በአዲስ አበባ ከ12ኛ ፎቅ ላይ የወደቁ ሦስት የግንባታ ሠራተኞች ሕይወታቸው አለፈ።
በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9፣ ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚያመራው መንገድ፣ ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በሚገኝ በግንባታ ላይ ባለ ሕንፃ ላይ ዛሬ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ገደማ አሳዛኝ የሥራ ላይ አደጋ ደርሷል።
አደጋው የተከሰተው ሦስቱ ሠራተኞች በሕንፃው ላይ የዕለት ተዕለት የግንባታ ሥራቸውን እያከናወኑ ሳለ ቆመውበት የነበረው ርብራብ በድንገት በመፍረሱ ከ12ኛ ፎቅ ላይ በመውደቃቸው ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ ለኤኤምኤን በሰጡት መግለጫ፣ ሦስቱም ሠራተኞች በአደጋው ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች የአደጋውን መንስኤና ዝርዝር ሁኔታ ለማጣራት ምርመራ እያካሄዱ ሲሆን፣ የምርመራው ውጤት ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።
⚠️ የኢትዮ ኮን ማሳሰቢያ
ይህ አሳዛኝ ክስተት በግንባታ ሥራዎች ውስጥ የሠራተኞች ደህንነት፣ የጊዜያዊ የሥራ መዋቅሮች ጥንካሬ፣ የደህንነት መሣሪያዎች አጠቃቀምና ተገቢ የሥራ ቦታ ቁጥጥር ምን ያህል ወሳኝ እንደሆኑ በድጋሚ ያሳስበናል።
በግንባታ ዘርፍ የሚፈጠር እያንዳንዱ አደጋ የሰው ሕይወትን ከማጥፋቱ በተጨማሪ ቤተሰብን፣ የሥራ ባልደረቦችንና መላውን የግንባታ ዘርፍ የሚነካ ኪሳራ ነው።
በዚህ አሳዛኝ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሠራተኞች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና የሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።
የሰው ሕይወት ከማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክት የበለጠ ዋጋ አለው!
📌 ኢትዮ ኮን | ETHIO CON የግንባታ፣ የመሠረተ ልማትና የሪል እስቴት ዘርፍ መረጃዎችና ትንታኔዎች።
📲 ለተጨማሪ መረጃዎች ይቀላቀሉን፦ https://t.me/ethioconradio
#ኢትዮኮን #EthioCon #የግንባታደህንነት #ConstructionSafety #የሥራቦታደህንነት