406.6 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መመቻቸቱና 746 ኢንተርፕራይዞች መደራጀታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም 29,409 ሥራ ፈላጊዎች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ56 ሺህ በላይ ዜጎች በለስላሳና ቴክኒክ ክህሎት ሥልጠናዎች ተሳትፈዋል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የቢሮው የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ፣ ከመጀመሪያው ዙር ንቅናቄ የተገኙ ልምዶችንና የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተቀናጀና ውጤትን ያማከለ አፈጻጸም ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሁሉም ክፍለ ከተሞች በአንድ ዕቅድና የሪፖርት ሥርዓት በመመራት፣ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሠሩም አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
👁 13 тыс. ❤ 49🤩 5🙏 1 ↻ 7 5 ноября