1. የንግድ ወኪሎች (Commercial Agents)
እቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ከአስመጪ፣ ከአምራች ወይም ከሌላ አገልግሎት ሰጪ በውክልና ተረክበው በወካያቸው ስም የሚሸጡ እና የሸጡበትን ዋጋ ለወካያቸው የሚያስረክቡ የንግድ ወኪሎች፤ አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚከፍሉት በሚያገኙት የኮሚሽን ክፍያ ላይ ነው።
2. የጅምላ ሻጮች እና የኅዳግ (Margin) ስሌት
የጅምላ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ግብር ከፋዮች ከአምራቹ፣ ከአስመጪው ወይም ከሌላ ጅምላ ሻጭ ጋር ባደረጉት ውል መሰረት ለቸርቻሪዎች ወይም ለሌሎች ጅምላ ሻጮች በሚሸጡበት ጊዜ ከሽያጩ የሚኖራቸው ድርሻ (Margin) በውል በመቶኛ የተወሰነ ከሆነ፤ አማራጭ አነስተኛ ግብሩ የሚሰላው በሚከፈላቸው መቶኛ ላይ ይሆናል።
አምራቹ/አስመጪው እና ጅምላ ሻጩ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋውን እና የኅዳግ/የኮሚሽን መጠኑን በውል ከወሰኑ፣ የታክስ ባለሥልጣኑ ሂሳብ ሲመረምር እነዚህን ውሎች በአንድነት ማየት አለበት።
3. የሰነድ አቀራረብ እና ማረጋገጫ ግዴታ
በውል የተወሰነውን መቶኛ መሰረት አድርጎ ግብር ለማስላት የሚከተሉት ሕጋዊ ሰነዶች ለታክስ ባለሥልጣኑ ቀርበው መመረመር ይኖርባቸዋል፡
አከፋፋዩ ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው የገዛበትን ዋጋ የሚያሳይ ደረሰኝ፣
ለቸርቻሪዎች ወይም ለሌሎች ወገኖች ሽያጭ የፈጸመበት ሕጋዊ ደረሰኝ፣
ለጉዳዩ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች የሂሳብ ሰነዶች።
4. የሰነድ ማረጋገጫ ካልተገኘ ወይም ከስምምነት ውጪ ከተከናወነ
የቀረቡት ሰነዶች ምርቱ ወይም አገልግሎቱ በአምራቹ/አስመጪው በተወሰነው የዋጋ ገደብ መሰረት መሸጡን ማረጋገጥ ካልቻሉ፣ ወይም ከስምምነት ውጪ ግብይት መፈጸሙ ከተረጋገጠ፤ የታክስ ባለሥልጣኑ አማራጭ አነስተኛ ግብሩን በግብር ከፋዩ ዓመታዊ ሽያጭ ላይ መሰረት በማድረግ ተፈፃሚ ያደርጋል።
ሕጉን ጥሶ በሌላ ዋጋ ወይም ከስምምነት ውጭ ግብይት ፈጽሞ የነበረ ግብር ከፋይ በሂሳብ ምርመራ ወቅት ከተገኘ፣ ቀደም ሲል ተከፍሎ የነበረው ግብር በታክስ አስተዳደር አዋጁ መሠረት እንደገና ተሰልቶ ልዩነቱ በግብር ከፋዩ እንዲከፍል ይደረጋል።
*ለተጨማሪ መረጃ የገቢ ግብር ደንብ ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 597/2019 ይመልከቱ
ግብር÷ ለሃገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡-
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2