Телеграм

ከፍልስፍና ዓለም™

@Philosophyofworld1 История и философия
РКН: проверяем Не иноагент
A wise man is one who has learned to restrain his desires.The lowest level of life is to live only within the bounds of desire.Most people have many desires but little knowledge wisdom belongs to those who have much knowledge and few desires -Schopenhauer

Статистика обновлена 14.11.2026 в 23:43 · 1 просмотр страницы · Хотите больше просмотров?

Подписчики26 438
Охват поста4 920 19% от подписчиков
ERR за месяц18,61%
ERR за 24 часа6,63%

Динамика за 30 дней

Рекламные публикации

Рекламных публикаций не найденоЗа последнее время мы не нашли на площадке ни одного рекламного поста.

Последние публикации

Все посты канала →
ከፍልስፍና ዓለም™ tg26 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
አስክሊፒዮስ(የህክምና አማልክት ነዉ) ሕክምናን ለልጆቹ ያላስተማረው ከድንቁርና አይደለም ይልቁንም በሥርዓት በተደራጀች ከተማ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሥራ አለው፣ ማንም ዕድሜ ልኩን ለመታመምና ለመታከም ጊዜ የለውም ብሎ ስላወቀ ነው። ሕክምናን የፈጠረው በተፈጥሮና በልማድ ጤናማ አካል ላላቸው ግን የተወሰነ በሽታ ላለባቸው ሰዎች ነው፤ በመድኃኒት ወይም በቀዶ ሕክምና በሽታውን አስወገደ፣ ከዚያ መደበኛ አኗኗራቸውን አዘዘ። በበሽታ የተሞላ አካል ላላቸው ሰዎች ሕይወታቸውን በረዥም ሥቃይ ለማራዘም እና ተመሳሳይ ልጆች እንዲወልዱ ለማድረግ አልሞከረም። መደበኛ ኑሮ መኖር ለማይችል ሰው ለራሱም ለከተማውም አይጠቅምም ብሎ ሕክምና አልሰጠም። የአስክሊፒዮስ ልጆች በትሮይ ጦርነት በሜኔላዎስ ቁስል ደሙን ጠጥተው ለስላሳ መድኃኒት ብቻ ሲቀቡ፣ ከዚያ በኋላ ምግብና መጠጥ አላዘዙም።
ፎኪሊዴስ "ኑሮ ሲኖርህ በጎነትን ተለማመድ" ብሏል። ግን ለሰውነት ከመጠን ያለፈ እንክብካቤ፣ቤት አስተዳደርን፣ ወታደራዊ አገልግሎትንና የፖለቲካ ሥራን እንዲሁም ማንኛውንም ትምህርት፣ አስተሳሰብና ፍልስፍናዊ ማሰላሰልን እንደሚያደናቅፍ ግላውኮንም ይቀበላል። አስክሊፒዮስ በወርቅ ተገዝቶ ሊሞት የተቃረበ ሀብታም ሰው ስለፈወሰ በመብረቅ ተመታ ይላሉ። ይህንንም በቅድሙ  መርሁ መሰረት ሶቅራጠስ አይቀበለዉም፤ ምክንያቱም የአምላክ ልጅ ከሆነ በገንዘብ አይሸነገልም፤በገንዘብ ከተሸነገለ ደሞ የአምላክ ልጅ አይደለም። ይሄን ጊዜ ግላውኮን...
በከተማችን ጥሩ ሐኪሞችና ጥሩ ዳኞች ያስፈልጉናል አይደል? ጥሩ ሐኪም ብዙ ጤነኛና የታመሙ ሰዎችን የተመለከተ፣ ጥሩ ዳኛም
ከብዙ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ጋር የተገናኘ ነው ይላል።

ሶቅራጠስ ግን ሁለቱ ጥያቄዎች አንድ ዓይነት አይደሉም ይላል...
ጥሩ ሀኪም አካልን በአካል ሳይሆን በነብስ ያክማል ፤ ከልጅነት ጀምሮ ከብዙ የታመሙ አካላት ጋር ቢቆይ፣ ራሱም ሁሉንም በሽታ ቢያገኝና በተፈጥሮው በጣም ጤነኛ ባይሆን ይበልጥ ብልህ ይሆናል። ጥሩ ዳኛ ግን ነብስን በነብስ ይገዛል ፤ ከልጅነት ጀምሮ ከመጥፎ ነብሳት ጋር ማደግና በኢፍትሐዊነት መጠመድ የለበትም፤ በውስጡ ኢፍትሐዊነትን የማያውቅ መሆን አለበት ፤ አዛውንት እና "ዘግይቶ ተማሪ" መሆን አለበት። ኢፍትሐዊነት ምን እንደሆነ ከራሱ ነብስ ሳይሆን በሌሎች ነብስ እንደ ባዕድ ነገር የሚያውቅ መሆን አለበት፤ በወጣትነታቸው ግን ተላላ ስለሚመስሉ ኢፍትሐዊ ሰዎች በቀላሉ ያታልሏቸዋል እነሆ በውስጣቸው የመጥፎ ባሕርይ ምሳሌ የላቸዉምና። ይላል።

ሕክምናና ዳኝነት ጥሩ አካልና ነብስ ያላቸውን ዜጎች ይንከባከባሉ፤ አካላቸው በተፈጥሮ ጤነኛ ያልሆነውን እንዲሞት ይፈቅዳሉ፤ ነብሳቸው በተፈጥሮ ሊታከም በማይችል ሁኔታ መጥፎ የሆኑትን ደግሞ ራሳቸው ይገድላሉ !። ግላውኮንም ይህ ለተቀበሉትም ለከተማዋም የተሻለ እንደሆነ ይስማማል። ቀጥሎም ይቺን የምናብ ከተማ ማን ይገዛል ለሚለዉ ስቅራጠስ አዛውንቶች ይገዛሉ፣ ወጣቶች ይገዛሉ፤ ገዥዎች ከጠባቂዎች ምርጦቹ ማለትም ከተማዋን በመጠበቅ የተሻለ ዕውቀትና ችሎታ ያላቸው እና ለከተማዋ የሚያስቡ መሆን አለባቸዉ። ሰው ከሁሉ የሚያስብለት የሚወደውን ነው፤ የሚወደውም ለእሱና ለራሱ አንድ ዓይነት ጥቅም እንደሚሰጥ ሲያስብ ነው። እሱ ሲሳካለት ራሱም እንደሚሳካለት ሲያምን ነዉ። ስለዚህ ከጠባቂዎች ለከተማዋ ጥቅም ነው ብለው የሚያምኑትን በሕይወታቸው ሙሉ ለማድረግ በጣም የሚያዘነብሉትን እንመርጣለን። ይላል።

ሶቅራጠስ ጠቃሚ ውሸቶችን ሲያነሳ ቆይቷል፤ አሁን "አንድ የተከበረ ውሸት" (a single noble lie) እንዴት እንደሚፈጠር ይጠይቃል፤ በተቻለ መጠን ገዥዎቹን ራሳቸውን የሚያሳምን፤ ካልተቻለ የቀረውን ከተማ የሚያሳምን መሆን አለበት። "የፊንቄ ተረት" ይለዋል፤ ባለቅኔዎች እንደሚሉት ብዙ ቦታዎች የሆነ ነገር ነው፤ በዘመናችን አልሆነም፣ ሊሆንም አይችልም፤ ሰዎችን ለማሳመን ብዙ ሥራ ይጠይቃል። ሶቅራጠስ ድፍረትና ቃላት ከየት እንደሚያገኝ እንደማያውቅ ይናገራል፤ ግላውኮንም "ለዚህ ነው ቀደም ብለህ ያፈርከው" ይለዋል። ሶቅራጠስም ተረቱን ይቀጥላል...

ዜጎች የተሰጣቸው አስተዳደግና ትምህርት ሁሉ እንደ ሕልም ነበር፤ እውነታው ግን እነሱና መሣሪያዎቻቸው በምድር ውስጥ ተሠርተውና ተመግበው ነበር፤ ሲጠናቀቁ እናታቸው ምድር ወደ ላይ ላከቻቸው። ስለዚህ ለምድሪቱ መጠበቅና ማሰብ አለባቸው፣ ሌሎችን ዜጎች "ከምድር የተወለዱ ወንድሞቻቸው" አድርገው መቁጠር አለባቸዉ። ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሲሠራችሁ ለመግዛት የሚችሉት ላይ ወርቅ፣ በአጋዥዎች ላይ ብር፣ በገበሬዎችና በሌሎች ሙያተኞች ላይ ብረትና ነሐስ ቀላቅሏል። ልጆች በአብዛኛው እንደ ወላጆቻቸው ይሆናሉ፤ ዝምድና ስላላችሁ ግን አልፎ አልፎ ከወርቅ ወላጅ የብር ልጅ፣ ከብር ወላጅ የወርቅ ልጅ ይወለዳል።የሚል ነበር።
አምላክም ለነዋሪዎቹ እንደዚህ ያዛል፤ በልጆቻቸው ነብስ ውስጥ ያለውን የብረት ድብልቅ ከሁሉ በላይ መጠበቅ አለባችሁ። ልጃቹ በብረት ወይም በነሐስ ተቀላቅሎ ቢወለድ በምንም መንገድ ሊራሩለት አይገባም፤ ለተፈጥሮው የሚስማማ ክብር ሰጥተው ወደ ገበሬዎችና ሙያተኞች ያስወጡታል። ከእነሱ ልጅ ወርቅ ወይም ብር ያለው ከተገኘ ክብር ተሰጥቶት ወደ ጠባቂዎች ወይም አጋዥዎች ይወሰዳሉ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ከተማዋ ብረት ወይም ነሐስ ጠባቂ ካላት ትጠፋለች።

ከተረቱ በኋላ ሶቅራጠስ ምድራዊ ልጆች መሣሪያ አስታጥቀው ከገዥዎቻቸው ጋር ወደ ከተማዋ ምርጥ ቦታ ሰፈር እንዲመሠርቱ ይመራል፤ ከዚያ በከተማዋ ውስጥ ሕጎችን የማይታዘዝ ማንኛውንም ሰው በቀላሉ መቆጣጠር ወይም እንደ ተኩላ መንጋ የሚያጠቃ የውጭ ጠላትን እንዲመክት መደረግ አለበትም ይላል። ከዚያ መስዋዕት ከፍለው ማረፊያ ይሠራሉ። ትምህርት ብቻ በቂ እንዳልሆነም ሶቅራጠስ ያስጠነቅቃል ፤ መኖሪያና ንብረትም ከጥሩ ጠባቂነት የማይከለክሉና በዜጎች ላይ ክፋትን የማያበረታቱ መሆን አለባቸው። ሕጉም እንደሚከተለዉ መሆን አለበት ይላል...

ከሚያስፈልገው በላይ የግል ንብረት ማንም አይኖረውም።
መኖሪያና ማከማቻ ቤቶች ሁሉም በፈለገው ጊዜ ሊገባበት የሚችል ክፍት ይሆናሉ።
አስፈላጊውን ምግብ ከሌሎች ዜጎች እንደ ጠባቂነት ደመወዝ ይቀበላሉ፤ መጠኑ በዓመቱ መጨረሻ ሳያንስና ሳይተርፍ እንዲወሰን ይደረጋል።
የጋራ ማዕድ ቤቶች በየሰፈሩ እንደ ወታደር አብረው ይኖራሉ።
መለኮታዊ ወርቅና ብር በነብሳቸው ውስጥ ከአማልክት እንደ ቋሚ ስጦታ አላቸው ስለዚህ የሰው ወርቅ አያስፈልጋቸውም።
ወርቅና ብር መንካት፣ ከእነሱ ጋር በአንድ ጣሪያ መኖር፣ እንደ ጌጥ መልበስ፣ ከወርቅ/ብር ጽዋ መጠጣት በመለኮታዊ ሕግ ተከልክሏል።

ሶቅራጠስም በዚህ መንገድ ራሳቸውንም ከተማዋንም ያድናሉ። ግን የግል መሬት፣ ቤትና ገንዘብ ካገኙ የቤት አስተዳዳሪዎችና ገበሬዎች ይሆናሉ እንጂ ጠባቂዎች አይሆኑም፤ የዜጎች ወዳጅ ሳይሆን ጠላት ጌቶች ለመሆን ይቃጣሉ።በሕይወታቸዉ ሙሉ ሲጠሉና ሲጠሉ፣ ሲያሴሩና ሲሴስኑ፣ ከውጭ ጠላቶች የበለጠ አደገኛ የዉስጥ ጠላቶች ይሆናሉ። ስለዚህ ይህ እንደ ሕግ ይደነገግ ይለዋል ፤ግላውኮንም ይስማማል።

ይቀጥላል...

ምንጭ፤ ከላይ ከተያያዘዉ መፅሀፍ (Republic) ከገፅ 128 እስከ 176
👁 931 ❤ 12🤷‍♂ 1🔥 1 💬 1 ↻ 2 вчера в 15:50
ከፍልስፍና ዓለም™ tg26 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ሶቅራጠስ ጠባቂዎች ድፍረት እንዲኖራቸው ከሞት ፍርሃት ነፃ መሆን አለባቸው ብሎ ይጀምራል። የሀደስ ዓለም(ይህ በግሪክ አፈታሪክ ገሀነምን ወይም የሙታን አለምን የሚወክል ነዉ) አስፈሪ ነው ብሎ የሚያምን ሰው ሞትን በጦርነት ከመሸነፍና ከባርነት አይመርጥም። ስለዚህ ስለ ሀደስ ዓለም የሚቀኙ ባለቅኔዎችን መቆጣጠር አለብን፤ ጥሩ ነገር እንዲናገሩ እንጠይቃቸዋለን፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ያሉት ነገር እውነት አይደለም፣ለወደፊት ተዋጊዎችም አይጠቅምም። ሶቅራጠስም ከዚህ በፊት ስለ አማልክት ከተደረሱት ድርሳናት ዉስጥም ምን ምን መወገድ እንዳለባቸዉ ለአብነት ያህል ያነሳል...
በሆሜር ድርሰት ላይ አኪሌስ "በሀደስ ዓለም ከሙታን ሁሉ ንጉሥ ከመሆን በምድር ላይ ድሃ ባሪያ መሆን ይሻለኛል" ማለቱ። ሀደስ(የሙት አለም አማልክት) ራሱ መኖሪያው ለሰዎችና ለአማልክት እንዳይታይ መፍራቱ። የፓትሮክለስ ነብስ፣ ቲሬሲያስ፣ እንደ ጢስ የሚጮኽ ነብሳት፣ እንደ የሌሊት ወፍ የሚጮኹ የሙታን ነብሳት መተረካቸዉ ፤ ኮኪቶስ (የለቅሶ ወንዝ)፣ ስቲክስ (የጥላቻ ወንዝ)... የመሳሰሉ አስፈሪ ስሞች በሙታን አለም ዉስጥ መሰየማቸዉን ይጠቅሳል።

ሶቅራጠስ በመቀጠል ይህን የሚለዉም የእነ ሆሜርን ስራ ለማጣጣል ሳይሆን በእነዚህ ትርክቶች የሚተላለፈዉ ነገር ጠባቂዎች/ዘቦች ላይ በሚፈጥረዉ የሞት ፍራቻ እና ስነ ልቦናዊ ጫና ተነሳስቶ እንደሆነ ያበክራል። በመቀጠል ሶቅራጠስ ሌላ ሙግትንም ያዋቅራል እሱም... ጥሩ ሰው ሌላ ጥሩ ሰው ሲሞት ሞቱን አስፈሪ ነገር አድርጎ አይቆጥረውም፤ ስለዚህ አያለቅስም። ጥሩ ሰው ጥሩ ህይወትን ለመኖር እራሱ ለራሱ በቂ ነዉ፤ ልጅ፣ ወንድም ወይም ንብረት ማጣት ለእሱ ያን ያህል አስፈሪ አይደለም። የሚል ነዉ፤ ይህንንም አምነን ከተቀበልን ሙሾን እናስወግዳለን፤ ለሴቶች እና ለፈሪ ወንዶችም እንተወዋለን፤ የምናሰለጥናቸው ጠባቂዎች ግን ደፋር ይሆናሉ።ይህም እንዲሆን ሆሜር ላይ ያሉ አንድ አንድ ትርክቶች መስተካከል አለባቸዉ ለምሳሌ አኪሌስ በጀርባው እና በሆዱ እየተገላበጠ በባሕር ዳርቻ ሲንከራተት፣ አመድ በራሱ ላይ ሲያፈስ፣ ፕሪያም በፍግ ውስጥ ሲንከባለል፣ አማልክት (ቴቲስ፣ ዜውስ ስለ ሳርፔዶን) ሲያለቅሱ...ያሉት ትርክቶች መፋቅ እና መሰረዝ አለባቸዉ ምክንያቱም ልጆች እነዚህን እየሰሙ ካደጉ ለትንሽ መከራ ሁሉ ዋይታን ወዳጅ ይሆናሉ ይህም ጥሩ ዘቦችን እንዳናፈራ ጋሬጣ ይሆንብናል። አክሎም ጠባቂዎች የሳቅ ወዳጆች መሆን የለባቸውም፤ይላል። ምክንያቱም ኃይለኛ ሳቅ ኃይለኛ ተቃራኒዉን ስሜት ያስከትላል። ማለትም በሃይል የሚስቅ ከሳቁ ቡሃላ ሃይለኛ ባዶነት እና ድብርት ይከተልበታል በዚህም የተነሳ ጥሩ ሰዎች እና አማልክት በሳቅ ተሸንፈዉ መታየት የለባቸዉም። ስለዚህ ሆሜር "አማልክት ሄፋይስቶስ በአዳራሹ ሲያነክስ አይተው ከባድ ሳቅ ሳቁ" ማለቱ መወገድ አለበት።

በመቀጠልም ሶቅራጠስ ከዚህ ቀደም ዉሸት ለአማልክት ምንም አይሰራም ለሰዎች ግን አንድ አንዴ ያስፈልጋል እንዳለዉ ሁሉ ማን ለምን ቢዋሽ ተቀባይነት እንደሚኖረዉ ያብራራል። ዉሸት መዋሸቱ ትክክል የሚሆነዉ እራስን ከጠላት ለመከላከል እና ከተማን ለመጠበቅ ብቻ በአመራሮች እንደሆነም ይገልፃል። ግለሰብ ግን ለእንዲህ ያሉ ገዥዎች ቢዋሽ ታማሚ ለሐኪሙ፣ አትሌት ለአሠልጣኙ፣ መርከበኛ ለካፒቴኑ ስለ ሁኔታው እውነቱን ከመንገር ይልቅ ቢዋሽ እንደሚሠራው ስሕተት ነው፤ ግለሰቡ እራሱን ጭምር የሚጎዳ ከባድ ስሕተት ይሆናል። በከተማ ውስጥ የተያዘ ማንኛውም ሌላ ሰው ነቢይ፣ ሐኪም፣ አናጢ ...ሲዋሽ ከተማን እንደ መርከብ የሚያፈርስ ልማድ ስላስተዋወቀ ይቀጣል። በዚህም የተነሳ ግለሰቦች ከግለሰቦች እና ዜጎች ከዜጎች ጋር በፍፁም መወሻሸት የለባቸዉም። በመቀጠል ለብዙሃኑ የራስን መግዛት ዋና ክፍሎች ሲል የሚዘረዝራቸዉን ያስቀምጣል፤ እነሱም ገዥዎችን መታዘዝ፣በመጠጥ፣ በወሲብና በምግብ ደስታ ላይ እራስን መግዛት ናቸው።ይላል። በዚህም አኪሌስ አጋሜምኖንን "ሰካራም፣ የውሻ ዐይን፣ የአጋዘን ልብ" ብሎ መሳደቡ፤ ጥበበኛው ኦዲሴዎስ የምርጥ ነገር ግብዣ ብሎ መናገሩ፤ ዜውስ በፍትወት ተሸንፎ ሄራን መሬት ላይ ሊወስዳት መፈለጉ፤ ሄፋይስቶስ አሬስንና አፍሮዳይትን ማሰሩ... እነዚህ ከትረካዎቹ ሊወገዱ የሚገቡ ትርክቶች ናቸዉ ምክንያቱም ሰዎች ራስን መግዛት እንዳይማሩ ያረጋል ለአማልክትም አጉል ባህሪን ያጎናፅፋል። ከሱ በተጨማሪም ጠባቂዎች በስጦታ የሚገዙ ወይም ገንዘብ ወዳዶች መሆን የለባቸውም፤ ስለዚህ "ስጦታ/መስዋዕት አማልክትንና ንጉሦችን ያሳምናል" የሚለው መዘመር የለበትም። ፎኒክስ ለአኪሌስ ስጦታ እንዲቀበል በመምከሩ መመስገን የለበትም፤ አኪሌስ ከአጋሜምኖን ስጦታ በመቀበሉ ወይም የሄክተርን አስከሬን በገንዘብ በመልቀቁ ገንዘብ ወዳድ መባል የለበትም። ሶቅራጠስ እነዚህን ስለ አኪሌስ መናገር በእርግጥ ኃጢአት እንደሆነ ይናገራል። ሰዎች አኪሌስ በአፖሎ ላይ እንደተናገረ (ኃይል ቢኖረኝ እቀጣሃለሁ)፣ ከወንዝ አምላክ ጋር እንደተዋጋ፣ የሄክተርን አስከሬን በፓትሮክለስ መቃብር ዙሪያ እንደጎተተ፣ በእሳት ላይ ምርኮኞችን እንደገደለ እንዲያምኑ መፍቀድ የለብንም። ቴሴዎስና ፔይሪቶስ የተባሉ የአማልክት ልጆች አሰቃቂ ጥቃት እንደሞከሩ ማመን የለብንም። ባለቅኔዎቹ ወይ እንዳላደረጉት ወይ የአማልክት ልጆች እንዳልሆኑ ማሳወቅ አለባቸው። ሁለቱንም መናገር አይችሉም፤ አማልክት ክፋትን እንደሚያመጡ ወይም ጀግኖች ከሰዎች የተሻሉ እንዳልሆኑ ወጣቶችን ማሳመን የለባቸውም። ሶቅራጠስ ይህን የሚለዉም እንዲህ ያሉ ታሪኮች ክፉ ሰው "የአማልክት ዘር እንኳ ተመሳሳይ አደረጉ" እያለ እራሱን እና ተግባሩን እንዲያፀድቅ ያረጋሉ በሚል ምክንያት ነዉ፤ ስለዚህ ወጣቶችን ለክፋት እና ግድየለሽነት ይዳርጋሉ።

ሶቅራጠስም ቀጠል አርጎ ከአማልክት፣ ከጀግኖችና ከሀደስ ዓለም ታሪኮች በኋላ የሰዎች ታሪኮች እንደሚቀሩ ይናገራል። ነገር ግን እሱ እዚህ ሊወስን እንደማይችል ይቀበላል ምክንያቱም ባለቅኔዎችና ጸሐፊዎች በጣም አስፈላጊ በሆነው ነገር ይሳሳታሉ "ብዙ ኢፍትሐዊ ሰዎች ደስተኛ ናቸው፣ ብዙ ፍትሐዊ ሰዎች ደሞ አይደሉም ፣ ከተደበቀ ኢፍትሐዊነት መፈጸም ይጠቅማል፣ ፍትሕ የሌላው ጥቅምና የራስ ኪሳራ ነውና" ይላሉ። እነዚህን መከልከልና ተቃራኒውን እንዲዘምሩ ማዘዝ ይገባል። ግን ይህ ቀደም ብለን ስንመረምረው የነበረውን ጥያቄ (ፍትሕ ምንድን ነው፣ ለባለቤቱ እንዴት ይጠቅማል) እንደ ተመለሰ መቀበል ነው፤ ስለዚህ ፍትሕን እስክናገኝ ድረስ ስለ ሰዎች የሚነገሩትን መወሰን አንችልም። በመቀጠል ሶቅራጠስ ጥያቄውን ከ "ምን ይባል?" ወደ "እንዴት ይባል?" ያዞራል፤ ባለቅኔዎችና ተረት ተናጋሪዎች የሚናገሩት ሁሉ ያለፈ፣ የአሁን ወይም የወደፊት ክስተቶች ትረካ ነው። ትረካ ደሞ በሦስት መንገድ ይሆናል...

ንጹሕ ትረካ(narration) በዚህ ያለ ማስመሰል ባለቅኔው ሁልጊዜ በራሱ ድምፅ በገሃዱ አለም ስለተፈጠሩ ነገሮች ብቻ ይናገራል፤ ንጹሕ ማስመሰል (imitation) እዚህ ላይ ደሞ የባለቅኔው ጠፍቶ ገጸ ባሕርያት ብቻ ይናገራሉ። ሌላዉ ደሞ የሁለቱም ድብልቅ ነዉ።

ከድርሳናቱ ላይ ምሳሌን ሲሰጥም እንዲህ ይላል...ሆሜር በኢሊያድ መጀመሪያ ካህኑ ክሪሴስ ሴት ልጁን እንዲለቅ አጋሜምኖንን ሲለምን ስንመለከት ባለቅኔው መጀመሪያ በራሱ ድምፅ ይናገራል(በሶስተኛ መደብ አርጎ)፤ ከዚያ ራሱ ክሪሴስ እንደሆነ ሆኖ ይናገራል ስለዚህ ይህ ማስመሰል ነዉ። ሶቅራጠስ በግጥም ሳይሆን በተራ ንግግር ተመሳሳይ ታሪክ በንጹሕ ትረካ ይነግራል (ካህኑ መጥቶ ጸለየ፣ አጋሜምኖን ተቆጣ፣ ካህኑ በፍርሃት ሄዶ ወደ አፖሎ ጸለየ...)። ምሳሌው ልዩነቱን ያሳያል። በቀጣይም ከዚህ በፊት የተቀመጠዉን መርሕ ማለትም እያንዳንዱ ሰው አንድ ሥራ ጥሩ አድርጎ ሊሠራ ይችላል፣ ብዙ ሊሠራ ግን አይችልም። ማስመሰልም እንዲሁ ነዉ ፤ አንድ ሰው ብዙን ነገር በጥሩ ሊመስል አይችልም። ተውኔት ጸሐፊና ኮሜዲ ጸሐፊ አንድ ሰው ሊሆን አይችልም።አንድ ሰው ብዙ ነገር በጥሩ ሊመስልም ሆነ ያንኑ ሥራዎች ራሱ በጥሩ ሊሠራ አይችልም።ጠባቂዎች ምን ሊመስሉ ይችላሉ? ከልጅነት ጀምሮ የሚስማማቸውን ብቻ ደፋር ፣ ራሳቸውን የሚገዙ፣ ቅዱሳን ፣ ነጻ ሰዎች። ነጻ ያልሆኑ ወይም አሳፋሪ ሥራዎችን በመመሰል ብልሃተኞች መሆን የለባቸውም ስለዚህ እውነተኛውን ጣዕም እንዳያገኙ ከማስመስል መራቅ አለባቸዉ። ማስመሰል በወጣትነት ከተደጋገመ በአካል፣ በድምፅና በአእምሮ ልማድ በመሆን ተፈጥሮ ውስጥ ይቆያል። በመቀጠል ጥሩ ሰዉ ሊመሰልበት የሚገባዉ እና የማይገባዉን ሶቅራጠስ ያስቀምጣል...
ጥሩ ሰዉ የሌላ ጥሩ ሰውን ቃልና ተግባር ሲያገኝ እንደ ራሱ ሆኖ ለመናገር አያፍርም በተለይ ጥሩው ሰው ያለ ስሕተት ደግ ስራን ሲሠራ። በሕመም፣ በፍትወት፣ በስካር የተናወጠውን ግን ለመምሰል ፈቃደኛ አይሆንም። መጥፎዉ ሰዉ ግን ማንኛውንም ነገር ለመተረክ ይፈቅዳል፤ ምንም ዝቅ ብሎ አይቆጥርም ነጎድጓድ፣ንፋስ፣ መሣሪያዎች፣ የእንስሳት ጩኸት ሁሉን ይመሰላል።
ከዚህም ቀጥሎ አዴይማንቶስ "የጥሩውን ሰው ንጹሕ አስመሳይ ብቻ ወደ ከተማዋ እናስገባለን" ይላል። ሶቅራጠስ ግን ድብልቁ ዘይቤ ደስ እንደሚያሰኝና ለልጆች፣ ለአስተማሪዎቻቸውና ለአብዛኛው ሰው ከሁሉ የሚያስደስተው ተቃራኒው እንደሆነ ያስታውሳል፤ ግን ከከተማችን ሕገ መንግሥት ጋር አይስማማም ፤ በእኛ ዘንድ ድርብ ወይም ብዙ ሰው የለም፣ እያንዳንዱ አንድ ሥራ ይሠራል (ጫማ ሠሪ ጫማ ሠሪ ነው እንጂ የመርከብ አለቃ አይደለም፤ ገበሬ ገበሬ እንጂ ዳኛ አይደለም፤ ወታደር ወታደር እንጂ ነጋዴ አይደለም)።  ታዲያ ሁሉን መመስል የሚችለዉ ሰው ግጥሞቹን ለማቅረብ ወደ ከተማችን ቢመጣ ቅዱስና አስደናቂ እንደሆነ እንሰግድለታለን፤ ግን በከተማችን እንዲህ ያለ ሰው እንደሌለና በመለኮታዊ ሕግ እንደማይፈቀድ እንነግረዋለን። ከዚያ ራሱን በሽቶ ቀብተን፣ በሱፍ አክሊል አስጊጠን ወደ ሌላ ከተማ እንልከዋለን። ለራሳችን ጥቅም ግን የበለጠ ጥብቅና ደስ የማያሰኝ ባለቅኔ እንቀጥራለን፤ እሱ የጥሩውን ሰው ንግግር ብቻ ይመስላል፣ ታሪኮቹም በመጀመሪያ ባስቀመጥናቸው ቅጦች ውስጥ ይሆናሉ።

ዘፈን ሦስት አካላት አሉት... ግጥም፣ ዜማ፣ ምት። ግጥሙ ቀደም ብለው ለተቀመጡት ቅጦች መታዘዝ አለበት፤ ዜማና ምት ደግሞ ግጥሙን ይከተላሉ። ሙሾ ከተወገደ የሙሾ ዜማዎችም ይወገዳሉ። ከዛም ባለፈ ስሜት ቀስቃሽ፣ፍርሃትን የሚነዙ፣ስካር እና ስንፍናን የሚጠሩ ዘፈኖችም ይታገዳሉ...ከዛ ሌላ ጀግንነትን የሚያበረታቱ ፤ ለመልካም ስራ የሚያነሳሱ እና አማልክትን የሚያሞግሱ ግጥሞች ይበረታታሉ። ሥዕል፣ ሽመና፣ ጥልፍ፣ ሥነ ሕንጻ፣ የዕቃ አሠራር እና የሕያዋን ፍጥረታት አካል ሁሉ ግርማ ወይም የግርማ እጦት አላቸው፤ የግርማ እጦት ከመጥፎ ንግግርና ከመጥፎ ባሕርይ ጋር ዝምድና አለው። ስለዚህ ባለቅኔዎችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሙያተኞችንም መቆጣጠር አለብን... በሥዕሎቻቸው፣ በሕንጻዎቻቸው የመጥፎ ባሕርይ ምስል እንዳይሠሩ፤ እንዲህ ማድረግ የማይችል በከተማችን እንዳይሠራ። ምክንያቱም ጠባቂዎቻችን "እንደ መጥፎ ሣር መስክ" በክፉ ምስሎች መካከል እየተመገቡ ቀስ በቀስ ሳያውቁ በነብሳቸው ታላቅ ክፋት እንዳይሰበስቡ ፤ ይልቁንም ከተፈጥሯቸው ውብና ግርማ ያለው ነገር የሚሠሩ ሙያተኞችን እንፈልጋለን፤ ወጣቶቹ ጤናማ ከሆነ ቦታ እንደሚመጣ ንፋስ ውብ ሥራዎች ዐይናቸውንና ጆሯቸውን ሲነኩ ሳያውቁ ከልጅነት ጀምሮ ከምክንያትና ውበት ጋር ተመሳሳይ፣ ወዳጅና ተስማሚ እየሆኑ ይመጣሉ። ምትና ዜማ የነብስን ውስጠኛ ክፍል ይገባሉ እና ከማንኛውም ነገር በላይ በኃይል ይነኩታል፤ በትክክል የተማረ ሰውን ግርማ ያለው ያደርጉታል፣ ያልተማረውን ተቃራኒ። በትክክል የተማረ ሰው ነገር ሲጎድል ወይም በጥሩ ሳይሠራ ሲቀር ወዲያው ያስተውላል፤ ስለዚህ ትክክለኛ ጥላቻ ስላለው ውብ ነገሮችን ያወድሳል፣ ይደሰትባቸዋል፣ ወደ ነብሱም ወስዶ ይመገባቸዋል፤ አስቀያሚውን ገና ወጣት ሳለ፣ ምክንያቱን ሳይረዳ በፊት ይጠላል። ምክንያት ሲመጣ ከራሱ ጋር ዝምድና ስላለው በቀላሉ ይለየዋል። ቀጥሎም ሶቅራጠስ ስለ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ያወራል...ጤናማ አካል በራሱ በጎነት ነብስን ጥሩ ያደርጋል ብሎ አያምንም፤ በተቃራኒው ጥሩ ነብስ በራሷ በጎነት አካልን በተቻለ መጠን ጥሩ ታደርጋለች። ስለዚህ አእምሮን በበቂ ሁኔታ ከጠበቅን አካልን ለእሱ ክትትል ሰጥተን አጠቃላይ ቅጦችን ብቻ እንጠቁማለን። ጠባቂ ሰካራም መሆን የለበትም (ጠባቂ ጠባቂ ሲፈልግ አስቂኝ ነውና)። የተለመደው የአትሌቶች አመጋገብ የሚያስተኛና ለጤና የማይታመን ነው፤ ተዋጊ አትሌቶቻችን እንደ ሌሊት እንደማይተኙ ውሾች ጥሩ ዕይታና መስማት ያላቸው፣ ውሃና ምግብ ለውጥ፣ የሙቀትና የክረምት ማዕበል መቋቋም የሚችሉ መሆን አለባቸው። ይሄንንም ከሆሜር መማር ይችላሉ...ጀግኖቹን በሄሌስፖንት ባሕር ዳርቻ እንኳ ዓሣ እየበሉ አያሳይም፤ የተጠበሰ ሥጋ ብቻ፣ ለማግኘት ቀላል የሆነውን፤ ወፍራም መረቅ አልጠቀሰም። ስለዚህ የሲራኩሳ ምግብ፣ የሲሲሊ ጣፋጭ መረቅ፣ የቆሮንቶስ ሴት ጓደኛና የአቲካ ጣፋጭ ዳቦ አያስፈልጉም።

ሶቅራጠስ አክሎም ልቅነትና በሽታ በከተማ ሲበዙ ብዙ ፍርድ ቤቶችና ክሊኒኮች ይከፈታሉ፤ ዳኞችና ሐኪሞች ነጻ ሰዎች ሳይቀሩ በቁም ነገር ሲወስዷቸው ኩራትን ያሳያሉ። ዝነኛ ሐኪሞችና ጠበቆች ለክፉ ሰዎችና ለእጅ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ነጻ ተብለው ለተማሩትም ሲያስፈልጉ ይህ ደካማና አሳፋሪ ትምህርት ምልክት ነው።በፍርድ ቤት ኑሮን ማሳለፍና በኢፍትሐዊነት የተካኑ መሆንን ማመስገን፣ ከአንድ የሚያንቀላፋ ዳኛ ፍርድ እንዳያስፈልግ ሕይወትን ማደራጀት የሚለውን የተሻለ መንገድ አለማወቅ ነዉ። ሐኪሞችም ከቁስል ወይም ከወቅታዊ በሽታ በቀር ለስንፍናና ለእንዲህ ያለ አኗኗር ሐኪም መፈለግ፤ የአስክሊፒያድ ሐኪሞች "ብርድ" እና "ጉንፋን" የመሰሉ አዳዲስ የበሽታ ስሞች እንዲፈጥሩ ይገደዳሉ ፤ በአስክሊፒዮስ ዘመን ግን እንዲህ ያሉ በሽታዎች አልነበሩም። ሄሮዲኮስ የአካል አሠልጣኝ የነበረ፣ ታምሞ በሥልጠናና በሕክምና ድብልቅ መጀመሪያ ራሱን፣ ከዚያም ብዙ ሌሎችን አሰቃየ፤ ሞቱን ረዥም ሂደት አደረገዉ። ዕድሜውን ሙሉ በሕክምና ሲኖር ለሌላ ነገር ጊዜ አልነበረውም። አናጢ ሲታመም ሐኪሙ ማስመለሻ፣ ማጽጃ፣ መቁረጫ ወይም ማቃጠያ ይሰጠዋል የሚል ተስፋ አለው፤ ረዥም ሕክምና ከተነገረው ግን ለመታመም ጊዜ የለኝም፤ እንዲህ መኖር አይጠቅመኝም ይላል፣ ወደ ሥራው ይመለሳል፤ ሰውነቱ ካልቻለ ይሞታል። ምክንያቱም የሚሠራው ሥራ አለው  ሳይሠራ መኖር አይጠቅመውምና።
👁 828 ❤ 5 вчера в 15:49
ከፍልስፍና ዓለም™ tg26 тыс. подписчиков
Открыть пост ↗
ሁለት ሶስቱ ስብሐት

በኢትዮጵያ ስነ_ፅሑፍ ዉስጥ ስማቸዉ በጉልህ ከሚነሱ ደራሲዎች መካከል አንደኛዉ ስብሐትላብ ገ/እግዚአብሔር ነዉ ።

ስብሐት አንድ ሁለት ሶስት ነዉ ስብሐት ከአብዮቱ በፊት የነበረዉ ስብሐት አብዮቱ ሲፈነዳ እና በአብዮቱ ጊዜ የነበረዉ ስብሐት እንዲሁም ድህረ አብዮት በኋላ የነበረዉ ስብሐት

ከብዮቱ በፊት የነበረዉ ስብሐት ዘናጭ የፕሮቶኮል ሰዉ በድርሰቱም ያን ያክል የማይታወቅ ስለ አለባበሱ እና ልብሶቹ የሚጨነቅ ሆኖም ግን ተራማጅነቱ አብሮት የነበረ ከፈረንሳይ ሀገር ትምህርት በኋላም የሚኒስቴር ልጅ ያገባ ወጣት ነበር ።

በአብዮቱ አካባቢ የነበረዉ ስብሐት ወደ ድርሰቱ ዓለም በጣም የቀረበዉ ወጎችን እና ተረቶችን በመፅሐፍ እየታወቀ የመጣበት ወቅት ነበር አብዮቱም ለእርሱ እንደ ደንቃራም እንደገና ሁለተኛዉን ስብሐት የተፈጠረበት ነበር ። ምክንያቱም አብዮቱ ሚኒስቴሮችን እና የኃይለስላሴ ባለስልጣናትን እያሳደደ የሚበላ ነበር በዚህ መካከል እርሱ ያገባት የሚኒስቴር ልጅ ነበረች ስሟም ሀና ትባላለች ልጅም ወልዳለታለች አብዮቱ ሊበላት አፉን እንደከፈተ ስለገባት ልጁን ይዛ ተሰዳለች በዚህ መካከል ነበር ስብሐት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበረዉ ።

አብዮቱ ጓድኞቹን በተለይም የሚወደዉን በዓሉ ግርማን በልቶበታል ሆኖም ግን እርሱ የጓድኞቹን ፅዋ ሳይቀምስ አልፎታል ምናልባትም ዕድለኝነትም ሊሆን ይችላል ብቻ ደረግ ካለፈ በኋላ ደረግ ሀገሪቱን እንዳመሳት በአንድ እንተርቪዉ ሲያወራ ሰምቸዋለሁ ።

ስብሐት በጣም የተሰበረበት እና ጨብራሪዉ ሰካራሙ ስብሐት የተፈጠረዉ በዚህኛዉ ህይወቱ ይመስለኛል ከመጀመሪያ ሚስቱ በኋላ ያገባት ሴተኛ ተዳዳሪ የሆነችዉ የትምወረቅ የምትባል ሴት ነዉ ። ይህች ሴትም ወንድ ልጅ ወለደችለት ህፃኑ ሲወለድ ፍልቅልቅ እና የሚያምር ነበር ሁልጊዜም በስስት ነበር የሚመለከተዉ ህፃኑ እያደገ ሲመጣ ግን ታማሚ ሆነ ሰዉነቱ ተቆለመመ እግሮቹ ተሳሰሩ መልኩ ተለወጠ እናት እና አባቱም ዉሏቸዉ እና አዳራቸዉ ሀኪም ቤት ሆነ ህክምናም መፍትሄ አልሰጥ አለ ልጁም ሌሊቱም ሙሉ ማልቀስ እና ማጓራት ሆነ ከወላጆቹ አልፎ ጎረቤትንም ረበሸ እዚህ ላይ ስብሐት መቋቋም አልቻለም የሌሊቱን ጮኽት ለመርሳት መጠጣት እና እየሰከረ መግባት ጀመረ በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለ ራሱን ሊያጣ እንደሚችል ጓድኞቹ ስላመኑ ተመካክረዉ አዲስ ሀሳብ አቀረቡ ታማሚዉን ልጅ ለማደጎ ይሰጥ የሚል ስብሐት ተቃወመ ግን እነ ባሴ ሐብቴ አግባብተዉ አሳመኑት አይኑ እያያ ለአሳዳጊ ድረጅት ፈረሞ ሰጠ በዚህም እጅግ አምርሮ እና ተንሰቅስቆ አለቀሰ እስከለተ ሞቱ ድረስ ስለዚህ ልጅ ምንም ነገር አልሰማም ግን መብሰልሰሉ እንዳልተወ በዙሪያዉ የነበሩ ሰዎች ይናገራሉ ።

ደህረ አብዮት የነበረዉ ስብሐት አድናቂዎቹ ጋር መቃበጥ የሚወደዉ ስብሐት ወጣት ሴቶች ጋር ፍቅር መስራት የሚወደዉ ስብሐት ( ሀቂቃዉ መ**ዳት የሚወድ ) ይበልጥ ተፈጥሯዊ ፅሐፊ እንደሆነ የታወቀዉ ስብሐት ሆነ በዚህ ህይወቱም ግን ስቃዬ አላመለጠዉም የሚወዳት ዜና የተሰኘች ልጅ ሙታበታለች የሷ ሀዘንም ሰብሮታል በዚህ ሀዘን እና እንግልት ሆኖም እንኳን እንደልቡ ኑሮ ሟቷል በመጨረሻ ዕድሚዉ አካባቢ በሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ቃልኪዳን የተሰኘች ወጣት አግብቶ ነበር ።

ስብሐት ብዙ ነዉ እዚህ በላይ ብዙ ታሪኮችን እንመዛለን የስብሐት ገድል ተፅፎ አያልቅም እንቀጥለዋለን አሁን ግን በጣም የምትታወቅለትን አባባል ብለን ትረካችንን እንቋጫለን ፦

... ተዘጋጀህም አልተዘጋጀህም ጉዳዩ አንድ ቀን ያበቃል ። ሀብትህ ዝናህ እና አለማዊ ሃያልነትህ መንምኖ እዚህ ግባ የማይባል ይሆናል ። ምን ምን የግልህ እንደነበረ ወይም ምን ምን ዕዳ ሊከፈልህ ሊገባ እንደነበረ ልዩነት አያመጣም ። ከየት መጣህ የደስተኛ ወይም መከረኛ ኑሮ አሳለፍክ በመጨረሻ ልዩነት አይኖረዉም ። መልከ ቀና ነበርክ ወይስ ጥበበኛ ? ልዩነት አያመጣም ። ፆታህና የቆዳህ ቀለም ሳይቀር እዚህ ግባ የማይባል ኢምንት ሆኖ ይቀራል ....
👁 1.9 тыс. 👍 28❤ 17💔 4 💬 12 ↻ 12 13 ноября