Телеграм

Ethiopia Insider

@EthiopiaInsiderNews Общие новости и СМИ
РКН: проверяем Не иноагент
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.

Статистика обновлена 15.11.2026 в 12:09 · 2 просмотра страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики19 603 -4 за 1 день
Охват поста6 104 31% от подписчиков
ERR за месяц31,14%
ERR за 24 часа13,30%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
Ethiopia Insider tg19 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያገኘው ህዝብ ብዛት ስንት ነው? 60 ወይስ 85 ሚሊዮን?

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ሶስተኛ ፕሮግራም፤ በመንግስት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የህዝብ ብዛት ትንበያዎች መካከል ባለው “ከፍተኛ ልዩነት” ሁለት የተለያዩ የዕቅድ አማራጮች ለማዘጋጀት ተገድዷል።

በሚቀጥሉት ዘጠኝ ዓመታት በመላ ሀገሪቱ ኤሌክትሪክ ለማዳረስ የተዘጋጀው ፖሊሲ፤ የህዝብ ቁጥርን በተመለከተ ባለው የተለያየ ትንበያ ምክንያት ሁለት አማራጭ ዕቅዶች ቀርቦበታል።

የትንበያው ልዩነት “በኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ ዕቅድ ኢንቨስትመንት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ” እንደሚያሳድር የብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ሶስተኛ ፕሮግራም ሰነድ ያብራራል።

በዚህም ምክያት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሁለት የተለያዩ የዕቅድ አማራጮች ለማዘጋጀት ተገድዷል።

የመጀመሪያው “የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 133 ሚሊዮን ይሆናል” የሚለውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የዓለም ባንክን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ትንበያ መሰረት ያደረገ ነው።

ሁለተኛው ከዓለም አቀፍ ተቋማት ትንበያ በ22 ሚሊዮን ዝቅ በሚለው፤ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት መረጃ ላይ የተመረኮዘ ነው። በመስሪያ ቤቱ ትንበያ መሰረት እስከ ፈረንጆቹ 2024 አቆጣጠር ድረስ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 111 ሚሊዮን ነው።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/19341/

@EthiopiaInsiderNews
👁 2.6 тыс. ❤ 7 ↻ 2 13 ноября
Ethiopia Insider tg19 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
የአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ሁኔታ በተለይም “ቀጠናዊ ግጭት” ሊቀሰቀስ የሚችለው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ድንበር ተሻጋሪ ውጥረት እንዳሳሰባቸው በኢኮኖሚ የበለጸጉት የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስጋታቸውን ገለጹ።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ከተካሄደ ስብሰባ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው።

በፓሪስ የተካሄደው ስብሰባ የካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጃፖን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት ነው።

ይህንኑ ስብሰባ፤ ከሰባቱ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይም ታድመውበታል።

በስብሰባው መጨረሻ ይፋ በተደረገው መግለጫ፤ የኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ቀውሶች ላይ ሀገራቱ ያላቸውን አቋም ያንጸባረቀ ሲሆን ግጭት ውስጥ የሚገኙት የሱዳን፤ የዩክሬን እና የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ተካተዋል።

የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተው የመግለጫው ክፍል፤ ሀገሪቱ ከኤርትራ ጋር የገባችበት ውጥረት ተነስቷል።

የቡድን ሰባት ሀገራት በመግለጫቸው፤ “ሁሉም ወገኖች” ውጥረቱን የሚያባብሱ እርምጃዎች ከመውሰድ እንዲቆጠቡ እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሰብአዊ እርዳታ ደህንነቱ ተጠብቆ ያለ ገደብ ለተቸገሩ ሰዎች እንዲደርስ፣ ሲቪል ሰዎች በተለይም ሴቶች እና ህጻናት ከጥቃት እንዲጠበቁም ሀገራቱ አሳስበዋል።

🔴ለተጨማሪ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/19336/

@EthiopiaInsiderNews
👁 3.7 тыс. ❤ 8 ↻ 5 11 ноября
Ethiopia Insider tg19 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
በመቐለ ከተማ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከነገ ጀምሮ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።

“ህጋዊ ፍቃድ የሌለው” የጦር መሳሪያ የያዙ አሊያም በቤታቸው የደበቁ የከተማይቱ ነዋሪዎች፤ ለትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲያስረክቡም ከነገ ጀምሮ የሶስት ቀናት ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።

የሰዓት እላፊውን እና የጦር መሳሪያ የማስረከቡን ቀነ ገደብ በከተማይቱ መጣሉን ያስታወቀው የመከላከያ ሰራዊት ነው።

በትግራይ ክልል መገናኛ ብዙሃን ምሽቱን በትግርኛ ቋንቋ የተሰራጨው የሰራዊቱ መግለጫ፤ እነዚህ እርምጃዎችን መተግበር ያስፈለገው የመቐለ ከተማን “ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ” እንደሆነ አመልክቷል።

የመቐለ የጸጥታ ሁኔታ “በሂደት መሻሻሎች እያሳየ” መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፤ ሆኖም የከተማይቱ ነዋሪዎች “አልፎ አልፎ” ለተለያዩ “የደህንነት ስጋቶች እየተጋለጡ” መሆኑን አስታውቋል።

እነዚህ ስጋቶች የመነጩት ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገዶች “ከእስር የተፈቱ ግለሰቦች” እና “የተደራጁ የዝርፍያ ቡድኖች” በሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ምክንያት እንደሆነም መግለጫው ጠቁሟል።

የትግራይ ክልል ዋና ከተማን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ባለፉት ቀናት ያነጋገረቻቸው አራት የከተማዋ ነዋሪዎችም፤ በመቐለ የጸጥታ ስጋቶች መኖራቸውን አረጋግጠዋል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈቀዱ አንድ የመቐለ ነዋሪ፤ የህወሓት ኃይሎች ከተማዋን ለቅቀው ከወጡ በኋላ በከተማዋ “ስርዓት አልበኝነት ሰፍኖ መቆየቱን” እና በግል እና በመንግስት ተቋማት ላይ “ከፍተኛ ዝርፊያ” መፈጸሙን አስታውሰዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/19329/

@EthiopiaInsiderNes
👁 6.9 тыс. ❤ 15😁 10👍 5 ↻ 7 5 ноября